Saturday, 23 May 2026 18:28

ከቻይናዊው አርሶ አደር ፊኛ ውስጥ 1.3 ኪ.ግራም የሚመዝን ግዙፍ ጠጠር በቀዶ ሕክምና ተወገደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በቻይና ጓንግዶንግ ግዛት ከሚኖሩ አንድ የ56 ዓመት አርሶ አደር ፊኛ ውስጥ ለሦስት ዓመታት ያህል የቆየና 1.3 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጅግ ግዙፍ ጠጠር በስኬት ተወገደ። ግለሰቡ ከዓመታት በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ የመሽናት ፍላጎትና የሽንት መውጣት ችግር ቢያጋጥማቸውም፣ ምልክቶቹን ቀላል አድርገው በመመልከታቸው ወደ ሕክምና ተቋም ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ሕመሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰባቸውና እየጠነከረ በመምጣቱ፣ በቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ግፊት ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ ለማድረግ ተገደዋል።
በጓንግዶንግ ሕክምና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተደረገላቸው የራጅና የላብራቶሪ ምርመራ በፊኛቸው ውስጥ ሙሉ የሽንት ፍሰትን የዘጋ ግዙፍ የካልሲየም ክምችት (ጠጠር) እንዳለ አሳይቷል። የሽንትና ፍሳሽ ሕክምና ክፍል ምክትል ዋና ሐኪም ሊን ዩዋን እንደገለጹት፣ ከታካሚው የወጣው ጠጠር 10 ሴንቲሜትር ስፋት እና 13 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ ክብደቱም ከአንድ ትልቅ ዱባ ጋር እኩል ወይም 1.3 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ግዙፍ ጠጠር በፊኛው ግድግዳ ላይ ለረጅም ጊዜ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና ምክንያት የታካሚውን ሕይወት ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ሆኖም ግን ሆስፒታሉ የተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ባለሙያዎችን ያካተተ ልዩ የዶክተሮች ቡድን በማደራጀት፣ ያደረጉትን ጥንቃቄ የተሞላበት ቀዶ ሕክምና በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ የሰውየውን ሕይወት ሊታደጉ ችለዋል።
AMN-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 3712 times