አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ሲቪያ በተደረገው የማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡
አትሌት ሰለሞን የማራቶን ውድድር ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን፤ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባትም ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡
በሌላ በኩል በሲቪያ በተደረገው የሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት አንችንአሉ ደሴ አሸንፋለች።
አትሌት አንችንአሉ ደሴ ርቀቱን 2፡22፡17 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቋን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
Sunday, 23 February 2025 00:00
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገዉ የማራቶን ዉድድር አሸነፈ
Written by Administrator
Published in
ስፖርት አድማስ