ሴቶች በተፈጥሮአቸው የወር አበባ መታየት የሚጀምርበት እና የሚቋረጥበት የእድሜ ክልል ያላቸው መሆኑ ተደጋግሞ የሚነሳ ነገር ነው፡፡ ታድያ አልፎ አልፎ የጋጥም ነገር አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች የወር አበባቸው ትክክለኛው እድሜ ደርሶ ከተቋረጠ (Menopause) በሁ ዋላ ዘግይቶ እንደ ገና የወር አበባ መሰል የደም ፍሰት ይስተዋላል፡፡ ታዲያ ይሄ ምንድነው ስንል ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እና የመራብያ አካላት ካንሰር Oncology gynecology ህክምና እስፔሻሊስትን ማብራሪያ ጠይቀ ናል፡፡
የወር አበባ መቋረጥ ጤናማና ጤናማ ያልሆነ ተብሎ ይገለጻል፡፡ ጤናማ የወር አበባ መቋረጥ (Menopause) የሚባለው ሴትዋ የመውለጃ እድሜዋ ሲያበቃ በአብዛኛውም በአርባዎቹ ወይም ወደህምሳው ሲጠጋ የሚኖረው የደም መፍሰስ መቋረጥ ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ከዘር ፍሬ ማለቅ ጋር ተያይዞ ጊዜው ሳይደርስ ገና በወጣትነት እድሜ ከሰላሳ አመት በታች እያሉ የወር አበባ መቋረጥ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህኛው ካለጊዜው የተቋረጠ በመሆኑ ከጤናማው የወር አበባ መቋረጥ ይለያል፡፡
አንዲት ሴት የወር አበባዋ ተቋርጦአል (Menopause) ገብታለች የምትባለው እድሜዋ በወር አበባ መቆሚያ እድሜ ውስጥ ከሆነ እና ለአንድ አመት የወር አበባ ሳታይ ከቆየች ነው፡፡ ከዚያ በሁዋላ ያለው ጊዜ Post Menopause ወይም የወር አበባ ከቆመ በሁዋላ ተብሎ ይጠቀሳል፡፡ በሌላው አጠቃቀስ ከ Menopause በፊት ያለው የመውለጃ ጊዜ ሲሆን ከዚያ በሁዋላ ደግሞ የመውለጃ ጊዜ ያልሆነ ወቅት ይባላል፡፡
የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚታይ የደም ፍሰት ወይም ነጠብጣብ ካለ Post Menopause Bleeding ወይም የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ ተመልሶ የመጣ የደም መፍሰስ ይባላል፡፡ ይሄ የደም መፍሰስ ከትክክለኛው የወር አበባ ጋር ሲነጻጸር አለአግባብ የተከሰተ ስለሆነ ባብዛኛውም የሚያያዘው ከአንዳንድ የስነ ተዋልዶ ጤና ሁኔታዎች ጋር ነው፡፡ ስለዚህም ጤናማ ነው ተብሎ የማይታሰብ እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነው፡፡ ዶ/ር ታደሰ እንዳሉት አንዲት ሴት ከተገ ቢው የእድሜ ክልል ደርሳ በትክክለኛው ተፈጥሮአዊ ወቅት የወር አበባ መቋረጥ ከተከሰተ በሁ ዋላ እንደገና የወር አበባ ማየትዋ ጤናማ ያልሆነ ሁኔታን ይጠቁማል ሲባል በዚህ ጊዜ የሚታ የው የደም መፍሰስ ቀድሞ በመውለጃ እድሜ ከነበረው የደም መፍሰስ ጋር ሲነጻጸር ከበሽታ ጋር የመያያዝ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ነገር ግን በደፈናው ሁሉም ከበሽታ ጋር ተያያዥ ናቸው ለማለትም አይደለም፡፡ ይን እንጂ የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ እንደገና የሚታየው የደም መፍ ሰስ ለበሽታ የመጋጥ እድሉ ሰፊ ነው ለማለት ያህል ነው፡፡ የሚረጋገጠው ደግሞ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው፡፡
ሁለት የሚነጻጸሩ ነገሮች አሉ እንደ ዶ/ር ታደሰ ማብራሪያ፡፡ በወር አበባ መካከል የሚፈስ ደም እና የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚፈስ ደም፡፡ በሁለቱም ወቅት አለአግባብ የሚፈስ ደም ጤናማ ነው ተብሎ ባይወሰድም በወር አበባ መካከል ከሚፈሰው ደም ይልቅ የወር አበባ ከተቋ ረጠ በሁዋላ የሚፈሰው ደም በአብዛኛው ከበሽታ ጋር የሚገናኝ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ ነገር በምርመራ እስኪታወቅ ድረስ እንዲህ ነው ብሎ የበሽታውን አይነት ለይቶ ለመናገር ቢያስቸ ግርም ብዙውን ጊዜ ግን ከማህጸን ግድግዳ ካንሰር ጋር የሚገናኝ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ይሁን እንጂ የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚታይ ደም ሁሉም ከማህጸን ካንሰር ጋር የሚያ ያዝ ነው ማለትም አይደለም ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በራሳ ቸው ሊድኑ የሚችሉ ናቸው፡፡ ግን የማህጸን ግድግዳ ካንሰር አለ ወይም የለም የሚለውን ለመወ ሰን ወደ ህክምናው ቀርቦ ምር መራ በማድረግ ማረጋገጥ ተገቢ ነው ብለዋል ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ፡፡
አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ከመቋረጡ በፊት በየመሐሉ የሚታያቸውን የደም መፍሰስ የወር አበባዬ ካለጊዜው ወይንም ከተቋረጠ በሁዋላ እንደገና መጣብኝ ከማለት ውጭ ትኩረት በመስ ጠት ብዙም ጊዜ ወደ ሐኪም አይቀርቡም ፡፡ የዚህን ምንነት ዶር ሲያብራሩ ጤናማ ከሆነው የወር አበባ አፈሳሰስ ውጭ የሚታየው የደም መፍሰስ ጤናማ ያልሆነ የደም መፍሰስ ነው፡፡ ጤናማ የወር አበባ የሚባለው በወር አንድ ጊዜ በአብዛኛው በ28 ቀን የሚመጣው ነው፡፡ የዚህ የወር አበባ ፍሰት መጠን መካከለኛ የሆነ ሲሆን የሚቆየውም ለጥቂት ቀናት ነው፡፡ ይህ ጤናማ የወር አበባ ከደም መጉዋጎል ጋር ያልተያያዘ ነው፡፡ ከዚህ ጤናማ ከሆነው የወር አበባ መፍሰስ ውጭ የሆነው ለብዙ ቀን መጠኑም ብዙ ሆኖ ሊፈስ ይችላል፡፡ በአንድ ወር ጊዜ ሁለት ሶስት ጊዜ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል፡፡ እንደዚህ በሚሆንበት ወቅት ጤናማ ያልሆነ የደም መፍሰስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ ጤናማ ያልሆነው የደም መፍሰስ በመውለጃ እድሜ ክልል ውስጥ ሆነው ሲከሰት እና የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ ከሚከሰተው ጋር ሲነጻጸር በመውለጃ እድሜ ላይ እያሉ የሚከሰተው የደም መፍሰስ ባብዛኛው ቀላል ከሆኑ ነገሮች ጋር የሚያያዝ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከመጥፎ ነገሮች ጋር የመያያዝ እድሉ ሲነጻጸር ይሄኛው ቀላል ሲሆን የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚከሰተው ግን ከባድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ጤናማ ላልሆነው በተለይም የወር አበባ ከተቋረጠ በሁዋላ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ አጋላጭ የሆኑ ነገሮች ምንድናቸው ሲባል በተለይም እድሜ አንዱ ነው ብለዋል ዶ/ር ታደሰ፡፡ እድሜ በጨመረ ቁጥር መጥፎ ከሆኑ የማህጸን ችግሮች ጋር የመያያዝ እድሉ የጨመረ ይሆናል፡፡ የወር አበባ ከመቆሙ በፊት የመውለጃ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን በቀላሉ ምርመራ በማ ድረግ የሚታከም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በመውለጃ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ አጋላጭ ምክንያት ካላቸው እነሱም ከበድ ያለ ምርመራና ሕክምና ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ለማህጸን ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ የደም ግፊት፤የስኩዋር ህመም፤የተለያዩ መድሀኒቶችን መውሰድ፤ሆርሞኖችን መውሰድ የመሳሰሉት ለዚህ ችግር ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው በተቻለ መጠን ምርመራ በማድረግ ችግር መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ የሚገ ባው፡፡የወር አበባ ሳይቋረጥም ሆነ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚፈስ ደምን ምክንያት ማወቅ የሚያስ ፈልገው በተለይም ከማህጸን ግድግዳ ካንሰር ጋር መያያዝ አለመያያዙን ለማወቅ ነው፡፡
ለ Post Menopause Bleeding የሚሰጠው ህክምና በበሽታው ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል፡፡ ትልቁ ነገርም የማህጸን ካንሰር መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ ነው፡፡ የማህጸን ካንሰር ከሌለ ቀለል ባለ የህክምና ዘዴ የደም መፍሰሱን ማቆም ይቻላል፡፡ ካንሰር ከሆነ ግን እንደደረጃው የሚወሰን ይሆናል፡፡ ደረጃው ዝቅ ያለ ከሆነ ኦፕራሲዮን በማድረግ እና በመድሀኒት በመርዳት በቀላሉ ሊያበቃ ይችላል፡፡ ደረጃው ከፍ ካለ ግን ኦፕራሲዮን ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ መድሀኒት እና ጨረር መውሰድም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ህክምናው የሚወሰነው በበሽታው ደረጃ እና አይነት ይሆናል፡፡
ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ ብዙ ጊዜ የምናያቸው ችግሮች በማለት የጠቀሱት የታካሚዎችን ሁኔታ ነው፡፡ እናቶች ብዙውን ጊዜ ወደህክምናው የሚቀርቡት የወር አበባዬ ከተቋረጠ ከሁለት ወይንም ከሶስት አመት በሁዋላ እንደገና ተመልሶ በመምጣት ያስቸግረኛል በሚል ጊዜ ከፈጁ በሁዋላ ነው፡፡ እነሱ የሚያስቡት የወር አበባው ተመልሶ እንደመጣ እንጂ ከህመም ጋር መያያ ዙን አይደለም፡፡ ይህንን ገጠመኝ በእፍረት ይሁን ወይንም የራስ ገመና አድርጎ በመያዝ ለማ ንም የቤተሰብ አባል ሳይናገሩ ዝም ብለው ይቆያሉ፡፡ ባለቤቶቻቸው ወይንም ልጆቻቸው እንኩ ዋን አብረው እየኖሩ ነገር ግን ምንም ሳይሰሙና ሳያውቁ ጊዜ የሚፈጁ ብዙ ናቸው፡፡ እስከአሁን ድረስ የወር አበባዬ ከተቋረጠ በሁዋላ ተመልሶ ደም መፍሰስ ከጀመረኝ ሳምንት ሆነኝ ወይንም አንድ ወር ሆነኝ ብለው የሚመጡ ሴቶች በጭራሽ አያጋጥሙም፡፡ ይቆይ፣ መፍሰሱ ይቆማል፤ ይቋረጣል ፤ ቀድሞውኑም ጊዜው ሳይደርስ ተቋርጦ ነው የሚሉና የመሳሰሉትን የተሳሳቱ መላ ምቶች ለራሳቸው እየሰጡ ወደ ህክምናው ሳይቀርቡ የሚቆዩ ብዙ ናቸው፡፡ ህክምናው ቢደረግም አልፎ አልፎ ከእይታ ውጭ የሆነ ነገር መከሰቱ ያጋጥማል፡፡ የደም መፍሰሱን ምክን ያት አድ ርጎ የሚደረገው የም ርመራ ውጤት ምክንያቱ ከካንሰር ጋር የተያያዘ አይደለም በሚል ቀለል ያለ ህክምና ከተደረገ በሁዋላ የደም መፍሰሱ የማይቆምበት ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንት ጊዜ ከአሁን ቀደም ታክሜአለሁ ይበቃኛል ሳይሉ እንደገና ወደ ህክምናው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ባጠቃላይም የወር አበባ ከቆመ በሁዋላ እንደገና ደም መፍሰስ ከጀመረ ስድስት ወር ሆነው፤ አመት ሆነው፤ ሁለት አመት ሆነው እያሉ እርምጃ አለመውሰድ ቀናት በጨመሩ ቁጥር ለደም መፍሰሱ ምክንያት የሆነ ውን ህመም እድሜ እየጨመሩ እና እያባባሱ ወደ ከፋ ደረጃ እየገፉት መሆኑን መዘንጋት አይገ ባም በማለት ማብራሪያቸውን አጠናቀዋል ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔ ሻሊስትና የመራቢያ አካላት ካንሰር Oncology gynecology ሕክምና እስፔሻሊስት፡፡