Sunday, 01 September 2024 20:16

ታካሚዎች ሐኪም ጋ መች ይቅረቡ?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

  ‹‹‹…..እንደ ጽንስና ማህጸን ህክምና ተቋም ያልታመሙ ሰዎች ለህክምና ይቀርባሉ፡፡ ለምሳሌ እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ያልታመሙ ናቸው፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የሚሰጣቸው እናቶች ያልታመሙ ናቸው፡፡…››
ይህንን ያሉት ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ የማህጸንና ጸንስ ህክምና እስፔሻሊስትና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የመካንነትና ከስነተዋልዶ ጤና ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሆርሞን ችግሮች እስፔሻሊስትነት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በመማር ላይ የሚገኙት ናቸው ፡፡ ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ ስለህክምና ስነምግባር ባለፈው እትም ሲያብራሩ የሚከተሉትን የስነምግባር እሴቶች ገልጸው ነበር፡፡
በህክምናው አለም የሚተገበሩ የስነምግባር እሴቶች፡-
የታካሚን ግለሰባዊ ማንነት ማክበር፡፡
ታካሚን የሚጠቅም ነገር ማድረግ፡፡
ታካሚን አለመጉዳት፡፡
ለታካሚ ፍትህ መስጠት፡፡
በዚህ እትም የምናተኩረው በተለይም ስለታካሚዎች ሁኔታ ይሆናል፡፡ ለመሆኑ ታካሚዎች መች ነው ወደሐኪማቸው መቅረብ ያለባቸው ለሚለው ጥያቄ ዶ/ር ገላኔ ሲመልሱ እኛጋ ያልታመሙ ሰዎችን እናክማለን ብለዋል፡፡ ለምሳሌም እርጉዝ ሴቶች ያልታመሙ ናቸው፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ ለመጠቀም የሚፈልጉ ጥንዶችም የታመሙ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና ተቋም ለመምጣት የግድ የታመሙ ሰዎች መሆን የለባቸ ውም፡፡ ይህ ማለት ግን ወደህክምና ተቋሙ የሚሄዱ ሁሉ ህመም የገጠማቸው አይደሉም ለማለት አይደለም፡፡ በተለያዩ መንገዶች ከመራብያ አካላት ጋር በተገናኘ ሕመም የገጠ ማቸው ወደህክምና ተቋሙ በሚቀርቡበት ጊዜ መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ያስፈልጋል፡፡
የታካሚዎች መብት፡-
ታካሚዎች ወደ ሐኪም ከቀረቡ በሁዋላ ሐኪሙ ስለህመማቸው በምርመራ ያገኘውን ውጤት የመረዳት መብት አላቸው ፡፡የሚታዘዝላቸውን ምርመራ ወይም ቀጣይ ህክምና የመጠየቅና የመረዳት መብት አላቸው፡፡ አማራጭ መንገዶችን …ለምሳሌ ይህንን መድሀኒት ብለውጥስ….መድሀኒት ባልወስድስ….ይሄ ቀዶ ህክምና ባይደረግልኝስ በሌላ ዘዴ መዳን አልችልም ወይ….እና የመሳሰሉትን ሁሉ በግልጽ ከሐኪ ማቸው ጋር መወያየት መብታ ቸው ነው፡፡ የህክምና ተቋሙ በሚፈቅደው ህግ መሰረት አገልግሎን ማግኘት አለባቸው፡፡ ተገቢው የሆነ መጠይቅ ቀርቦ፤አካላዊ ምርመራ ተደርጎላቸው የገጠማቸው የጤና እክል መገኘት አለበት፡፡ አንድ ታካሚ መረጃ ላይ የተመሰረተ ሕክምና ማግኘት መብት አለው፡፡
የታካሚዎች ግዴታ፡-
አንድ ታካሚ ወደ ሐኪም በሚቀርብበት ጊዜ ለሚጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ለምሳሌ አንድ ታካሚ በመጀመሪያ በቀረበበት የህክምና ተቋም በጤንነቱ ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ፤ የቀዶ ሕክምና ለማድረግ ምን አይነት ጥንቃቄ ወይንም ቅድመ ሕክምና እንደሚያስፈልገው የመሳሰሉት መረጃዎች ሲሰጣቸው ይህንን መረጃ እንደስህተት ቆጥረው የታማው መረጃ በጭራሽ በማይታወቅበት ሌላ የህክምና ተቋም በመሄድ የተነገራ ቸውን ነገር በመደበቅ ህክምና ለማድረግ ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ ምናልባትም አንዳንድ ጊዜ ስለሁኔታው ሊታወቅ የሚችልበት ምንም ፍንጭ ሳይገኝ የቀዶ ህክምናው በሚደረግት ጊዜ ታካው ከአደጋ ላይ ሊወድቅ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል፡፡ ታካሚዎች ወይንም ቤተሰቦቻቸው የጤና ችግራቸውን በሚመለከት በመጀመሪያ ከሄዱበት ሆስፒታል ያገኙትን መረጃ ቢችሉ ከሆስፒታሉ ጠይቀው .ካልሆነም የተነገራቸውን ነገር በመንገር ሕክምናቸውን መቀጠል ሲገባቸው እንደ አዲስ ምንም እንደማያውቁ በመሆን ህክምናን ማድረግ ምናልባት ችግር ያስከትላል ብሎ አስቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡
ሐኪም ሁሉንም ነገር ያውቃል ብለው ሰዎች ያስባሉ፡፡ ግን ሐኪም ስራውን የሚሰራው የሚቀርብለትን መረጃ በማየት በመመርመር እንጂ ሁሉንም ነገር ከምንም ተነስቶ በመገ መት አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጣም ጎበዝ ሐኪም የተባለ ሰው አንዲት ትንሽ ነገርን በመሳት ችግር ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለዚህ ታሚዎች በራሳቸው በኩል ያለውን ማንኛውንም መረጃ ለሐኪማቸው በግልጽ ሊያስረዱ ይገባቸዋል፡፡ እንደዚህ ያለ ሆስፒታል ሄጄ እንደዚህ ተብያለሁ፡፡ እስቲ እናንተ ደግሞ መርምሩኝና ምን ችግር እንዳለብኝ ልወቅ ብሎ መጠየቅ ከማንኛውም ሰው የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡    
የሐኪምና ታካሚ ግንኙነት በከበሬታ እና በአመኔታ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ አንድ ታካሚ በህክምናው ዓለም ትክክለኛውን ያደርጋል ብሎ ከማያምነው ባለሙያ ወይንም የጤና ተቋም ጋ እንዲሄድ አይገደድም፡፡ ግንኙነቱ ከሁሉ አስቀድሞ በጥሩ መንፈስ ቢሆን ይመረ ጣል፡፡ ህክምናው ከተጀመረ በሁዋላ ደግሞ ለሚሰጡት ምክሮች ወይንም በምርመራው ለሚ ገኙ ችግሮች የታካሚው አቅም በፈቀደው መንገድ በጊዜው አስፈላጊው አገልግሎት እንሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን የሚያጋጥሙ አስቸጋሪ ነገሮች አሉ ፡፡ ለምሳሌም በማለት ዶ/ር ገላኔ የሚከተለውን ጠቅሰዋል፡፡
‹‹….አንዲት ታካሚ አስፈላጊው ምርመራ ሁሉ ተደርጎለት የጤናው ችግር ምን እንደሆነና ሕክምናውም በምን ሁኔታ ሊሰጥ እንደሚገባ ከቤተሰቡ ጋር ምክክር ተደረገ፡፡ ቤተሰቦቹ ለህ ክምናው የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟልተው አመሻሹ ላይ መድሀኒት እንዲጀመርና በነጋ ታው ቀዶ ህክምና እንደሚደረግ ተነግሮአቸው ይሄዳሉ፡፡ ቤተሰቦች ታካሚውን ይዘው እንደ ሄዱ ባልታወቀ ምክንያት የተወሰነ ጊዜ ይቆያሉ፡፡ እንደገና ተመልሰው ሲመጡ ሕመሙ የመስፋፋት እድሉ ጨምሮአል፡፡ በዚህ ጊዜ ታካሚዋን የማቆየት እንጂ የማዳን እድሉ ይዳ ከማል፡፡…››ብለዋል ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን አይነት አጋጣሚዎች በብዛት የሚታዩ ናቸው፡፡ አንድ ታካሚ በአንድ የህክምና ተቋም መጀመሪያ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሌላ ተቋም መሄድ የለበትም የሚል እምነት የለም፡፡ በእርግጥ ሁሉም የጤና ተቋማት ህክምናውን የሚሰጡባቸው ዘዴ ዎችና የበጀት ሁኔታ እኩል አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ታካሚ ደግሞ አቅሙ ከሚፈቅደው ቦታ ሄዶ ህክምናውን የማድረግ መብት እንዳለው መረዳት አለበት፡፡ እዚህ ላይ ታካሚ ወይንም ቤተሰብ ሊረዳ የሚገባው ህመም ሲከሰት በፍጥነት ወደ ህክምና ማምራት፤ በመጀመሪያ በተደረገ ምርመራ የተገኘውን ውጤት ችላ ካለማለት በሚቻለው ሁሉ ህክም ናው  እንዲገኝ ማድረግ ይገባል፡፡
እዚህ ላይ የአንዲትን ሴት ታሪክ ለአንባቢዎች ማጋራት ወደድን፡፡ ሴትየዋ በማህጸን ካንሰር መያዝዋን አላወቀችም፡፡ በእርግጥ ሕመሙ ብዙ ጊዜ ምልክቱን ሳያሳይ ስለሚቆይ የብዙ ሴቶች የጤና ችግር ነው፡፡ እንደአጋጣሚ ሆኖ ግን ህክምና ስትጀ ምር የካንሰር ህመሙ ገና አንደኛ ደረጃ ላይ ነበር፡፡ ሐኪሙዋም እድለኛ ነሽ ትድኛ ለሽ፡፡ ምክንያቱም ካንሰሩ ገና አን ደኛ ደረጃ ላይ ነው ይላታል፡፡ እሱዋም መጀመሪያ ከታከ መች በሁዋላ ለክትትል በተቀጠ ረችበት ወቅት ሳትመለስ ትቀራለች፡፡ ከቆይታ በሁዋላ ግን ህመም ሲያስቸግራት እንደገና ወደሐኪምዋ ትመለሳለች፡፡ ሐኪምዋ እጅግ በጣም ነበር ያዘነው፡፡ ምን ሆነሽ ነው ለክትትል በተቀጠርሽበት ጊዜ ያልመጣሽው ? ይህን ያህል ጊዜስ ለምን ቆየሽ ሲላት…. አ..አ..ይ…እድለኛ ነሽ ትድኛለሽ ስላልከኝ ….በቃ እድናለሁ….ገንዘቤን ለምን አወጣለሁ ብዬ ነው ነበር ያለችው፡፡ የካንሰር ደረጃው ግን መዳን ከማይችልበት ደረጃ ስለደረሰ ሴትየዋ ለህልፈት ተዳርጋለች፡፡ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን በትክክል ያለመረዳትና ለጤና ቅድሚያ ያለመስጠት ነገሮች ይስተዋላሉ፡፡
አንዳድ ጊዜ በሐኪሞች ስህተት ሞተ ወይንም ሞተች ሲባል ይሰማል፡፡ ይህ አጋጣሚ ምናልባት ታካሚዎች ያለባቸውን የጤና ችግር ቀድመው ካለመረዳት ወይንም በአካባ ቢያቸው ላሉ ሰዎች አለማስረዳታቸው ይሁን ወይንም የህክምና ስህተት ተፈጥሮ ይሁን በምን መረጋገጥ ይችላል ለሚለው ሀሳብ ዶ/ር ገላኔ ሲመልሱ አንድ የማይፈለግ ሁኔታ በራስም ላይ ይሁን በቤተስብ ላይ ሲደርስ በተለያዩ ደረጃዎች ለተቀመጡ አካላት ጉዳዩን ማመልከት ይገባል፡፡ እንደዚህ ያለውን ቅሬታ የሆስፒታል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፤የስነምግባር ኮሚቴ ወይንም በቀ ጥታ የሆስ ፒታሉ አስተዳደር ጉዳዩን የሚመለከትበት አሰራር አለ፡፡ ከዚያም በላይ በጤና ቢሮዎች የተ ቋቋሙ የስነምግባር ኮሚቴዎች ወይንም በፍርድቤቶች ጉዳዩ እንዲታይ ማድ ረግ ይቻ ላል፡፡ አንድ ህክምና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ በነበረው ምርመራ በመሳሰሉት የነበረው ታሪክ ምንድነው? ህክምናው በምን ሁኔታ ነው የተሰጠው? ምንድን ነበር የሚጠበ ቀው? ከህክም ናው በሁዋላ ታካሚው ቢሞት ለዚያ የሚያበቃ ምን የህክምና ስህተት ታይቶ አል? …ወዘተ የመሳሰሉት ነገሮች ሳይታዩ አንዳንድ ጊዜ የሚሰጡ ሚዛናዊ ያልሆኑ አስተ ያየቶች በታካሚ ውና አካሚው መካከል ያለውን ግንኙነት እንደ ሚያሻክር አስቀድሞ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል ብለዋል ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት፡፡                      

Read 359 times