Saturday, 21 December 2024 20:28

መሬቱ እህል ፈራ፤መደቡ ሰው አፈራ…አሉ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

በኢትዮጵያ እንደውጭው አቆጣጠር ኖቨምበር 22/2024 የቫዜክቶሚ ቀን በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊ ኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተከብሮ መዋሉን ባለፈው እትም አስነብበናል፡፡ ለግማሽ ቀን በተካ ሄደው የልምድ ልውውጥ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ እንግዶች እንደነበሩና ሀሳብ መሰንዘሩንም በመጠኑ ለንባብ ማለታችን ይታወሳል፡፡ የወንዶችን የስነተዋልዶ ጤና ተሳትፎ ማጎልበት አስ ፈላጊ መሆኑ በተነገረበት በዚያ መድረክ በስተመጨረሻው የአምዱ አዘጋጅ አንድ ተሳታፊ አነ ጋግራ ለች፡፡ እንደሚከተለው ነበር መልሱ፡፡
‹‹……እኔ በበኩሌ ይህን ነገር ስሰማ የመጀመሪያዬ አይደለም፡፡ ባለቤቴ የዘር ፍሬዋን ለማስ ቋጠር ወደ ቤተሰብ መምሪያ ሄዳ ነበር፡፡ ባለቤትሽን ይዘሽው ነይ ፡፡ የምናማክራችሁ ነገር አለ ብለዋት ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ምን ተፈጠረ ብዬ ተከትዬ ሄድኩ፡፡ ከዚህ በሁዋላ ልጅ መውለድ በቃን ካላችሁ ዘላቂ መከላከያ መውሰድ ይጠቅማል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከእስዋ ይልቅ አንተ ስላልተ ጎዳህ የዘር ፍሬህን ብታስቋጠር ምን ይመስልሀል አሉኝ፡፡ እኔም …..አረ ምን በወጣኝ…..እስዋ ከፈለገች ታስቋጥር እንጂ እኔማ አልሞክረውም አልኩ፡፡ ለምን….ስባል እስዋ እድሜዋ ሲደርስ ለሚቋረጥ እርግዝና …..ምን አስቸኮለኝ እና ነው ገላዬን ኦፕራሲዮን የማስደርግ ብያቸው ተመ ለስኩ፡፡ ባለቤትህስ ምን አደረገች ….ቀጣዩ ጥያቁ ነበር፡፡ እስዋም ተወችው፡፡ በእርግጥ ከዛ በሁ ዋላ እስዋም እርግዝናውን ስለምትፈራ ….እንደገናም ….ለእኔም ማሰብ ነበረብህ በማለት ብዙም ሰላም አላገኘንም፡፡›› አለ፡፡
የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በአገራችን ተግባራዊ ሲደረግ ብዙ ችግር የታየበት ነበር፡፡ አገልግሎ ቱን ሲሰጡ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ለእስር የሚዳረጉበት ሁኔታም ነበር፡፡ ስራው በሚጀመ ርበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ልጅ እንዳይረገዝ ለማድረግ የባሎች ስምምነት ያስፈልግ ስለነበር ነው፡፡ ወንዶቹ ሳይፈቅዱ ሴቶቹ በራሳቸው ውሳኔ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል አይችሉም ነበር፡፡ ታዲያ መከላከያውን ስለማይጠቀሙ እርግዝናው በሚከሰት ጊዜ በተለያዬ ምግብና መጠ ጦች የተለያዩ መድሀኒቶችን እያቀላቀሉ በመውሰድ እንዲሁም እናውቃለን በሚሉ ሰዎች ጽን ስን በማቋረጥ ሂደት የብዙ ሴቶች ህይወት ያልፍ እንደነበር ምስክርነቶች አሉ፡፡
ይህንን የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ለማስጀመር አዳጋች የነበረውን መንገድ ለመወጣት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ1966 ዓ/ም ሲጠየቁ …..ሳትንጫጩ ስሩ ….ብለው እንደነበር አይዘ ነጋም፡፡ የቤተሰብ እቅድ አገልግ ሎትን ለማሳካት ወይንም ሴትዋ ጤንነትዋን ጠብቃ የወለደ ቻቸውን ልጆች በብ ቃት ለማሳደግ እንድትችል የተለያዩ መከላከያዎች ያሉ ሲሆን ለወንዶች ግን በተለይም እንደ እኛ ባሉ ሐገሮች ውስን ነው፡፡ ስለዚህ የወለድናቸው ልጆች ቁጥር ለእኛ አቅም በቂ ናቸው… ከዚህ በላይ ልጅ መውለድ አያስፈልገንም… በቃን… ብለው ለሚወስኑ የትዳር አጋሮች ለወንዱም የዘር ፍሬን ….ለሴ ትዋም የእንቁላል ማስተላለፊያውን መስመር ዘለቄ ታዊነት ባለው መንገድ ማስቋጠር ነው፡፡ ሆኖም ግን የማስቋጠር ሂደቱ ለወንዶቹም ለሴቶቹም የሚቻል ሆኖ እያለ በሴቶቹ ላይ ብቻ መወሰኑ ለምን ድነው የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ወንዶቹ ብዙውን ጊዜ መረጃ የሌላቸው እና የህክምና ባለሙያዎ ቹም እውቀቱ ስለሌላቸው በምክር አገልግሎቱ ወቅት አያነሱትም የሚል ነበር ከመድረክ የተ ገኘው መልስ ፡፡
ዶ/ር አስቻለው በእለቱ የተለያዩ ምስክርነቶችን አቅርበዋል፡፡
ቫዜክቶሚ ዘላቂ የሆነ የእርግዝና መከላከያ ሲሆን በሰለጠነ ባለሙያ፤ንጹህ በሆነ ቦታ የትም መሰራት የሚችል በጣም ትንሽ ጊዜ የሚወስድ የዘር ፍሬ የማስቋጠር የቀዶ ህክምና ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ አጀማመሩ ረዘም ላለ ጊዜ በእንስሳት ላይ ከተሞከረ በሁዋላ ወደቤተሰብ እቅድ ዘዴ ወይ ንም ወደሰዎች ሲመጣ የአእምሮ ችግር ያለበት፤አመጸኛ የሆነ ፤ወይም ደግሞ ከህብረተሰቡ አመለካከት ወጣ ያለ ሰው ዘሩ መቀጠል የለበትም ብለው ሲያም ቫዜክቶሚ እንዲ ሰራ ያደርጉ ነበር፡፡ በሁዋላ ግን ይህ የሰዎች መብት ስለሆነ በዚህ መቀጠል የለበትም ተብሎ በውጭው አቆጣጠር በ1971/ ዓ/ም ቫዜክቶሚ በቤተሰብ እቅድ አንዱ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከያ ተደርጎ እንዲወሰድ ሆነ፡፡ ቫዜክቶሚ በጣም ትንሽ ቀዶ ህክምና የሚፈልግ ሊነገር የማይችል የጎንዮሽ ጉዳት ያለው ነው፡፡ በ1974/ዓ/ም በቻይና ውስጥ ቀድሞ ከነበረው አሰራር ዘመናዊ በሆነ መንገድ መስራት እንደ ሚቻል የታየበት ነው፡፡ በቻይናና በህንድ መካከል ሂማ ሊያ ተራራ አካባቢ የምትገኝ ብዙም የማት ታወቅ አገር ወደ 40% የሚሆነው የመከላከያ ዘዴ ቫዜክቶሚ ነው፡፡ እንደነ አሜሪካ፤ ካናዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም እስከ 20 % ቫዜክቶሚ ተጠ ቃሚዎች ናቸው፡፡ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች 2.5 % ሲሆን ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ሲታይ 1%/ አይሞ ላም፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ከ1% በታች የሚል ሲሆን እንዲያውም በመቶኛ የማይቆጠር ወይም አገልግሎቱ የቀረ በሚል የሚገልጹም አሉ፡፡
የመጀመሪያው የቤተሰብ እቅድ ክሊኒክ በ1966 ዓ/ም የነበረው በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲ ካል ኮሌጅ ነበረ ብለዋል ዶ/ረ አስቻለው ፡፡ አሁንም የቫዜክቶሚ አገልግሎትን ለማስጀመር ሆስ ፒታሉ ትኩረት ሰጥቶ መን ቀሳቀሱ ያስደስታል፡፡ በ1966 ብዙ ሰዎች እየታሰሩ ነው ስራውን ሲሰሩ የነበረው፡፡ በ1980/ዓ/ም ጤና ጥበቃ ስራውን መስራት ሲጀምር ችግሩ ሁሉ በስፋት እየተ ቀረፈ ነጻ እየሆነ መጣ፡፡ በዚ ያን ጊዜ ወንዶች ከተቃውሞ ይልቅ እገዛ እንዲያደርጉ የሚያ ስችሉ ቅስቀሳዎችና አሰራሮች በስ ፋት ተዘረጉ፡፡ ዛሬ ደግሞ ከተቃውሞ ወደ ድጋፍ የሄደው ወንድ መከላከያውን በራሱ ላይ እንዲ ተገበር በማድረግ ሚስቱን ያግዛት የሚል ሀሳብ ነው በቫዜክቶሚ የሚገለጸው፡፡ ይህ አገልግ ሎት በአሁኑ ወቅት በህብረተሰብ ደረጃ እገዛ የሚደረግ ለት እና እውቅናም ያገኘ ነው፡፡ ስለዚህ መረጃውን ለማሰራጨት ምቹ ሁኔታዎች ያሉበት ወቅት ላይ ነው ያለነው፡፡ አንድ መረዳት ያለ ብን ነገር ቫዜክቶሚ በሰዎች ዘንድ ምን ያህል እውቅና አግኝቶአል ሲባል በአንድ ጥናት እንደ ተረጋገጠው ወደ አንድ አራተኛ የሚሆነው መልስ ሰጪ መረጃው እንዳለው የሚያሳይ ሲሆን ወደተግባሩ ሲኬድ ግን ከአንድ ከመቶ በታች…እንዲያውም በመቶኛ ሊቀመጣ የማይችል …የተ ዘነጋ ነው የሚል ምላሸ የሚሰጠው ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ዶ/ር አስቻለው እንደሚሉት ቫዜክቶሚ ጥቅም ላይ ያለመዋሉ ነገር ብዙ ጊዜ እንዲያውም በጠቅ ላላው ማለት በሚያስችል ሁኔታ የቤተሰብ እቅድ ፕሮጀክቶች በሚነደፍበት ጊዜ ወንዶችን ያካ ተተ አለመሆኑ እንደ አንድ ምክንያት ይቆጠራል፡፡ ወንዶች መረጃው በትክክል ከደረሳቸው ፈቃ ደኛ መሆናቸውን የሚያሳዩ ገጠመኞች አሉኝ በማለት እንደሚከተለው ገልጸዋል ዶ/ር አስቻለው፡፡
ደቡብ ምእራብ ዘጠኝ ሴቶች ዘላቂ የሆነውን መከላከያ ለማሰራት፤ወደ ሰላሳ የሚሆኑት ደግሞ የረዥም ጊዜ መከላከያን ለማሰራት የመጡ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል በአጋጣሚ ሁለቱ ሴቶች ባላቸው አብሮ መጥቶ ነበር፡፡ …ሁለቱም ሚስቶችህ ከሚሰሩ ይልቅ አንተ ብትሰራ ሁለቱም ማርገዝ አይችሉም….ለምን እንደዚህ አትወስንም ሲባል እኔ ብሰማ ኖሮ መች ይዣቸው እመጣ ነበር የሚል መልስ ነበር የሰጠው፡፡ ቫዜክቶሚ ተሰርቶለት ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
ሌላ ቦታ ለስራ ስሄድ አምስት ወንዶች ቁጭ ብለው ያወራሉ፡፡ ሁሉም ሚስቶቻቸውን ተከትው የመጡ ባሎች ናቸው ፡፡ እነዚህን ሚስቶቻቸውን ተከትለው የመጡ ባሎችን የምክር አገልግሎት ስንሰጣቸው ከአምስቱ አራቱ ቫዜክቶሚ በፈቃደኝነት አሰርተው ወደ ቤታቸው ሄዱ፡፡
ሌላው ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ ስራውን የሚሰሩ ሰዎችን ተመልከትልን ተብዬ በሄድኩበት ጊዜ ያጋጠመኝ ነው፡፡ በአጋጣሚ ከአምስቱ ሴቶች የአራቱ ባሎች ከሚስቶቻቸው ጋር አብረው መጥተው ነበር፡፡ ከዚያም አንዱን አጠገቡ ቁጭ ብዬ የምክር አገልግሎት ስሰጠው…. እንዴ ይሄ እኮ እኛ ባለንበት አይነገርም፡፡ ምንም አናውቅም፡፡እንደዚህ መሆኑን ባውቅ እስከዛሬ አንቆ ይም ነበር ነው ያለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ ወንዶች ቫዜክቶሚ አሰርተው ሚስቶቻቸ ው ሳይነኩ በሰላም ወደቤታቸው ሄደዋል፡፡
ሌላ የማልረሳው ነገር በቀድሞ ጊዜ የፓርላማ አባል የነበሩ ትልቅ ሰው ቫዜክ ቶሚ ካሰሩ በሁዋላ የነገሩኝ ነው፡፡ ‹‹ ….እኔ ከባ ለቤቴ ጋር ከተገናኘሁ ሶስት አመት ሆኖኝ ነበር አሉኝ፡፡ ለምንድነው ስላቸው…..መሬቱ እህል ፈራ ….መደቡ ሰው አፈራ የሚል ነበር አገላለጻቸው፡፡ ትርጉዋሜውም እኔ ዝም ብዬ ከባለቤቴ ጋር ብገ ናኝ በበቂ ሁኔታ አብልተን አጠጥተን የማናሳድገውን ልጅ ነበር የምንወልደው፡፡ አሁን እንግዲህ ነጻ ነን ነበር ያሉኝ፡፡ እኝህ ሰው እንዲያውም ሌሎች ወንዶችን በገበያ ቦታ ሁሉ ይመ ክሩ ነበር፡፡
ወንዶች የምክር አገልግሎቱ ከተሰጣቸው ለእርምጃቸው ወደ ሁዋላ እንደማይሉ ብዙ ማሳያዎ ችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ባለሙያዎች የምክር አገልግሎቱን ለሴቶቹ ብቻ ሳይሆን ለወን ዶችም እንዲሰጡና በሙያውም በተገቢው እንዲሰለጥኑ አምነውበት እንዲሰሩም ያስፈል ጋል ነበር ያሉት ዶ/ር አስቻለው፡፡

Read 422 times