አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን ጸጉር ማስቆረጥ ጀምሯል አሉ፡፡ እኔ መጀመሪያ ስሰማ የምር አልመሰለኝም ነበር፡፡ አሁን እንደሚታየው ግን ጭራሽ ህግ የወጣለትም ጉዳይ ነው፡፡
"ዩኒቨርሲቲ" ተብለው እንዲህ አይነት ሀሳብ ከየት እንደመጣላቸው ራሱ አላውቅም፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ማስተካከል የሚገባው በጣም ብዙ ጉዳይ እያለ ከዚህ ለምን መጀመር እንደፈለገም አልገባኝም፡፡ ዞሮ ዞሮ እንዲህ አይነት ሀሳብ መነሻው ህዝበኝነት (populism) ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡
ተራ ጭብጨባ የመቃረም አባዜ ያመጣው ሀሳብ እንደሆነ እጠረጥራለሁ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ከፍተኛ የትምህርት ተቋም" ነው፡፡ ስለዚህም ማተኮር ያለበት ስለ ጸጉር ርዝማኔ ሳይሆን ከጸጉር በታች ያለው ጭንቅላት ስለሚያፈልቀው ሀሳብ ብቻ ነው፡፡ዩኒቨርሲቲው በአብዛኛው በሀያዎቹ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን እንደማስተማሩ አንዳንድ ነገሮችን ለእድሜና ለተፈጥሮ መተው አለበት፡፡ ጸጉራችንን ተቆርጠን ስንመጣ "ጨዋ" የሚል ሙገሳ ሊሰጡን የሚገባው ወላጆቻችን እንጂ ዩኒቨርሲቲው አይደለም፡፡
ህዝበኝነት ይጥፋ!
(Ab Bella-)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

