ፍልስጤማዊቷ የቁንጅና ንግሥት ናዲን አዩብ ሀገሯ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ በምትሆንበት የወይዘሪት ዩኒቭርስ (Miss Univers) የቁንጅና ውድድር እንደምትሳተፍ ተሰምቷል።
የ27 ዓመቷ ወጣት ናዲን አዩብ ሀገሯን ወክላ ታይላንድ በሚደረገው የዓለም ወይዛዝርት ውድደር ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ናቸው የተናገሩት።
ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ልቦናን ያጠናችው ናዲን አዩብ፤ በ2022 የወይዘሪት ፍልስጤምን የቁንጅና ዘውድ መድፋቷ ይታወቃል።
በፍልስጤማዊያን ዘንድ ተስፋ የተጣለባት ናዲን፤ በኅዳር ወር 2025 በታይላንድ ፓክ ከሬት ከተማ ከዓለም ዙሪያ ከተወጣጡ ቆነጃጅት ጋር እንደምትወዳደር ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

