Friday, 01 August 2025 16:25

የፑቲን አስፈሪ መግለጫ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የመጀመሪያው መጠነ ሰፊ የዖሪሺኒክ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ስርዓት ምርት መጠናቀቁን አስታወቁ።
የመጀመሪያውን መጠነ ሰፊ ምርት ሂደት ያለፈውና የተመረተው ዖሪሺኒክ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ስርዓት፤ በሩሲያ ጦር ወደ ስራ መግባቱን ፑቲን ይፋ አድርገዋል። ለምዕራቡ ዓለም አስደንጋጩ መረጃ መሆኑ አይቀርም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት አገራቸው በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው፡፡
ሩሲያ ባለፈው ህዳር ወር በዩክሬንዋ ከተማ ኒፕሮ ላይ ዖሪሺኒክን በሞከረችበት ወቅት የፍንዳታው ቃጠሎ ለሦስት ሰዓታት ያህል መቆየቱ ይታወሳል። የሚሳዔል ስርዓቱ ኑክሌር አረር ጫፍ መሽከም የሚችል እንደሆነም ይታመናል።
ቀደም ሲል ፑቲን ሚሳዔሉ በመደበኛ የጦር መሳሪያነት አቅሙ ከዝቅተኛ የኑክሌር ፍንዳታ ጋር የሚስተካከል ውድመት ያስከትላል በሚልም አረጋግጠው ነበር።
NBC
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 6915 times