በቼክ ሪፐብሊክ ለእይታ ቀርበው የነበሩት ሉሲና ሰላም ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡
ሁለቱ ቅሪተ አካላት በፕራግ ሙዚየም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው፣ ዛሬ ንጋት ላይ አዲስ አበባ መግባታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሁለቱ ቅርሶች ከነሐሴ 10 ቀን 2017 እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2018 በነበራቸው ቆይታ ከመላው አውሮፓ በጎረፉ ቱሪስቶች እንደተጎበኙና የኢትየጵያን የሰው ዘር መገኛነት በዓለም አደባባይ ማስተዋወቃቸውን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

