Saturday, 02 August 2025 08:37

ካፍ አዲስ ያሰራውን ዋንጫ አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
• የቻን አፍሪካ ዋንጫ ነገ በይፋ ይጀመራል
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ካፍ አዲሱን የቻን አፍሪካ ዋንጫ ይፋ አድርጓል፡፡
ለ8ኛ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በጣምራ የሚዘጋጀው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ካፍ አዲስ ያሰራውን ዋንጫ አስተዋውቋል፡፡
ነገ የሚጀመረው የቻን መድረክ በኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ በጣምራ የሚዘጋጅ ሲሆን፤ አዲሱን ዋንጫም ኡጋንዳዊው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦንያንጎ፣ ኬንያዊው የቀድሞው የቶተንሀም ሆትስፐር አማካይ ቪክቶር ዋኒያማ፣ እና ታንዛንያዊው መሪሾ ነጋሳ እንዳስተዋወቁት ኢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
በሀገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚገኙ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ ነገ በይፋ የሚጀመር ሲሆን፤ለ29 ቀን በሚቆየው ውድድር 19 ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚሳተፉበት ዘገባው አመልክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 469 times