Sunday, 02 November 2025 06:26

ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበባዊ ወግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት 10ኛውን የወር ወንበር በድምቀት አከናወነ።
በአስረኛው የወር ወንበር
"ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበባዊ ወግ"
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ማህበራዊ፣ፍልስፍናዊ፣ታሪካዊ፣ጥበባ
ዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ጥልቅ ውይይት እና የሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት የወር ወንበር አስረኛ መርሐግብሩን ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በተቋሙ ብላታ መርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ አዳራሽ አከናውኗል።
የወሩ ወንበር "ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበብ ወግ" በሚል ርዕስ ሲሆን የውውይት መነሻ ሀሳብ
ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ ፈለገ ሰላም የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ዲን ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ ናቸው።
የአደባባይ ሐውልቶቻችን አሠራራቸው፣በታሪክ ውስጥ ያለፉበት መንገድ፣የታለመላቸውን ሀሳብ ዓላማ
የማስተላለፍ አቅማቸው፣ የተሰሩበት ዓላማ፣የፈረሱ ሐውልቶች፣በአደባባይ በቆሙ ሐውልቶቻችን ላይ የተነሱ ጉዳዮች እና ስለሐውልቶቹ ምን ተባለ የሚሉትን ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ በገለጻቸው ከዳሰሷቸው ነጥቦች የሚጠቀሱ ናቸው።
የዕለቱ ታዳሚያን ንቁ ተሳትፎ ጎልቶ በወጣበት የወር ወንበር፤የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት መርሐግብሩን ከዚህ በላቀ መልኩም ለማስቀጠል ተቋሙ እንደሚሰራ እና የወር ወንበር ሁሌም በወሩ የመጨረሻ ሳምንት ቅዳሜ ላይ የሚዘጋጅ በመሆኑ ታዳሚያን ይገኙ ዘንድ የክብር ጥሪን አስተላልፈዋል።
Read 470 times