"ፕሬዚዳንቱ ለሰላም ላደረጉት ታላቅ ጥረት እውቅና እንሰጣለን"
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካምቦዲያ ከታይላንድ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት ለማስቆምና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንድትደርስ መርዳታቸውን ተከትሎ፣ አገሪቱ ለኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት እንደምታቀርባቸው ገልጻለች፡፡
የካምቦዲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሱን ቻንቶል ባለፈው አርብ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ትራምፕ በቀጠናው ሰላም በማምጣታቸው አመስግነዋል።
ቻንቶል፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ለኖቤል የሰላም ሽልማት ሊታጩ ይገባቸዋል ሲሉም ተናግረዋል፤ በመግለጫቸው፡፡
"ፕሬዚዳንቱ ለሰላም ላደረጉት ታላቅ ጥረት እውቅና እንሰጣለን" ብለዋል፤ የካምቦዲያው ምክትል ጠ/ሚኒስትር፡፡
ባለፈው ወር የእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለኖቤልየሰላም ሽልማት ማጨታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ የፓኪስታን ባለሥልጣናትም በሸኔር ላይ አገራቸው ከህንድ ጋር የነበራትን ግጭት ለማስቆም ለተጫወቱት ሚና ትራምፕን ለኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት እንደሚያቀርቡ መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
እውን ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት ያገኙ ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል፡፡



