ከዚህ ሥር በአጭሩ ስለ አሁናዊ ሁኔታችን የተሰማኝን አወጋለሁ…
…ከምንኖረው ይልቅ የምንሰማው የሚያሳስበን ሕዝቦች ሆነናል፤ ከላመው፣ ከጣመው፣ ካጣጣምነው፣ ከቀመስነው በላይ የተነገረንን አስቀድመን እናስሰልፋለን፤ በአመክኒዮ የትምህርት ዘርፍ ‹‹The problem of proof›› ይሉት ጉዳይ አለ፤ ትክክል መሆንን የማረጋገጥ ክፍተት እንበለው መሰለኝ፤ መድረሻችን፣ ወይም ድምዳሜያችን መነሻን መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት የሚተነትን ሲሆን፣ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ሁነኛ፣ ወይም ትክክለኛ መነሻ ሊኖረን እንደሚገባ ያትታል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሐይማኖቶች (በርካቶቹ) ከመጡ/ከተዋወቁ ረጅም ጊዜን አስቆጥረዋል፤ ሕዝቡም በተለያዩ ሐይማኖቶች ሥር ተቻችሎ ረጅም ዓመታትን ኖሯል፤ ብሔርም ቢሆን የቆየ ጉዳይ ነው፤ ነገር ግን አልፎ፣ አልፎ በተወሰኑ ግለሰቦች ዘንድ በሐይማኖትና በብሔር ጎራ ከፍሎ መናቸፍ አለ፤ ሐይማኖት የሚያጣላን፣ ብሔር የሚያናክሰን ከሆነ፣ ‹እስከዛሬ ለምን ሳያናክስ ቆየ?› ብሎ መጠየቅ የሕዝቡ ጉዳይ ነው፤ እስከዛሬ በሠላም የኖርን ሰዎች ደርሰን የምንጣላ ከሆነ፣ ሐይማኖት ወይም ብሔር ሳይሆኑ ጥፋተኞቹ እኛው ነን።
ይኼን ሁሉ ዘመን ኖረን፣ ኖረን አሁን ላይ የምንናቸፍበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም በማለት መለስ ብሎ የኖርነውን ዘመን ማሰብ መልካም ነው፤ ስህተቶቹ ሕዝቦች ነን፤ በሶስዮሎጂ መስክ ደግሞ ‹‹Noble Lies›› የሚባል ነገር አለ፤ ዋሽቶ ማስታረቅ ዓይነት ጉዳይ ነው፤ ዋሽቼ ላስታርቃችሁ አይደለም፤ ሕጸጻችሁን አምናችሁ መነቃቅራችሁ እንድትጥሉት ለመናገር ያህል ነው። ከመስማት መኖር፣ ከመቅዳት ማጣጣም ይቀድማሉና ኑሯችሁን እመኑ።
ኑሯችንን ስለማናምን ጠንካራ ሐይማኖተኛ፣ ጠንካራ ዜጋ፣ ተቆርቋሪ ትውልድ ከማፍራት አፈግፍገናል፤ ስለ ሀገሩ የሚጮኽ እንጂ ስለ ሀገሩ የሚተጋ ማግኘት ዘበት እየሆነ መጥቷል፤ ሰሚዎች፣ ጢያራ ጋላቢዎች፣ አጉል ተስፈኞች፣ ተነጂዎች ስለሆንን እውንና ሕልማችን ተባርዘዋል፤ ጠንካራ ሕዝብና መንግሥት እንዳይኖረን ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ይኼው አመላችን ነው።
ሕዝብን የሚቀርጸው ሕዝብ ነው፤ መንግሥትንም ቢሆን በአብዛኛው የሚቀርጸው ሕዝብ ነው፤ ሕዝቡ መንግሥትን ሥራህን ሥራ ሊለው ይገባል፤ መንግሥትን ሊመከርና ሊዘክር ይጠበቃል፤ መንግሥትን መደገፍ አንድ ነገር ነው፤ ለሀገር ዋስትና ሀገርን የሚያስቀድም መንግሥት ሊደገፍ ይገባል፤ ነገር ግን በእኛ ዘመን መንግሥትን ማበረታታት፣ መደገፍ፣ ከጎኑ መሆን… ሳይሆን እየተደረገ ያለው የመንግሥት አክቲቪስት የመሆን ዳርዳርታ ነው።
ቢቻል መንግሥትን ደግፎ፣ መንግሥትን አበርትቶ ለሕዝብ ነው አክቲቪስት መሆን የሚገባው፤ የሕዝባዊ ግዴታን መወጣት፣ መብትና ግዴታን አውቆ በሕግና ሥርዐት መተዳደር፣ ልማትን በንቃት መተግበር… መንግሥትን ከመደገፍ የሚመደቡ እና የዜግነት ግዴታ ተብለው ከሚታሰቡ ጉዳዮች መካከል ዋንኞቹ ናቸው፤ ነገር ግን ለመንግሥት ማጎብደድ፣ ለሕዝቡ ጠብ የማይል ሥራን እየሠራ ሕዝቡን የሚያንገሸግሸውን መንግሥት ሙጥኝ ማለት የአመክኒዮ ክፍተት ነው።
አሁን፣ አሁን ላይ አብዛኛው ሕዝብ በአንቂ ንግግሮች፣ በተራ ተስፋ ሰጪ ወሬዎች፣ ሐሳዊ በሆኑ አብቂ አባባሎች ታጅሎ ኑሮውን በመግፋት ላይ እንዳለ መገመት ከባድ አይደለም፤ በሚሰማው የተቀነባበረ አንቂ ንግግር ነገውን ይጠባበቃል፤ አንገሽጋሽ ኑሮው የሚነግረውን ከማመን ባለፈ የመንግሥትንና የሚዲያዎችን ተረታ፣ ተረት እየቀረደደ ይባትላል።
ማነው መባተል ዕጣ-ፈንታችሁ ነው ያለን? ማነው ጢያራ ስትጋልቡ፣ ነፋስ ስትከተሉ ከርማችሁ ኑ ያለን? በውል መንገዋለልና መንከራተት ምንድር ነው? መንግሥትም ቢሆን የተያያዘው ጉዳይ የማንቃት ሥነ-ዘዴውን ነው፤ ‹‹motivational speech›› መሳይ ነገሮች፣ ነገር ግን ከሥሌት ይልቅ ሥሜት የበዛባቸው ሥራዎችና ድርጊቶች አጥለቅልቀውናል…
…ይኼ የአንቂ ነገር ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል፤ መንግሥት የሀገር ማልማትና የነገን መንገድ ጥርጊያ ድርጊቱን ቸል ብሎ አንቂ ሆኖ አርፏል፤ አንቂዎች በነቂው ላይ ምቹ ሥሜትን፣ ተነሳሽነትን መፍጠር እንጂ ማጃጃል ሥራቸው አይደለም። ነቂ በአጉል ብጽዕና ታጅሎ ዛሬን ሳይኖር ነገን መጠባበቅ የለበትም። የተያያዝነው ጉዳይ ሐይማኖት አይደለምና መሬት ባለ ነገር እንጅ በተሰፈረ የአንቂ ንግግር ብቻ መወሰን ያለበት አይመስለኝም።
በበኩሌ፣ መሬት ባልረገጠ መናኛ ተስፋ አላምንም፤ በተነገረኝ ሳይሆን በኖርኩበት ልክ ነገሮችን ልመዝን እገደዳለሁ፤ እውነት የስብከት ውጤት ብቻ አይደለም፤ እውነት የሚነገረን መሸንገያ ሳይሆን፣ የምንኖረው ኑሮ ነው፤ በዚህ ዘመን ጥጋብ ረሃባችንን፣ ጥማት ቁርጥማታችንን፣ መውደቅ መነሳታችንን…መንግሥት ነው የሚነግረን፤ የምንኖረው እኛ፤ የሚነግረን ሌላ ከሆነ መጣረስ ተከትሏል ማለት ነው፤ መድኀኒት መግዣ ተወዶብኝ የምንገላታውን እኔ ነኝ የማውቀው እንጂ አድገሃል ስለተባልኩ አዎ የምልበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኑሮዬን፣ መንገፍገፌን እኔው አውቀዋለሁና ለእኔው ተውልኝ…
ጉዳዩ የእኛው ክፍተት እንደሆነም ጭምር አድርገን መውሰድ ብልሃት ነው፤ ሕዝብ ተብለን እስከተጠራን እምነትና ተስፋችንን በመልክ፣ በመልኩ ማድረግ አለብን፤ መረጃዎችን ማጥራት፤ ምንጮችን መገምገም ግዴታ ነው፤ ለነገሩ ከመኖር በላይ ምን እውነት አለ? የኖርነውን ለመገምገም ምን አደከመን? መገምገም የቤት ሥራችን ይሁን፤ የማይገመግም ማኅበረሰብ የማሰላሰል ክፍተት እንዳለበት ይገመታል፤ ነገሮችን በቁም በውርዳቸው መሰልቀጥ መዘዙ ብዙ ነውና፣ ቆም ብሎ ማጤን ተገቢ ነው።

Published in
ነፃ አስተያየት