የውሃ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ፣ ሰሞኑን በሱዳን የተከሠተው ጎርፍ ከሕዳሴ ግድብ ጋር የተያያዘ አይደለም ማለታቸውን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፣ አንዳንድ የግብጽ የውሃ ባለሙያዎች፣ የሱዳኑን ጎርፍ በሕዳሴ ግድብ ምክንያት የተከሠተ መኾኑን መግለጣቸውን ተከትሎ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል።
ጎርፉ የኋይት ናይል ወንዝ ሙላት የፈጠረው ሊሆን ይችላል ያሉት አቶ ሐብታሙ፣ ግድቡ ባይኖር የጎርፍ አደጋው እጅግ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል ተብሏል።
ግድቡ እንዲያውም ጎርፉ ከፍተኛ ውድመት እንዳያደርስ በመከላከል ረገድ ቁልፍ አስተዋጽዖ ማድረጉን ሚኒስትሩ መግለጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከግድቡ ትርፍ ውሃ አለመልቀቋንም ተናግረዋል ተብሏል።
ዋዜማ-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና

