Friday, 22 November 2024 07:24

የከተማ አስተዳደሩ መርካቶ ሸማ ተራ በእሳት አደጋ ሱቅ ለተቃጠለለባቸው ነጋዴዎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እስኪገነባ ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል።

በአካባቢው ያለውን ጥግጊትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ጨምረው ገልጸዋል።

ከከንቲባ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ድጋፉን የተቀበሉት የአካባቢው ነጋዴዎች ተወካዮች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው ድጋፉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

Read 843 times