የዝነኛው አቀንቃኝ ዘ ዊክንድ (አቤል ተስፋዬ)፣ የተጣራ የሀብት መጠን በአራት ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ አድጎ 600 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተዘገበ፡፡
ሰለብሪቲ ኔት ዎርዝ ድረ-ገጽ እንደገለጸው፤ የዚህ ዓለማቀፍ ድምጻዊ አጠቃላይ ሀብት እ.ኤ.አ. በ2021 ከነበረበት 200 ሚሊዮን ዶላር በአራት ዓመታት ወደ 600 ሚሊዮን ዶላር አሻቅቧል - የ400 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ በማሳየት፡፡
የድምጻዊው "Blinding Lights"ን የመሳሰሉ ተወዳጅ ሥራዎቹ በበይነመረብ የሙዚቃ ማሰራጫ መድረኮች በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጊዜያት መደመጣቸው ለገቢው መጨመር የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው የተነገረ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ. በ2024 ከስፖቲፋይ ብቻ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ዝነኛው አቀንቃኝ ከአዳዲስ፣ ፑማና ሌሎች ታላላቅ ኩባንያዎች ጋር ባለው የሥራ ውል ከፍተኛ ገቢ እንደሚያገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ዘ ዊክንድ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በስፋት እንደሚሳተፍም ይታወቃል፡፡

