Sunday, 02 March 2025 20:56

ዛሬ ለሊት ለ18ኛ ጊዜ በተደረገ የቶከዮ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል።

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በወንዶች ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በበላይነት አሸንፋለች።

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች።

በወንዶች የቶክዮ ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰአቱን በማሻሻል ጭምር አሸንፏል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ደረሳ ገለታ በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

Read 258 times