የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
እኔ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በነበርንበት ሰፈር በየግቢው ሀያ ሠላሳ ቤተሰብ ሆነን ነበር የምንኖረው። የቤተሰብ ብዛት ሲታሰብ፤ በአንድ ግቢ ውስጥ መቶ ሁለት መቶ ሰው ይሆናል። አዲስ መኖሪያ ቤት፣ ሁሉም ቤተሰብ የየራሱ መታጠቢያ መጸዳጃ ቤት፣ የየራሱ ማድ-ቤት ሲያገኝ ደስ ይላል።
ዛሬ ደግሞ አይቼ የማላውቀውን አከባበር አይቻለሁ። በ65 ዓመት ዕድሜዬ፣ ከንቲባ በዐይኔ አይቼ አላውቅም። እዚህ መጥተው ሲያበረታቱን፣ ለጥያቄዎችም ጥሩ ምላሽ ሲሰጡን… በጣም ደስ ብሎኛ። በጣም ረክቻለሁ።
=======================
ክብርት ከንቲባ ቤት-ለእንቦሳ ሊሉን መጥተዋል። ባዶ እጃቸውን አልመጡም። ቡና አፍልተን የምንጠጣው ይዘውልን መጥተዋል። ለምግባችንም ሰርተን የምንመገበውን ስጦታ አበርክተውልናል።
====================
ከንቲባዋም እዚህ መጥተው ጠይቀውናል። እንዴት እንዴት እየሆናችሁ ነው ብለው ለመጠየቅና በአካል ለማየት ብለው ነው የመጡት። የሥራ ጊዜያቸውን አብቃቅተው እኛን ለመጠየቅ ስለመጡ ደስ ብሎናል። በጣም እናመሰግናለን።
========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
=========================
በጣም ደስ የሚል ሰፈር ነው የገባነው። አየሩ ራሱ ይመቻል። በተለይ ለእኛ ለሽማግሌዎች ጥሩ አየር ማግኘታችን ጥሩ ነው። አየሩ በጣም ተስማምቶኛል። መንገድ ነበር ችግሩ። አስፋልት አይደለም።
መንገዱን ቶሎ እንሠራዋለን ብለውናል። ትራንስፖርት እዚህ ስለማይደርስ ያስቸግራል። አውቶቡስ ይመደባል ብለው ቃል ገብተውልናል። በዚህ ደስ ብሎኛል።
===========================
ጥራቱን የጠበቀ ቤት ውስጥ ነው የገባነው። መጸዳጃ ቤትም፣ ማድቤትም… ሁሉም ነገር የተሟላ ቤት ነው። ከተጎሳቆለ ጭቃ ቤት ተገላግለናል። ዕድለኛ ነን። ቅር የሚል ነገር የለም። ከዛ ክፉ ችግር ተላቅቄ እዚህ መድረሴ ትልቅ ነገር ነው። ያላሰብነውን ነው ያገኘነው።
እንደዚህ ዐይነት ዕድል ማን ያገኛል? ቦታው ሩቅ አይደለም። መሀል ከተማ ነው። መንገዱ ጭቃ የለው! ምን የለው! ምስጋና ይድረው።
=======================
አዲሱ ሰፈራችን ጥሩ ነው። የነበርንበት ሰፈር፣ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። መጸዳጃ ቤት ሁል ጊዜ ችግር ነበር። ወረፋ ነው። ፍሳሽም አለ። የወዲህኛው ቤት ደህና ቢሆን፣ ከወዲያኛው ወይም ከጓሮ በኩል ፍሳሽ ይመጣል። በጣም ይረብሻል። ብቻ… ብዙ ችግር ነበር። ወደ አዲሱ ሰፈራችን ስንገባ አስተዳደሩ ጥሩ ድጋፍና አቀባበል አድርጎልናል። የዕቃ ለማጓጓዝ የከተማው አስተዳደር የጭነት መኪኖችን በነፃ ሰጥቶናል። የጫኝ የአውራጅ ወጪም አልነበረብንም። በከተማው አስተዳደር ድጋፍ በነፃ ነው።
ሌላው በጣም ደስ ያለኝ ነገር፣ የመኖሪያ ቤት አመዳደብ ነው። አካል ጉዳተኞችና በዕድሜ የገፉ አዛውንት፣ በመኖሪያ ሕንጻው እንዳይቸገሩ የታችኛው ፎቅ ላይ ተስማሚ ቤት አግኝተዋል። ጥሩ አስበውበታል። የሚመሰገን ተግባር ነው።
Saturday, 19 October 2024 12:47
የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ሐሳብ ከራሳቸው አንደበት በዐጭር በዐጭሩ እነሆ።
Written by Administrator
Published in
ባህል