Saturday, 30 November 2024 19:42

ጨቅላ…እንደተወለደ…ቀዶ ህክምና ሊደረግለት ይችላል፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

አንድ ቤተሰብ ልጅ ሲያፈራ ለተወሰኑ ወራት ህጻኑን እንደተሰባሪ እቃ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ህጻኑ እንዳይቀጭ፤ብርድ እንዳይመታው፤ትን እንዳይለው፤እንዳይታፈን የሚ ለው ጥንቃቄ ይደረግለታል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ይህ ገና ከማህጸን የወጣ ህጻን የአፈጣ ጠር ጉድለት ቢገጥመው 24/ሀያ አራት ሰአት ሳይሞላው ወደ ቀዶ ህክምና የሚገባበት አጋጣሚ አለ፡፡ ያ እንጭጭ ገላ እንዴት ስለትን ይችላል? የሰመ መን ወይንም የማደንዘዣውን ጉዳይ እንዴት ይወጣዋል ስንል ወደ ባለሙያ አመራን፡፡ ያነጋ ገርናት ዶ/ር ትሁት ተሾመ የህጻናት የሰመመን ወይንም የአንስቴዥያ ህክምና እስፔ ሻሊስት ናት፡፡ ዶ/ር ትሁትን ያገኘናት ኪዩር ከተሰኘ ሆስፒታል በስራ ላይ እያለች ነው፡፡ የሰጠችንን ማብራሪያ እነሆ ብለናል፡፡
ኪዩር የተሰኘው ሆስፒታል የሚገኘው ስድስት ኪሎን ወይንም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን አለፍ ብሎ ወደ ቀኝ በመታጠፍ የሚገኝ ነው፡፡ ኪዩር ሆስፒታል ህክምናውን የሚሰጠው በነጻ ነው፡፡ ህክምናው ብቻም ሳይሆን የታካሚውም ሆነ የአስታማሚው ምግብ ጨምር በነጻ ይቀርባል፡፡ ኪዩር ሆስፒታል የአጥንትና የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና ላይ የሚያተኩር ሆስፒታል ነው፡፡ በተለይም የተሰነጠቀ ከንፈር፤ላንቃ ያላቸው፤በቃጠሎ ምክንያት እጃቸው ወይንም እግራቸው የታጠፈ ወይንም የተጣመመ፤ በሚደርስባቸው ጉዳት ምክንያት ለመተንፈስ ወይንም አይና ቸውን ገልጠው ለማየት የማይችሉ ትን የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ የአጥንት ህክምና ያገኛሉ፡፡ ልጆች ሲወለዱ አጥንታቸው ተጣምሞ ወይንም ሌሎች የአካል ጉድለት ደርሶባቸው የሚወለዱ ከሆነ የህክምና እርዳታ ያገኛሉ፡፡ ጨቅላዎቹ ሲወለዱ የጀርባ አጥንት ክፍተት ወይንም መጣመም ካላቸው ሀያ አራት ሰአት ሳይሞላቸው ቀዶ ህክምናው ይደረጋል፡፡ በአጠቃላይም ጨቅላዎችም ሆኑ ህጻናት በአደጋም ይሁን በተፈጥሮ የሚደርስባቸውን የአካል አለመስተካከል እንደየሁኔታው ህክምና በማግኘት የሚስተካከሉበትን ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ነው፡፡ ኪዩር በአንድ አመት ከ ሶስት ሺህ እስከ ሶስት ሺህ አምስት መቶ (3000-3500) ለሚሆኑ ህክምና ይሰጣል፡፡ ይህን ህክምና የሚያገኙት ሁሉም ህጻናት ናቸው፡፡ ታካሚዎች ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ይመ ጣሉ ማለት ይቻላል፡፡
ዶ/ር ትሁት ለቃለምልልሱ ወደምትሰራበት ኪዩር ሆስፒል በሄድንበት ወቅት የኦፕራሲዮን ስራዋን እስክትጨርስ መጠበቅ ነበረብን፡፡ አንዳንድ ቀዶ ህክምናዎች በዘመቻ ስራ ስለሚካሄዱ ከበድ ያለ ስራ ነበራት፡፡ ቀዶ ህክምናው የፈጀው አምስት(5)ሰአት ነበር፡፡ ምናልባትም ከዚያ ወጥታ ለቃለምልልሱ ፈቃደኛ ትሆናለች ወይ የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ ነበር፡፡ እስዋ ግን ከኦፕራሲዮን ክፍሉ ስራዋን ጨርሳ ስትወጣ ልናነጋግራት ወደምንችልበት ክፍል ነበር የጋበ ዘችን፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ህብረተሰቡ ሆስፒታሉ እንደዚህ ያለ ከበድ ያለ የህክምና አገልግ ሎት ያውም በነጻ እንደሚያቀርብ በምን መንገድ ያውቃል ለሚለው ጥያቄ የሰጠችው ማብራሪያ የሚከተለው ነበር፡፡
‹‹….ሆስፒታሉ የአጥንት ህክምና ላይ ለሚሰማሩ ሐኪሞች ትምህርት ይሰጣል፡፡ እነዚያ ሐኪሞች በሚመደቡበት ቦታ የሚያውቁትን በመንገር ለምርመራ ህጻናቱን ይልካሉ፡፡ በጄሶ በቀላሉ የሚሰራውን ስራ ዘመቻ ሳያስፈልገው በቀላሉ የምንሰራ ሲሆን በዘመቻ በሚሰራበት ወቅት ግን የተለያዩ ሐኪሞች በተሟሉበት የሚሰራ ስራ ነው፡፡ ሰዎች ያዩትን ይመሰክራሉ፡፡ ሐኪሞች ወደሚያውቁት ህክምና ታካሚዎችን ያስተላልፋሉ፡፡ አሁን በተለይም በስፋት ታውቆአል ማለት ይቻላል፡፡ምክንያቱም ተመዝግበው ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ብዙ ናቸው፡፡…››
ገና ለተወለደ ልጅ ማደንዘዣ ሲሰጥ ሊሆን የሚችለውን ነገር ማሰብ ይከብዳል፡፡ ሐኪሞቹ ግን ይወጡታል፡፡ ዶ/ር ትሁት እንዳለችው….በዚህ እድሜ ላለ ልጅ እና ለአዋቂ ማደንዘዣ መስጠት በጣም የተለያየ ነገር ነው፡፡ ህጻኑ ማደንዘዣ ሲሰጠው የሚወስ ደው እያንዳንዱ መድሀኒት በክብደቱ እየተባዛ ነው መጠኑ የሚወሰነው፡፡ትልቅ ሰው ብርድ ቢሰማው ልብስ ይደርባል፡፡ ህጻናቱ ግን ሙቀታቸውን ማስተካከል አይችሉም፡፡ አዋቂ ሆኖ ብርድ ቢሰማው ሰውነቱ ይንቀ ጠቀጣል፡፡ ይህ የሚሆነው ሰውነት እራሱ ሙቀቱን ለመፍጠር በሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ህጻናቱ በተለይም ከዘጠኝ ወር በፊት የሚወለዱ ልጆች ይህን ማድረግ አይችሉም፡፡ ስለዚህ አንዱ በጣም የሚያስቸግረን ነገር ሙቀታቸው በጣም የሚወርድ መሆኑ ነው፡፡ ሙቀታቸው በሚወርድበት ጊዜ ከሰመመን ቶሎ አይነቁም፡፡ ልብ ምታቸው ከመቀነስ አልፎ እስከመቆምም ሊደርስ ይችላል፡፡ ስለዚህ ሙቀቱን ጠብቀን፣ማሞቂያ ውስጥ አድርገን ፤በሚሞቅ ልብስ ጠቅልለን በመሳሰለው ሁኔታ እንክብካቤ ተደርጎ ነው ስራው የሚሰ ራው፡፡ ሌላው ከዘጠኝ ወር በፊት የሚወለዱ ልጆች የሚያጋጥማቸው ችግር በሰውነታቸው ውስጥ ያለው ስኩዋራቸው ሊያልቅ ይችላል፡፡ ይህም ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል እንከታተላለን፡፡ የደም ግፊቸው በጣም ከፍ ዝቅ ይላል፡፡ የአዋቂዎች ደምግፊት መለኪያ በየ ቦታው ይገኛል፡፡ የእነዚህ ጨቅላ ዎች ግፊት መለኪያ ግን እንደልብ አይገኝም፡፡ በደማቸው ውስጥ ያለው የኦክስጂን መጠን በጣም አስፈላጊው ነገር ነው፡፡ ስለዚህ የህጻናቱ መለኪያ ባይኖር እንኩዋን የአዋቂ አንድ ጣት ላይ የሚደረገው መለኪያ ውስጥ የህጻናቱ ሁለት ወይንም ሶስት ጣቶች ተሰብስበው ይከተቱና ይለካል፡፡ በተቻለ መጠን ግን ለኦፕራሲዮኑ ሲዘጋጁ ለአዋቂ የሚደረገው ጥንቃቄ በሙሉ እንዲ ያውም በተሻለ ወይም በበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራ ላቸዋል፡፡ እነዚህን ህጻናት በተመለከተ በእኛ ሐገር ያለውን የህክምና አሰራር ከባድ የሚያደ ርገው ሁኔታ ለእነሱ ምርመራ የሚሆኑ መሳሪያዎች እና መድሀኒቶች እንደልብ አለመገኘ ታቸው ነው፡፡ በውጭው አለም በተለይም ባደጉት ሐገራት ሁሉም የምርመራ መሳሪያዎች በጨቅላዎቹ ወይንም በህጻናቱ ልክ ተሰርተው አገልግሎት ላይ ስለሚውሉ የበለጠ ቀለል ባለ መንገድ ስራውን መስራት ይቻላል፡፡ በእኛ ሐገር ግን ይህ ባለመሆኑ ስራውን ከባድ ያደር ገዋል፡፡ ቢሆንም ግን እየተወጣነው ነው ብላለች ዶ/ር ትሁት ተሸመ የሰመመን ህክምና እስ ፔሻሊስት፡፡
በአስተሳሰብ ደረጃ አንድ ስህተት አለ ብላለች ዶ/ር ትሁት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከዘጠኝ ወር በፊት የተወለዱት ለጆች ለኦፕራሲዮን ሲዘጋጁ እነሱ ምንም እንደማይሰማቸውና እንደማያውቁ ተደ ርጎ መወሰዳቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ወላጅ እራሱ መጨነቁን እንጂ ልጁ ህመሙን ያውቀዋል የሚል እሳቤ አያድርበትም፡፡ ግን ማወቅ ያለብን ህጻን ከዘጠኝ ወር በፊት ቢወለድም ከመወለዱ በፊት በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ እንደሚሰማ እና እንደሚያውቅ ነው፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ልጆች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት የበለጠ ትኩረትን የሚፈልጉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ከዘጠኝ ወር በፊትም ሆነ ዘጠኝ ወር ሞልቶአቸው ሲወለዱ ሊከሰት የሚችል የአካል ጉድለቶች ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ የጭንቅላት ትልቅ መሆን፤የጀርባ አጥንት ክፍት መሆን የመሳሰሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ጨቅላው በኦፕራሲዮን ካልሆነ በስተቀር አካሉ ሊስተካከል እንደማይችል ሲታወቅ ወደኦፕራሲዮን አገልግሎት የሚመጡት በሐኪሞች ትእዛዝ ነው ወይንስ ወላጅ እራሱ ፈቅዶ ይመጣል የሚለውን ጥያቁ ለዶ/ር ትሁት አንስተን ነበር፡፡ እንደሚከተለው ነበር ማብራሪያዋ፡፡
‹‹….ወላጅ በልጁ ለይ ለመወሰን በጣም ይቸገራል፡፡ ባህላዊ ህክምናን ማሰብም ይታያል፡፡ በዚህ እድሜው ቀዶ ህክምና መደረግ የለበትም የሚል ድምዳሜ የመስጠት ሁኔታም ይታያል፡፡ ስለዚህ ቤተሰብ በዚያ ሰአት ለመወሰን በጣም ስለሚቸገር ነግሮ ማሳመን የባለሙያው ስራ ነው፡፡ ወላጅ የማያውቀው ነገር ልጁን ኦፕራሲዮን በማድረግ ወቅት የሚሰጠውን ማደንዘዣ ነው፡፡ እንደምንም ልጃቸው ቀዶ ህክምና ቢደረግለት እንደሚስተካከል ካሳመንን በሁዋላ ባለሙያዎቹ ብዙ ነገሮችን ለማስተካከል ትግል አድርገን ነው ህክምናው የሚሰጠው፡፡ እኛን ይበልጥ የሚያሳስበን ልጁን ኦፕራሲዮን ለማድረግ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ የበለጠው ስራ እኛጋ ስላለ ልጁ ኦፕራሲዮን መደረግ አለበት የሚለውን ማሳመን ቀለል ያለ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ህጻኑ ሲወለድ የጀርባው አጥንት ክፍት ከሆነ በሀያ አራት ሰአት ውስጥ መሰራት አለበት፡፡ አለበለዚያ ኢንፌክሽን፤ማጅራት ገትር የመሳሰለውንና የከፋም ነገር ሊፈጠር እንደሚችል በግልጽ ነግሮ ማሳመን የእኛ ግዴት ነው ብላለች ዶ/ር ትሁት ተሸመ፡፡›› ለማጠቃለያም ዶ/ር ትሁት ተሸመ የሰመመን ህክምና እስፔሻሊስት ለወላጆች የሚከተለውን ምክር ሰጥረዋል፡፡
‹‹…ልጆች ለኦፕራሲዮን ሲቀርቡ በጤ ንነትም ይሁን በአመጋገብ ደረጃ የሚሰጣቸውን መመሪያ በትክክል እንዲተገብሩ እና የሚጠየቁትን ጥያቄ በትክክል እንዲመልሱ ነው፡፡ በግልጽ ካልተናገሩ ግን ልጃቸውን ለአደጋ ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ሊያውቁት ይገባል…››

Read 507 times