Saturday, 17 December 2011 10:52

የካዝና ሰባሪው ንስሃ

Written by  ኦ. ሄንሪ
Rate this item
(0 votes)

2011-12-17

“ጂሚ፤ ይቅርታ... ቶሎ አልደረስንለህም” አሉ ማይክ ዳለን። “ስፕሪንፊልድ ውስጥ ተቃውሞ ተነሳብን፤ አገረ ገዢውም እምቢ ሊሉ ትንሽ ነበር የቀራቸው። የምህረት ደብዳቤውን ላለመፈረም አንገራግረው ነበር። ግን አንተ ደህና ነህ... እ?”
“ሰላም ነው” አለ ጂሚ። “ቁልፌ አለ?”
ቁልፉን ተቀብሎ የፎቅ ደረጃውን እንደወጣ፤ የዳር የሚገኘውን ክፍል ከፍቶ ገባ። ምንም የተነካ ነገር የለም። ሁሉም ነገር፤ እንደነበረው ነው። ወለሉ ላይ የሸሚዝ ቁልፍ ወድቋል። ከታዋቂው መርማሪ ፖሊስ፤ ከቤን ፕራይስ ሸሚዝ የተበጠሰ ቁልፍ ነው - ያኔ ጂሚን ለማሰር ሲመጡ በተፈጠረ ግርግር።
ወደ ግድግዳው ተጣብቆ የነበረውን ታጣፊ አልጋ በመዘርጋት፤ ግድግዳውን ዳበሰ ጂሚ። አነስ ያለ ሰሌዳ አንሸራተተና፤ በአቧራ የተሸፈነ ሻንጣ ጎትቶ አወጣ። ሻንጣውን ከፍቶ፤ በፍቅር አይን ውስጡን ቃኘ። በአገሪቱ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው የተራቀቁ ምርጥ የዝርፊያ መሳሪያዎች ተደርድረዋል። የተሟላ መሳሪያ ነው። በልዩ ትእዛዝ፤ ተነጥሮና ተቀምሮ ከተሰራ ጠንካራ ብረት የተዘጋጁ መሳሪያዎች፤ በአዲስ ዲዛይን የተሰሩ መሰርሰሪያና መቦርበሪያዎች፤ መብሻ ዘንጎችና መቆንጠጫዎች፤ ሽብልቆችና መጭመቂያቆች... ሁለት ሶስቱ መሳሪያዎች በጂሚ በራሱ የተሰሩና የሚኮራባቸው ልዩ ፈጠራዎች ናቸው። ሌሎቹን መሳሪያዎች በትእዛዝ ለማሰራት፤ ብዙ ገንዘብ አውጥቷል - ሁለት መኪና የሚያስገዛ ገንዘብ።
ከግማሽ ሰአት በኋላ፤ ከክፍሉ የወጣው ጂሚ፤ ደረጃውን ወርዶ ቡና ቤቱ ጋ ደርሷል። በልኩ የተሰፋና ያማረ ልብስ አድርጓል። አቧራው ተራግፎ የተወለወለ ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሏል።
“የተገኘ ስራ አለ?” ጠየቀ ማይክ ዳላን በወዳጅነት ስሜት።
“ማ? እኔ?” አለ ጂሚ ግራ በተጋባ ስሜት። “አልገባኝም። የኒውዮርክ አኝጥንቅሽ የብስኩት ኩባንያ ወኪል ነኝ”
የሚግባቡት ቋንቋ ነው። ማይክ በዚህ ንግግር ከመደሰቱ የተነሳ፤ ጂሚን ካልጋበዝኩህ ብሎ ያዘው - የሚኩረፈረፍ ወተት ነው ግብዣው፤ ጂሚ አልኮል አይጠጣም።....
***
ጂሚ ከተፈታ ከሳምንት በኋላ ነው፤ በሪችሞንድ ከተማ የተዋጣለት የካዝና ዝርፊያ እንደተፈፀመ የተወራው። ሁለት መኪና የሚያስገዛ አነስተኛ ገንዘብ ከመወሰዱ በስተቀር፤ ይህ ፀሃፊ ስለዝርፊያው ዝርዝር መረጃ የለውም። ሁለት ሳምንት ቆይቶ ደግሞ፤ 40 ኪሜ ያህል ራቅ ብሎ በሚገኝ ሎጋንስፓርት ከተማ ሌላ ዝርፊያ ተፈጠረ። ተሻሽሎ የተሰራና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠለት አንድ ካዝና፤ እንደቅርፊት በቀላሉ ተከፍቶ ተገኘ። በውስጡ የነበረው ገንዘብ የለም - ከመጀመሪያው ዝርፊያ በእጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ። ይህም ነው፤ የፖሊሶችን ትኩረት የሳበው። እንደገና በምእራብ አቅጣጫ በበርካታ መቶ ኪ.ሜ ርቀት ጄፈርሰን ሲቲ ውስጥ፤ እድሜ የጠገበ የባንክ ካዝና፤ ኦና ቀረ። የሚዘረፈው ገንዘብ አሁንም በእጥፍ እየጨረ ነው - በካዝናው የነበረ ገንዘብ አስር መኪና ባያዝገዛ ነው? ዝርፊያው በጣም እየጨመረ ከመሄዱ የተነሳ፤ ጉዳዩ ወደ ታዋቂው መርማሪ ፖሊስ ወደ ቤን ፕራይስ ደርሷል።
በየከተሞቹ በፖሊስ ተዘጋጅተው የተመጡ ሪፖርቶችን በማንበብ፤ የዝርፊያዎቹ ዘዴዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን ታዝቧል - ቤን ፕራይስ። የዝርፊያዎቹ ቦታዎች ጋ በአካል እየሄደም መርምሯል። ከምርመራው በኋላ ቤን ፕራይስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ተሰምቷል...
“እነዚህማ የጂሚ ቫለንታይን ፈርማዎች ናቸው። እንደገና ወደ ስራው ተመልሷል ማለት ነው። የካዝናውን ቁልፍ እንዴት በቀላሉ እንደነቀለው ተመልከቱ፤ ከእርጥብ መሬት ካሮት እንደመምዘዝ ያህል ነው የቀለለው። ይህን ቁልፍ ለመንቀል የሚችል መወጠሪያና መጭመቂያ መሳሪያ ያለው ጂሚ ቫለንታይን ብቻ ነው። የቁልፉ ተወርዋሪ ለማዞር፤ ቀለበቶቹን እንዴት አስተካክሎ ያለ እንከን እንደነደላቸው አያችሁ? አንድ ቀዳዳ ብቻ ሰርስሮ፤ እንዲህ ካዝናዎችን መክፈት የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ጂሚ ቫለንታይንን ፈልጉልኝ። አሁን ስንይዘው፤ ሙሉ ለሙሉ የእስር ጊዜውን ይጠጣታል - በምህረት መለቀቅና በአጭር ጊዜ መፈታት ብሎ ነገር አይኖርም”
ቤን ፕራይስ፤ የጂሚን ባህርይ ያውቃል። ከተማ እያራራቀ ነው ካዝና የሚሰብረው። ሞጭልፎ እልም ነው። በጋራ ወይም በትብብር ሳይሆን ለብቻው ነው የሚሰራው። እና ደግሞ፤ ከታዋቂ ሰዎችና ከተከበሩ ቤተሰቦች ጋር ተቀራርቦ፤ ተወዳጅቶ መኖር ይፈልጋል። ጂሚ ቫለንታይን ብዙውን ጊዜ፤ ከቅጣትና ከእስር የማምለጥ እድል የሚያገኘው በእነዚህ ባህሪዎቹ ነው። ቤን ፕራይስ፤ ካዝና ሰባሪውን ለመያዝ ዱካውን መከታተል እንደጀመረ አገር ምድሩ ያውቃል። እስከዚያው ግን፤ “አይነኬ ካዝና” የገዙ ሰዎች ብቻ ናቸው፤ ያለ ሃሳብ ተኝተው ለማደር የቻሉት።
በዚህ መሃል፤ በመቶ ኪሎሜትሮች ርቀት፤ በአርካንሳ ግዛት ኢልሞር ወደ ምትባል ከተማ፤ ጂሚ ቫለንታይን ከነሻንጣው ከተፍ አለ። የስፖርተኛ ቁመናው ሲታይ፤ ከዩኒቨሪሲቲ ትምህርት ለእረፍት ወደ መኖሪያ ከተማው የሚመለስ ወጣት ይመስላል። በሰፊው የእግረኛ መንገድ ፤ታች ወዳለው ሆቴል አቅጣጫ እየተራመደ ነው። አንዲት ወጣት ሴት፤ መንገዱን አቋርጣ፤ በጂሚ አጠገብ አለፈችና በር ከፍታ ገባች። በሩ ላይ፤ “ኢልሞር ባንክ” የሚል ፅሁፍ ይታያል። ከመግባቷ በፊት፤ ጂሚ ቫለንታይን ወደ ወጣቷ አይኖች ጠልቆ አየ። እናም፤ ራሱን ረስቶና ዘንግቶ፤ ሌላ... ሌላ ሰው ሆነ። ወጣቷ አይኗን ሰበረች፤ ፊቷም ቀላ። ጂሚን የመሰለ ወጣትና ማራኪ ቁመና፤ በኢልሞር ብርቅ ነው።
ጂሚ፤ የባንኩ ደረጃዎች ላይ ሲንገላወድ ያገኘውን ልጅ ለቀም አድርጎ፤ ስለከተማዋ በጥያቄ ያጣድፈው ጀምሯል፤ በየመሃሉ ሳንቲሞችን እያስታቀፈ። ብዙም ሳይቆይ ወጣቷ፤ ከባንኩ ወጣች። ቅድም ያየችውን ወጣት፤ ጂሚን ከቁብ ሳትቆጥርና ዞር ብላም ሳታይ፤ መንገዷን ቀጠለች።
“ይህች፤ ወይዘሪት ፖሊ ሲምፕሰን አይደለች እንዴ?” አለ ጂሚ አሳማኝ በሚመስል አጠያየቅ።
“አይ” አለ ልጁ። “ይህችማ፤ አናቤል አዳምስ ነች። ባንኩ የአባቷ ነው። ወደ ኢልሞር ምን ልትሰራ መጣህ? እንዴ፤ የሰአት ማሰሪያህ ወርቅ ነው አይደል? ሽጉጥ ልገዛ ነው። ሳንቲም አትጨምርልኝም?”ጂሚ ልጁን ትቶ ወደ ሆቴሉ ሄደ። ራልፍ ስፔንሰር በሚል ስም ቤርጎ ከተከራየ በኋላ፤ በጠረጴዛው ላይ ጠጋ ብሎ፤ አዲስና ትኩስ እቅዱን፤ ለእንግዳ ተቀባዩ በይፋ ገለፀ። የሆነ ቦታ አግኝቶ አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ ኢልሞር እንመጣ ተናገረ። “ከተማዋ ውስጥ የጫማ ገበያ እንዴት ነው? የጫማ ቢዝነስ ለመጀመር... የሚያዋጣ ይመስልሃል?...”እንግዳ ተቀባዩ፤ በጂሚ አለባበስና ስነስርአት ተማርኳል። “ሚስተር ራልፍ ስፔንሰር፤  ለጫማ ቢዝነስ ጥሩ ገበያ የሚኖር ይመስለኛል” ... እንግዳ አተቀባዩ የሚችለውን ያህል ለማብራራት ሞክሯል። “በኢልሞር ጫማ ብቻ የሚሸጥ ድርጅት የለም። የከተማዋ ገበያ በአጠቃላይ ደህና ነው። የከተማዋ ሰውም ተግባቢ ነው...” አብራርቶ ሲያበቃ፤ የእንግዳውን ሻንጣ ወደ መኝታ ክፍል ማድረስ እንደሚያስፈልግ ያውቃል።“ግድ የለም። ሻንጣዬ ትንሽ ስለሚከብድ ራሴ እይዘዋለሁ” አለ ራልፍ ስፔንሰር። ማለትም ጂሚ ቫለንታይን።በጂሚ ቫለንታይን መቃብር ላይ ነው ራልፍ ስፔንሰር የበቀለው። ከአንዲት ወይዘሪት በተመዝገዘገው የፍቅር ነበልባል አማካኝነት ጂሚ ቫለንታይን አመድ ሲሆን፤ ከአመዱ ውስጥ ነፍስ ዘርቶ የተፈጠረው ራልፍ ስፔንሰር፤ በኢልሞር ከተማ ከእንግድነት አልፎ ቀስ በቀስ ስመ ጥርና ነባር የከተማዋ ነዋሪ ሆኗል። የጫማ ቢዝነስ ከፍቶ ጥሩ ንግድ እያካሄደ ነው። ብዙ ጓደኞችንና ወዳጆችን አፍርቷል። እናም የልብ ምኖቱን ከእጁ አስገብቷል። ከአናቤል አዳምስ ጋር ተዋውቆ ይበልጥ ሲቀርባት፤ በመስህቧ ይበልጥ እየተማረከ ጠቅልሎ ልቡን ሰጥቷታል።ይሄውና አንድ አመት አለፈ። የራልፍ ስፔንሰር ህይወትም ይህን ይመስላል። በከተማዋ ውስጥ የተከበረ ሰው ሆኗል። ቢዝነሱ እያበበ ነው። ከአናቤል ጋር ቀለበት አስረው በሁለት ሳምንት ውስጥ በሰርግ ይጋባሉ። እንደ አብዛኞቹ የትንሽ ከተማ ባንከኞች ሁሉ፤ በእርጋታ የሚታትሩት ሚስተር አዳምስ፤ ራልፍ ስፔንሰር ለልጃቸው ጥሩ ባል ይሆናል ብለው በደስታ ተቀብለውታል። አናቤልማ፤ የፍቅሯን ያህል ትኮራበታለች። የአናቤል ታላቅ እህትም ከነባለቤቷ፤ ራልፍ ስፔንሰርን እንደ ቤተሰብ ነው የሚያዩት። የድሮው ጂሚ ቫለንታይን እንዲሁም የድሮው የካዝና ሰበራ ዛሬ የለም። የእስር ታሪኩና የመባዘን ህይወቱም ጠፍቷል። ስሙ ራልፍ ስፔንሰር፤ ስራው የጫማ ቢዝነስ ሆኗል። በከተማዋ ህዝብ የተከበረ ሰው፤ በአናቤል ፍቅር ያማረ ህይወት አግኝቷል። ወይም የዚያን ጣፋጭ ህይወት ጫፍ በእጁ ይዟል። ይዘልቅ ይሆን? የድሮውንና የዛሬውን ህይወት የሚያደባልቅ ነገር ሲፈጠር ነው ጉዱ። ይቀጥላል።

እስረኞች የእጅ ስራ ወደሚሰሩበት ክፍል፤ አንዱ ጠባቂ ሲመጣ፤ ጂሚ ቫለንታይን በጥንቃቄ ጫማ እየሰፋ ነበር - በስራው ተመስጦ። ጠባቂው ጂሚን ይዞ ወደ እስር ቤቱ ሃላፊ ወሰደው። ሃላፊው እዚያው ቢሮው ውስጥ ነው፤ የምህረት ደብዳቤውን ለጂሚ የሰጡት። የክልሉ አገረ ገዢ፤ ያን እለት ጥዋት የፈረሙበት የምህረት ደብዳቤ ነው። ጂሚ ደብዳቤውን ሲቀበል፤ የድካም ስሜት የተጫጫነው ይመስላል። የአራት አመት እስር ከተፈረደበት በኋላ፤ ይሄውና አስር ወራት በእስር አሳልፏል። ቢበዛ፤ ከሶስት ወር በላይ እንደማይቆይ ነበር የገመተው። እንደ ጂሚ ቫለንታይን ብዙ ወዳጅ ጓደኛ ያለው ሰው ወደ እስር ቤት ሲመጣ፤ ፀጉሩን መላጨት ዋጋ የሌለው ከንቱ ድካም ነው - በእስር ቤቱ ብዙ አይቆይም።

“ስማኝ፤ አቶ ጂሚ” አሉ የእስር ቤቱ ሃላፊ፤ “ነገ ጥዋት ከእስር ትወጣለህ። ሰው ለመሆን... በወኔ ጠንከር ማለት ነው። ውስጥህ ሲታይ መጥፎ ሰው አይደለህም። ልብህ ንፁህ ነው። ከእንግዲህ፤ ካዝናዎችን መስበር ይቅርብህ። በቅንነት ኑር”

“እኔ?” አለ ወጣቱ ጂሚ በመደነቅ ስሜት። “እንዴት? በህይወት ዘመኔ፤ አንድም ካዝና ሰብሬ አላውቅም”

“ኧረ በጭራሽ” ...የእስር ቤቱ ሃላፊ ሳቃቸውን ለቀቁት። “አንድም ካዝና አልሰበርክም። እስቲ አስብ ካስታወስክ። በስፕሪንፊልድ ከተማ ካዝና ተሰብሮ ስለተዘረፈ፤ እንዴት አንተ ወደ ወህኒ የተወረወርክ? በዝርፊያው ቦታ እንዳልነበርክ፤ ከካዝናው አጠገብ እንዳልደረስክ የሚያረጋግጥ፤ ‘ከኔ ጋር ነበር’ ብሎ ቃል የሚሰጥ የሚል ምስክር አጥተህ ነው?  ‘ከተማው ሁሉ የሚያከብራቸው እመቤት ጋ ለአዳር ሄጄ ስለነበር፤ የሳቸውን ሚስጥርና ክብር ለመጠበቅ ስል እስር ቤት ገባሁ’ በለኛ!። ወይስ አዛውንቱ ዳኛ በምቀኝነት ስለጠመዱህ ብቻ ይሆን? ሁሌም የምሰማቸው ምክንያቶች ናቸው - ከወንጀሉ ንፁህ ነን ከሚሉ እስረኞች።”

“እኔ?” አለ ጂሚ፤ አሁንም ንፁህ ነኝ በሚል ያፈጠጠ ስሜት። “እንዴት? በህይወት ዘመኔ ስፕሪንግፊል ከተማን ረግጬ አላውቅም”

“በል መልሰህ ውሰደው” አሉ የእስር ቤቱ ሃላፊ በፈገግታ ወደ ጠባቂው ዞር ብለው። “ቅያሪ ልብስ ስጠው። ነገ ጥዋት፤ አንድ ሰአት ወደ መሰናበቻው ቢሮ ታመጣዋለህ። ለማንኛውም አቶ ጂሚ፤ የመከርኩህን ልብ ብትል ይበጅሃል”

ጂሚ፤ በማግስቱ ጥጠዋት፤ በመሰናበቻው ቢሮ ውስጥ ቆሟል። እስረኞችን ለማሰናበት የሚዘጋጀውን አስቀያሚ ልብስ ለብሷል - የቆረፈደና ሲጥሲጥ ከሚል ጫማ ጋር።

የቢሮው ተላላኪ፤ የባቡር ቲኬት እና አምስት ዶላር ለጂሚ አስጨበጠው - በዚህችው ነው የራሱን ኑሮ መልሶ በማቋቋም ጥሩ ዜጋ እንዲወጣውና ሃብት እንዲያፈራ የሚጠበቅበት። የእስር ቤቱ ሃላፊ ደግሞ ሲጋራ ሰጠው - ለስንብት እየተጨባበጡ። “9762” በሚል የእስረኛ ቁጥር የተመዘገበው ጂሚ ቫለንታይን፤ በአገረ ገዢው የምህረት ደብዳቤ ከእስር እንደተለቀቀ መዝገቡ ውስጥ ተፃፈና ወጣ - ፏ ያለውን ሰማይ እያየ የነፃነት አየር ሊተነፍስ።

እሱ ግን፤ የወፎቹን ዜማ፤ የለምለም ዛፎችን ውዝዋዜ፤ የአበቦቹን መአዛ ከምንም ሳይቆጥር፤ በቀጥታ ወደ ምግብ ቤት አመራ። እዚያም የመጀመሪያውን የነፃነት ጣፋጭነት አጣጣመ - የዶሮ ጥብሱን በነጭ ወይን እያወራረደ። ከዚያም ምርጥ ሲጋራ እያጨሰ። ከምግብ ቤቱ እንደወጣ፤ ዘና ብሎ ወደ ባቡር ጣቢያው ተራመደ። ከበሩ ስር ተቀምጦ ለሚለምነው አይነስውር ስሙኒ ወርውሮ ባቡሩን ተሳፈረ። ከሶስት ሰአት በኋላ ነው ከባቡሩ ወርዶ በትንሿ ከተማ ወደሚገኘው ቡና ቤት የሄደው። የቡና ቤቱ ባለቤት ማይክ ዳለን፤ ከባንኮኒው ጀርባ ለብቻቸው ቆመዋል። ጂሚና ማይክ ተጨባበጡ።

“ጂሚ፤ ይቅርታ... ቶሎ አልደረስንለህም” አሉ ማይክ ዳለን። “ስፕሪንፊልድ ውስጥ ተቃውሞ ተነሳብን፤ አገረ ገዢውም እምቢ ሊሉ ትንሽ ነበር የቀራቸው። የምህረት ደብዳቤውን ላለመፈረም አንገራግረው ነበር። ግን አንተ ደህና ነህ... እ?”

“ሰላም ነው” አለ ጂሚ። “ቁልፌ አለ?”

ቁልፉን ተቀብሎ የፎቅ ደረጃውን እንደወጣ፤ የዳር የሚገኘውን ክፍል ከፍቶ ገባ። ምንም የተነካ ነገር የለም። ሁሉም ነገር፤ እንደነበረው ነው። ወለሉ ላይ የሸሚዝ ቁልፍ ወድቋል። ከታዋቂው መርማሪ ፖሊስ፤ ከቤን ፕራይስ ሸሚዝ የተበጠሰ ቁልፍ ነው - ያኔ ጂሚን ለማሰር ሲመጡ በተፈጠረ ግርግር።

ወደ ግድግዳው ተጣብቆ የነበረውን ታጣፊ አልጋ በመዘርጋት፤ ግድግዳውን ዳበሰ ጂሚ። አነስ ያለ ሰሌዳ አንሸራተተና፤ በአቧራ የተሸፈነ ሻንጣ ጎትቶ አወጣ። ሻንጣውን ከፍቶ፤ በፍቅር አይን ውስጡን ቃኘ። በአገሪቱ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው የተራቀቁ ምርጥ የዝርፊያ መሳሪያዎች ተደርድረዋል። የተሟላ መሳሪያ ነው። በልዩ ትእዛዝ፤ ተነጥሮና ተቀምሮ ከተሰራ ጠንካራ ብረት የተዘጋጁ መሳሪያዎች፤ በአዲስ ዲዛይን የተሰሩ መሰርሰሪያና መቦርበሪያዎች፤ መብሻ ዘንጎችና መቆንጠጫዎች፤ ሽብልቆችና መጭመቂያቆች... ሁለት ሶስቱ መሳሪያዎች በጂሚ በራሱ የተሰሩና የሚኮራባቸው ልዩ ፈጠራዎች ናቸው። ሌሎቹን መሳሪያዎች በትእዛዝ ለማሰራት፤ ብዙ ገንዘብ አውጥቷል - ሁለት መኪና የሚያስገዛ ገንዘብ።

ከግማሽ ሰአት በኋላ፤ ከክፍሉ የወጣው ጂሚ፤ ደረጃውን ወርዶ ቡና ቤቱ ጋ ደርሷል። በልኩ የተሰፋና ያማረ ልብስ አድርጓል። አቧራው ተራግፎ የተወለወለ ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሏል።

“የተገኘ ስራ አለ?” ጠየቀ ማይክ ዳላን በወዳጅነት ስሜት።

“ማ? እኔ?” አለ ጂሚ ግራ በተጋባ ስሜት። “አልገባኝም። የኒውዮርክ አኝጥንቅሽ የብስኩት ኩባንያ ወኪል ነኝ”

የሚግባቡት ቋንቋ ነው። ማይክ በዚህ ንግግር ከመደሰቱ የተነሳ፤ ጂሚን ካልጋበዝኩህ ብሎ ያዘው - የሚኩረፈረፍ ወተት ነው ግብዣው፤ ጂሚ አልኮል አይጠጣም።....

***

ጂሚ ከተፈታ ከሳምንት በኋላ ነው፤ በሪችሞንድ ከተማ የተዋጣለት የካዝና ዝርፊያ እንደተፈፀመ የተወራው። ሁለት መኪና የሚያስገዛ አነስተኛ ገንዘብ ከመወሰዱ በስተቀር፤ ይህ ፀሃፊ ስለዝርፊያው ዝርዝር መረጃ የለውም። ሁለት ሳምንት ቆይቶ ደግሞ፤ 40 ኪሜ ያህል ራቅ ብሎ በሚገኝ ሎጋንስፓርት ከተማ ሌላ ዝርፊያ ተፈጠረ። ተሻሽሎ የተሰራና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠለት አንድ ካዝና፤ እንደቅርፊት በቀላሉ ተከፍቶ ተገኘ። በውስጡ የነበረው ገንዘብ የለም - ከመጀመሪያው ዝርፊያ በእጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ። ይህም ነው፤ የፖሊሶችን ትኩረት የሳበው። እንደገና በምእራብ አቅጣጫ በበርካታ መቶ ኪ.ሜ ርቀት ጄፈርሰን ሲቲ ውስጥ፤ እድሜ የጠገበ የባንክ ካዝና፤ ኦና ቀረ። የሚዘረፈው ገንዘብ አሁንም በእጥፍ እየጨረ ነው - በካዝናው የነበረ ገንዘብ አስር መኪና ባያዝገዛ ነው? ዝርፊያው በጣም እየጨመረ ከመሄዱ የተነሳ፤ ጉዳዩ ወደ ታዋቂው መርማሪ ፖሊስ ወደ ቤን ፕራይስ ደርሷል።

በየከተሞቹ በፖሊስ ተዘጋጅተው የተመጡ ሪፖርቶችን በማንበብ፤ የዝርፊያዎቹ ዘዴዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን ታዝቧል - ቤን ፕራይስ። የዝርፊያዎቹ ቦታዎች ጋ በአካል እየሄደም መርምሯል። ከምርመራው በኋላ ቤን ፕራይስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ተሰምቷል...

“እነዚህማ የጂሚ ቫለንታይን ፈርማዎች ናቸው። እንደገና ወደ ስራው ተመልሷል ማለት ነው። የካዝናውን ቁልፍ እንዴት በቀላሉ እንደነቀለው ተመልከቱ፤ ከእርጥብ መሬት ካሮት እንደመምዘዝ ያህል ነው የቀለለው። ይህን ቁልፍ ለመንቀል የሚችል መወጠሪያና መጭመቂያ መሳሪያ ያለው ጂሚ ቫለንታይን ብቻ ነው። የቁልፉ ተወርዋሪ ለማዞር፤ ቀለበቶቹን እንዴት አስተካክሎ ያለ እንከን እንደነደላቸው አያችሁ? አንድ ቀዳዳ ብቻ ሰርስሮ፤ እንዲህ ካዝናዎችን መክፈት የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ጂሚ ቫለንታይንን ፈልጉልኝ። አሁን ስንይዘው፤ ሙሉ ለሙሉ የእስር ጊዜውን ይጠጣታል - በምህረት መለቀቅና በአጭር ጊዜ መፈታት ብሎ ነገር አይኖርም”

ቤን ፕራይስ፤ የጂሚን ባህርይ ያውቃል። ከተማ እያራራቀ ነው ካዝና የሚሰብረው። ሞጭልፎ እልም ነው። በጋራ ወይም በትብብር ሳይሆን ለብቻው ነው የሚሰራው። እና ደግሞ፤ ከታዋቂ ሰዎችና ከተከበሩ ቤተሰቦች ጋር ተቀራርቦ፤ ተወዳጅቶ መኖር ይፈልጋል። ጂሚ ቫለንታይን ብዙውን ጊዜ፤ ከቅጣትና ከእስር የማምለጥ እድል የሚያገኘው በእነዚህ ባህሪዎቹ ነው። ቤን ፕራይስ፤ ካዝና ሰባሪውን ለመያዝ ዱካውን መከታተል እንደጀመረ አገር ምድሩ ያውቃል። እስከዚያው ግን፤ “አይነኬ ካዝና” የገዙ ሰዎች ብቻ ናቸው፤ ያለ ሃሳብ ተኝተው ለማደር የቻሉት።

በዚህ መሃል፤ በመቶ ኪሎሜትሮች ርቀት፤ በአርካንሳ ግዛት ኢልሞር ወደ ምትባል ከተማ፤ ጂሚ ቫለንታይን ከነሻንጣው ከተፍ አለ። የስፖርተኛ ቁመናው ሲታይ፤ ከዩኒቨሪሲቲ ትምህርት ለእረፍት ወደ መኖሪያ ከተማው የሚመለስ ወጣት ይመስላል። በሰፊው የእግረኛ መንገድ ፤ታች ወዳለው ሆቴል አቅጣጫ እየተራመደ ነው። አንዲት ወጣት ሴት፤ መንገዱን አቋርጣ፤ በጂሚ አጠገብ አለፈችና በር ከፍታ ገባች። በሩ ላይ፤ “ኢልሞር ባንክ” የሚል ፅሁፍ ይታያል። ከመግባቷ በፊት፤ ጂሚ ቫለንታይን ወደ ወጣቷ አይኖች ጠልቆ አየ። እናም፤ ራሱን ረስቶና ዘንግቶ፤ ሌላ... ሌላ ሰው ሆነ። ወጣቷ አይኗን ሰበረች፤ ፊቷም ቀላ። ጂሚን የመሰለ ወጣትና ማራኪ ቁመና፤ በኢልሞር ብርቅ ነው።

ጂሚ፤ የባንኩ ደረጃዎች ላይ ሲንገላወድ ያገኘውን ልጅ ለቀም አድርጎ፤ ስለከተማዋ በጥያቄ ያጣድፈው ጀምሯል፤ በየመሃሉ ሳንቲሞችን እያስታቀፈ። ብዙም ሳይቆይ ወጣቷ፤ ከባንኩ ወጣች። ቅድም ያየችውን ወጣት፤ ጂሚን ከቁብ ሳትቆጥርና ዞር ብላም ሳታይ፤ መንገዷን ቀጠለች።

“ይህች፤ ወይዘሪት ፖሊ ሲምፕሰን አይደለች እንዴ?” አለ ጂሚ አሳማኝ በሚመስል አጠያየቅ።

“አይ” አለ ልጁ። “ይህችማ፤ አናቤል አዳምስ ነች። ባንኩ የአባቷ ነው። ወደ ኢልሞር ምን ልትሰራ መጣህ? እንዴ፤ የሰአት ማሰሪያህ ወርቅ ነው አይደል? ሽጉጥ ልገዛ ነው። ሳንቲም አትጨምርልኝም?”ጂሚ ልጁን ትቶ ወደ ሆቴሉ ሄደ። ራልፍ ስፔንሰር በሚል ስም ቤርጎ ከተከራየ በኋላ፤ በጠረጴዛው ላይ ጠጋ ብሎ፤ አዲስና ትኩስ እቅዱን፤ ለእንግዳ ተቀባዩ በይፋ ገለፀ። የሆነ ቦታ አግኝቶ አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ ኢልሞር እንመጣ ተናገረ። “ከተማዋ ውስጥ የጫማ ገበያ እንዴት ነው? የጫማ ቢዝነስ ለመጀመር... የሚያዋጣ ይመስልሃል?...”እንግዳ ተቀባዩ፤ በጂሚ አለባበስና ስነስርአት ተማርኳል። “ሚስተር ራልፍ ስፔንሰር፤  ለጫማ ቢዝነስ ጥሩ ገበያ የሚኖር ይመስለኛል” ... እንግዳ አተቀባዩ የሚችለውን ያህል ለማብራራት ሞክሯል። “በኢልሞር ጫማ ብቻ የሚሸጥ ድርጅት የለም። የከተማዋ ገበያ በአጠቃላይ ደህና ነው። የከተማዋ ሰውም ተግባቢ ነው...” አብራርቶ ሲያበቃ፤ የእንግዳውን ሻንጣ ወደ መኝታ ክፍል ማድረስ እንደሚያስፈልግ ያውቃል።“ግድ የለም። ሻንጣዬ ትንሽ ስለሚከብድ ራሴ እይዘዋለሁ” አለ ራልፍ ስፔንሰር። ማለትም ጂሚ ቫለንታይን።በጂሚ ቫለንታይን መቃብር ላይ ነው ራልፍ ስፔንሰር የበቀለው። ከአንዲት ወይዘሪት በተመዝገዘገው የፍቅር ነበልባል አማካኝነት ጂሚ ቫለንታይን አመድ ሲሆን፤ ከአመዱ ውስጥ ነፍስ ዘርቶ የተፈጠረው ራልፍ ስፔንሰር፤ በኢልሞር ከተማ ከእንግድነት አልፎ ቀስ በቀስ ስመ ጥርና ነባር የከተማዋ ነዋሪ ሆኗል። የጫማ ቢዝነስ ከፍቶ ጥሩ ንግድ እያካሄደ ነው። ብዙ ጓደኞችንና ወዳጆችን አፍርቷል። እናም የልብ ምኖቱን ከእጁ አስገብቷል። ከአናቤል አዳምስ ጋር ተዋውቆ ይበልጥ ሲቀርባት፤ በመስህቧ ይበልጥ እየተማረከ ጠቅልሎ ልቡን ሰጥቷታል።ይሄውና አንድ አመት አለፈ። የራልፍ ስፔንሰር ህይወትም ይህን ይመስላል። በከተማዋ ውስጥ የተከበረ ሰው ሆኗል። ቢዝነሱ እያበበ ነው። ከአናቤል ጋር ቀለበት አስረው በሁለት ሳምንት ውስጥ በሰርግ ይጋባሉ። እንደ አብዛኞቹ የትንሽ ከተማ ባንከኞች ሁሉ፤ በእርጋታ የሚታትሩት ሚስተር አዳምስ፤ ራልፍ ስፔንሰር ለልጃቸው ጥሩ ባል ይሆናል ብለው በደስታ ተቀብለውታል። አናቤልማ፤ የፍቅሯን ያህል ትኮራበታለች። የአናቤል ታላቅ እህትም ከነባለቤቷ፤ ራልፍ ስፔንሰርን እንደ ቤተሰብ ነው የሚያዩት። የድሮው ጂሚ ቫለንታይን እንዲሁም የድሮው የካዝና ሰበራ ዛሬ የለም። የእስር ታሪኩና የመባዘን ህይወቱም ጠፍቷል። ስሙ ራልፍ ስፔንሰር፤ ስራው የጫማ ቢዝነስ ሆኗል። በከተማዋ ህዝብ የተከበረ ሰው፤ በአናቤል ፍቅር ያማረ ህይወት አግኝቷል። ወይም የዚያን ጣፋጭ ህይወት ጫፍ በእጁ ይዟል። ይዘልቅ ይሆን? የድሮውንና የዛሬውን ህይወት የሚያደባልቅ ነገር ሲፈጠር ነው ጉዱ። ይቀጥላል።

Read 3524 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:57