የቫዜክቶሚ ትውስታ በዚህ አምድ አዘጋጅ ምናልባት ከሀያ አምስት በላይ ይወስዳታል፡፡ ሴቶች በእርግዝና እና ብዙ በመውለድ ምክንያት ከተንገላቱ በሁዋላ ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ ያልተ ፈለገ እርግዝናን እንዲከላከሉ ለማስቻል የእንቁላል ማስተላለፊያቸውን መስር ለመቋጠር መለ ስተኛ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡ ነገር ግን በመውለድ ምክንያት የሚጎዱትን የት ዳር አጋሮቻቸውን ለማገዝ ፈቃደኛ የሆኑ ባሎች የራሳቸውን የዘር ፍሬ እንዲያስቋጥሩ የሚያ ስችል በጣም አነስተኛ የሚ ባል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ቢያደርጉ ጥሩ መሆኑ ይመከራል፡፡ ይህ ሳይንስ በጊዜው በስፋት ነበር የተዋወቀው፡፡ የመገናኛ ብዙሀንም ሲዘግቡት ነበር፡፡ ታዲያ ይህንን እና ከሴቶቹም ጋር በተገናኘ የተለያዩ የቤተሰብ እቅድ ዘዴዎችን በመስራት ላይ እያለን በወቅቱ ቤተሰብ መምሪያ ከሚባለው መስሪያ ቤት አንድ ባለሙያን አነጋገርን፡፡ ቃለ ምልልሱ እንደሚከ ተለው ነበር፡፡
ጥ/ ወንዶች የዘር ፍሬ የማስቋጠሩን ሂደት (ቫዜክቶሚ) እንዲያውቁ ምን እየተደረገ ነው?
ዶ/ ሴቶቹ ወደ ክሊኒኩ ሲመጡ የማስቋጠሩን ስራ በአንቺ ላይ ከምንሰራ ባለቤትሽን ብት ጠሪው ምን ይመስልሻል ስንላት እሺ እጠራዋለሁ ብላ ትሄዳለች፡፡ በሚቀጥለው ቀጠሮ ስትመጣ ግን ብቻዋን ነው የምትመጣው፡፡
ጥ/ ምክንያትዋ ምን ድነው?
መ/ መልስዋማ አንቺው ተቋጠሪ እንጂ እኔ ምንበወጣኝ እቋጠራለሁ ብሎኛል፡፡ እኔ በቃኝ ፡፡ ልጅ መውለድ አልፈልግም ስትለን እኛም በጥያቄዋ መሰረት አገልግሎቱን እንሰጣታለን የሚል ነበር መልሳቸው፡፡
ይህንን ጥያቄ ከአንድ አመት በሁዋላ እንደገና ይዘን ሄድን፡፡
ጥ/ በዚህ አንድ አመት ውስጥ ቫዜክቶሚን ለማስተዋወቅ በመገናኝ ብዙሀኑም ብዙ ሰርተናል፡፡እናንተም እንዲሁ ለአገልግሎቱ ፈላጊዎች ምክሩን ስትሰጡ ቆይታችሁዋል፡፡ ምን ለውጥ አለ?
መ/ ብዙም ባይሆንም ትንሽ ለውጥ አለ፡፡
ጥ/ ተጠቃሚ ወንዶች እየመጡ ነው?
መ/ አዎን ፡፡ እየመጡ ነው፡፡ በዚህ አንድ አመት ውስጥ ሁለት አባቶች መጥተው አገልግ ሎት ተሰጥቶአቸዋል፡፡
ጥ/ ሴቶች ባሎቻቸውን አምጥተው ነው ወይስ?
መ/ አ….አ….አይ አይደለም፡፡ እኛም ምክንያቱ አልገባንም፡፡ የሚል ነበር መልሱ፡፡
ለማንኛውም በአመቱ ውስጥ ተሰርቶላቸዋል የተባሉ ወንዶች ቁጥር ሁለት ይሁን እንጂ ከዚያ በሁዋላ ደግሞ ጭርሱንም የደበዘዘ እና በሶስት እና አራት አመትም የማይገኝበት ሁኔታ ነበር ሲስተዋል የነበረው፡፡ በአሁኑ ወቅት እንዲያውም ተረስቶአል የሚል መንፈስ ነው ያለው፡፡
ዘንድሮ እንደውጭው አቆጣጠር ኖቨምር 22/2024 በኢትዮጵያ የቫዜክቶሚ ቀን ተብሎ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለግማሽ ቀን ያህል በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች የተገና ኙበት አንድ ስብሰባ ተደርጎ ነበር፡፡ ስብሰባው የልምድ ልውውጥ የተደረገበት እና በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ ለመነጋገር ያስቻለ ነበር፡፡ በስብሰባው ላይ የእንኩዋን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር ድልአየሁ ነበሩ፡፡ ፕሮፌሰር እንደገለጹትም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን እንዲሁም በስነተዋልዶ ጤና በኩል ልጅ መውለድ ከመቻል እና ካለመቻል ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለሚፈልጉ እናቶች እንዲሁም ጥንዶች በስፋት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን እና ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት አሰጣጡም ከመጀመሪያዎቹ የሚመደብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቢሆንም ግን አሉ ፕሮፌሰር….ቢሆንም ግን በእስከዛሬው ስራ ችን ወደሁ ዋላ የቀረው የወንዶች በቤተሰብ እቅድ ዘዴው ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ አለማስቻላችን ነው፡፡ እሱም የቫዜክቶሚ አገልግሎትን ማሰተዋወቅና መኖሩንም ማሳወቅ በጭ ራሽ እየተሰራበት አይደለም ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡
በእለቱ የወንዶች የቤተሰብ እቅድ ተሳፎን ለማጎልበት መሰራት ስለሚገባው ቫዜክቶሚ ከራሳ ቸው ልምድ በመነሳት ማብራሪያ ካቀረቡት መካከል ዶ/ር አስቻለው ይገኙበታል፡፡
‹‹….የቤተሰብ እቅድ ዘዴው ገና ስራ ከመጀመሩ በፊት በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ለማስጀመር ትልቅ ችግር ነበር፡፡ በወቅቱ የቤተሰብ መምሪያ የሚባል መስሪያ ቤት ተቋቁሞ ስራውን ተግባ ራዊ ለማድረግ በልና ሚስቶች አብረው ወደ ክሊኒኩ በመምጣት ባልየው እንደሚከተለው ጥያቄ ያቀርብ ነበር፡፡ በቅድመሚያ አገልግሎቱን በኢትዮያ ውስጥ ለማስጀመር እምቢተኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ይታይ ነበር፡፡ ስለዚህ ባለሙያዎቹ በ1966ዓ/ም ወደ ጃንሆይ ቀረቡን ሁኔታውን አስ ረዱ፡፡ እሳ ቸውም ሲፈቅዱ…. ‹‹….ሳትንጫጩ ስሩ…›› ብለው ፈቀዱ፡፡ ስራው በተጀመረበት ወቅትም ወን ድየው ከፈቀደላት ከሚስቱ ጋር አብሮ በመቅረብ እኔ እከሌ የተባልኩ ሰው ባለቤቴ ወ/ሮ እገሊት የወሊድ መከላከያ እንድትወስድ ፈቅጄላታለሁ በማለት እንዲፈርም ከተደረገ በሁ ዋላ ሴትየዋ አገ ልግሎቱን ታገኛለች፡፡ ባልየው በዚህ መልክ ሳይፈቅድ አገልግሎቱን ካገኘች የህክምና ባለሙያ ዎቹ እስከመታሰር ይደርሱ ነበር፡፡ የወንዶቹ ቫዜክቶሚ ምንም ትእዛዝና መከላከል በሌለበት ነጻ በሆነው ጊዜ የተጀመረ ነው፡፡ ወንዶቹ ግን ለአገልግሎቱ ሲቀርቡ አይታ ዩም ብለዋል…››
እንደ ፕሮፌሰር ድልአየሁ ማብራሪያ ቫዜክቶሚ በተጠቃሚዎች ብቻም ሳይሆን በባለሙያዎ ችም ዘንድ የተረሳ ወይም የማይታወስ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ሙያውን እስፔሻላይዝ በሚያ ደር ጉበት ጊዜም ይሁን ስልጠና በሚሰጥበት ጊዜ ርእሰ ጉዳዩ የማይነሳ ከሆነ ሌላ እንዲያው ቁት የሚደረ ግበት መንገድ አይኖርም፡፡ ስለሆነም የቤተሰብ እቅድ ዘዴን አተገባበር በሚመለከት በሚሰጠው የምክር አገልግሎትም ጭርሱንም የሚረሳ በመሆኑ ለተገልጋዮች ባሎችም መከላከያ ውን በማድረግ ረገድ የሚሳተፉበት መንገድ አለ ብሎ የሚነገርበት አጋጣሚ የለም፡፡ ያልተፈለገ እርግዝና መከላ ከያው ሴቶች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፡፡ በእርግጥ ኮንዶም መጠቀምን፤መታቀብን የመሳሰሉት ምክ ሮች ይሰጣሉ፡፡ ይህ ቫዜክቶሚ ግን በተለይም ልጅ መውለድ በቃን ለሚሉ ዘለቄታዊ የሆነ የወን ዶች የመከላከያ መንገድ መሆኑን ባለሙያዎች ለተገልጋዮቻቸው አያማ ክሩም፡፡ ስለዚህ በጥቅሉ የምንለው ባሎች ይህ እድል መኖሩ ስላልተነገራቸው እየተጠቀሙበት አይደለም፡፡
በስብሰባው ላይ ሀሳባቸውን ከሰነዘሩት መካከል ዶ/ር ወንድሙ የጽንስና ማህጸን ሐኪም ይገኙ በታል፡፡ እሳቸውም እንዳሉት ….ብዙ ጊዜ በፈጣሪ ፈቃድ ትውልድን ማስቀጠል የተሰጠን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ነው፡፡ ይሄም ወንድና ሴት እኩል ኃላፊነት የተሰጣቸውና በተፈጥሮአቸው ዘርን መተካት የሚችሉበት ሁኔታ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ ከተ ለያዩ ሁኔታዎች አንጻር እንዲገደብ የሚፈለግበት ፤ቤተሰብ በጥሩ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያስ ችል አቅምን ለማጎልበት የሚቻልበት፤ ባጠቃላይ ነገሮች ተመቻችተው ልጆች የሚያድጉ በትን ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል የቤተሰብ እቅድ ዘዴ የሚባለው አሰራር አለ፡፡ ይህንን በመተግበሩ ረገድ ግን ሴትና ወንድ እኩል በሆነ መንገድ የሚተገብሩት ሳይሆን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ይሆ ናል፡፡ ስለዚህም ምን ያህል ልጅ ይወለድ ፤በየስንት ጊዜው ልጅ ይወለድ የሚለውን ለመወሰን ሁልጊዜም ኃላፊነቱ ሴቶች ላይ ብቻ ሲወድቅ ይስተዋላል፡፡ ይህ በተለይ ኢትዮ ጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች በስፋት የሚታይ ነው፡፡ አንዲት ሴት በመውለድ ምክን ያት ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል ወድቆባት መቆጣጠሪያውን መውሰድ ሳትችል የዘር ፍሬ ወደ ማስቋጠር አማራጭ የምትሔደው ምንም ችግር የሌለበት ጤነኛው ባለቤትዋ ከአጠገብዋ እያለ ነው፡፡
አለም አቀፉ የቫዜክቶሚ ቀን አላማው ሰዎች በጉዳዩ ላይ ሰፊ ግንዛቤ እንዲወስዱ ለማስቻል ነው፡፡ ስለዚህም ወንዶች በስነተዋልዶ ጤና እንዲሳተፉ ማድረግ ቀዳሚው ሲሆን እንዴት ለሚለው ደግሞ ቫዜክቶሚ አንዱ አማራጭ መሆኑ በስፋት መነገር አለበት፡፡
Saturday, 14 December 2024 12:19
Vasectomy - የቤተሰብ እቅድ ለወንዶች
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ