Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 09:25

ፖርቱጋል ኢኮኖሚውን ለመታደግ 4 በዓላትን ሰረዘች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በኢኮኖሚ ቀውስ ከተዘፈቁት የአውሮፓ አገሮች አንዷ በሆነችው ፖርቱጋል አራት ብሔራዊ በአሎች ተሰርዘው የስራ ቀናት እንዲሆኑ መወሰኑ ተገለፀ፡፡ ውሳኔው የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሏል፡፡ በፖርቱጋል በአመት አስራ አራት በአሎችን ለማክበር ስራ ይዘጋ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ውሳኔ መሠረት ህዳር አንድ ይከበር የነበረው የቅዱሳን ቀን እና ከፋሲካ በኋላ በስልሳኛው ቀን የሚከበር ሃይማኖታዊ በአል የስራ ቀን እንደሆኑ ተወስኗል፡፡ በሀይማኖታዊ በአሎች የስራ ቀን መሆን ቫቲካን የፖርቹጋልን ኢኮኖሚ ለመታደግ የሚያግዝ ከሆነ በሚል ስምምነቷን ገልፃለች፡፡

ሚዛናዊ ለመሆን በሚል የስራ ቀን እንዲሆኑ ከተደረጉት ውስጥ ሁለት የሲቪል በአሎች የሚገኙበት ሲሆን አንደኛው በ1640 ፖርቹጋል ከስፔይን ነፃ የወጣችበት ዲሴምበር አንድ ነው፡፡ ሁለተኛው በ1910 የፖርቱጋል ሪፐብሊክ መመስረትን ተከትሎ ብሔራዊ በአል ሆኖ የቆየው ኦክቶበር አምስት እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

 

 

Read 4608 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 09:32