Tuesday, 14 January 2025 20:56

እግር ኳስን ከባዶ እግሩ ከመጫወት እስከ አውሮፓ ክለቦች የተጓዘው ሴኔጋላዊው “ኔይማር”

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
የእግር ኳስ ክህሎቱን የተመለከቱ ሴኔጋላዊው ”ኔይማር” ብለው ይጠሩታል፡፡ከህፃንነቱ እስከ 16 ዓመቱ ድረስ ኳስን በጫማ ሳይሆን በባዶ እግር ተጫውቷል፡፡ ፍጥነቱ እንደ አቦ ሸመኔ በመሆኑና በሚመታቸው ጠንካራ ኳሶች በርካቶች ከዲዲየር ድርጎባ ጋርም ያመሳስሉታል፡፡ የ23 ዓመቱ ተስፈኛ ሴኔጋላዊ የቼልሲ የፊት መስመር ተጫዋች ኒኮላስ ጃክሰን፡፡
በአውሮፓ ሊጎች ድንቅ የእግር ኳስ ችሎታ ካላቸው ወጣት አፍሪካውያን ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ኒኮላስ ጃክሰን የተወለደው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ መዲና ባንጁል ውስጥ ነው፡፡ እናቱ ሴኔጋላዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ ጋምቢያዊ ነው፡፡ለእግር ኳስ ያለው ጥልቅ ፍላጎት ትምህርቱን አቋርጦ ቤተሰቡን ጥሎ ወደ ስፔን እንዲሰደድ አድርጎታል፡፡
የሴኔጋል የኳሳ ስፖርት አካዳሚን ከመቀላቀሉ በፊት በደቡባዊ ሴኔጋል ለኤ.ኤስ.ሲ እግር ኳስ ቡድን ተጫውቷል፡፡ በክለቡ ተቀይሮ በመግባት በ15 ደቂቃዎች ባሰየው ድንቅ ብቃት ሰኔጋላዊው “ኔይማር” የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶታል፡፡ የእግር ኳስ ተምሳሌቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ መሆኑን የሚናገረው ኒኮላስ ጃክሰን ወደ ፊት ብዙ ታሪክ የመስራት ህልም እንዳለው ይናገራል፡፡
Read 470 times