Monday, 15 September 2025 08:28

የቀድሞ የግብጽ ወታደራዊ አዛዥ እስራኤልን አስጠነቀቁ

Written by 
Rate this item
(4 votes)
"የእስራኤል ጄቶች ግብፅን ቢያጠቁ መመለሻ አያገኙም"
የቀድሞ የግብጽ ወታደራዊ አዛዥ ኮሎኔል ሃተም ሳበር፣ የእስራኤል አውሮፕላኖች በግብፅ ላይ ጥቃት ቢሰነዝሩ "መመለሻ ቦታ እንደማያገኙ" በቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለመጠይቅ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
"የእስራኤል አየር ሃይል ግብፅን ቢያጠቃ፣ ከእስራኤል ለጥቃት የሚነሱ አውሮፕላኖች የሚመለሱበት መንገድ አያገኙም" ሲሉ ሳበር አስጠንቅቀዋል፡፡
አዛዡ ይህን የተናገሩት በቅርቡ እስራኤል በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ከፍተኛ የሃማስ መሪዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ ነው።
በአንድ ወቅት በግብፅ ጦር ውስጥ ካሉት ልዩ የፀረ-ሽብር ክፍሎች አንዱን የመሩት ሳበር፤ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ባይሰጡም፣ መልዕክታቸው ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀጥተኛ እንደነበር ዴይሊ ኒውስ ኢጂፕት ዘግቧል፡፡
ተንታኞች፤ የአዛዡ ማስጠንቀቂያ የእስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከተለመደው አድማስ እየተስፋፋ መምጣቱ፣ ካይሮ ላይ የፈጠረውን ሰፊ ስጋት እንደሚያንጸባርቅ ጠቁመዋል፡፡
የግብፅ መንግስትና ወታደራዊ ሃይሎች ለሳበር የቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ አዘል አስተያየቶች እስካሁን ምላሽ አልሰጡም ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 6788 times