ኢትዮጵያ ምርቶቿን ከቀረጥ ነጻ በሆነ ሥርዓት ወደ አፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አባል ሀገራት መላክ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፤ መስከረም 29 ኢትዮጵያ አህጉራዊ ነፃ የሸቀጦች ንግድ ትግበራን በይፋ ታስጀምራለች ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አባል ሀገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ምርቷን ከቀረጥ ነፃ መላክ ትጀምራለች ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የንግድ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር ተናግረዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ፣ ከንግድ ቀጠናነት ባሻገር የአፍሪካ ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

