Wednesday, 01 October 2025 12:42

ህወሓት የፕሪቶሪያው ስምምነት አፈራራሚዎችን ከሰሰ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ዋስትና ሰጪ የሆኑት አሜሪካ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ አፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ሳያደርጉ ቀርተዋል ሲል ከሰሰ።
ፓርቲው ስምምነቱ ከተፈረመ ከሦስት ዓመታት በኋላም ቢሆን፣ በትግራይ ክልል “በዝምታ ውስጥ እየተፈጸመ ያለ ዘር ማጥፋት ቀጥሏል” ሲልም ገልጿል።
ህወሓት መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን ውድመት ለማስቆም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ አሳስቧል። አክሎም፣ “ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁን እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን። የትግራይ ውድመት በዝምታ እንዲቀጥል አትፍቀዱ። ለሰላም የገባችሁትን ቃል አክብሩ፣ ንጹሐንን ጠብቁ፣ እናም ሌላ አሳዛኝ ክስተት እንዳይከሰት ተከላከሉ” ብሏል።
ፓርቲው፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና የተያዙ ቦታዎች እንዲለቀቁ ለማስቻል በህዳር 2022 የተፈረመው የፕሪቶሪያው ስምምነት በአብዛኛው ሳይተገበር ቀርቷል ብሏል። መግለጫው፣ “አብዛኞቹ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ አልተደረጉም፤ተፈናቃዮች ሳይመለሱ ቀርተዋል፣ የተያዙ ቦታዎችም አልተለቀቁም። አደጋው እየከፋ ሄዶ በዝምታ ውስጥ እየተፈጸመ ያለ ዘር ማጥፋት ቀጥሏል” ሲል አክሏል።
በተጨማሪም ፓርቲው፣ ዋስትና ሰጪዎቹ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለመቻላቸውንም በማውገዝ፤ “የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር፣ ኃይሎች ከያዙት ቦታዎች አስቸኳይ ለቀው እንዲወጡና ተፈናቃዮች በሰላም እንዲመለሱ” ጠይቋል።
አስ-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of text
 
 
 
 
Read 1241 times