Saturday, 26 May 2012 12:11

..ልጄን ለበሽታ ያጋለጣት... የእውቀት ማነስ ነው፡፡..

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

....እኔ እድሜዬ ወደ 19 አመት ገደማ ነው፡፡ የተዳርኩት በውስጤ ብዙ ንዴት እያለብኝ ነው፡፡ እሱም እንደጉዋደኞቼ ትምህርን ሳልማር ...በደንብ ሳልጫወት በመሆኑ ነው፡፡ ትምህርን ገና አራተኛ ክፍል ስገባ ነበር ትዳር እንድይዝ የተደረግሁት፡፡ ቀድሞውንም በጊዜው ትምህርት ቤት ስላልገባሁ በእርግጥ ዘግይቼአለሁ፡፡ ቢሆንም ግን ይኄው አሁን ጉዋደኞቼ ወደ ሰባተኛ ክፍል እየደረሱ ናቸው፡፡ ታዲያ ልጅ ባረገዝኩበት ጊዜ በጣም ከመበሳጨ የተነሳ ጤንነን ለመጠበቅ የሚነገረኝን ነገር ሁሉ ምንም አልቀበልም ነበር፡፡ በሁዋላም ልጅትዋ ተወለደች፡፡ በቃ ተገላገልኩ ብዬ ጉዋደኞቼ ትምህርት በሌላቸው ጊዜም ይሁን ከትምህርት ውለው ሲመጡ ከእነርሱ ጋር መጫወት እወድ ነበር፡፡ ልጅቱዋ ጡት ብትጠባ ባትጠባ ምንም ግድ የለኝም፡፡ የባለቤ እናት ሲቆጡኝ ሁሉን ነገር ትቼ ወደእና እሸሽ ነበር፡፡ በሁዋላ ግን ልጅቱዋ በጣም ታመመች፡፡ ልጅቱዋ በጠና ስትታመም ሁሉ ሰው ተቆጣኝ፡፡ ባለቤ ሁለታችንንም ይዞን ወደዚህ ሆስፒታል አመጣን፡፡ ይኼው አሁን ወር ሆኖናል፡፡ የምግብ እጥረት ይዞአት ነበር አሉ፡፡ ምግብም ይሰጡአታል፡፡ በዚያም ምክንያት ሕመም ይዞአት ነበር፡፡ ሕመሙንም አክመዋታል፡፡ አሁን ደህና ነች፡፡ እኔም ተጸጽቼአለሁ፡፡ ከዚህ በሁዋላ ልጄን በደንብ እይዛለሁ፡፡..

አይሻ ሰኢድ አጣጥ ሆስፒታል

አይሻን ያገኘናት ቡና በመውቀጥ ላይ እያለች ነበር፡፡ ቡናውን የምትወቅጠው ለማን እንደሆነ ስንጠይቃት ሕጻናትን ለማስታመም በሆስፒታሉ መቆያ ክፍል ለተኙ እናቶች መሆኑን ነገረችን፡፡ አጣጥ ሆስፒታል የእናቶች መቆያ እንዳለውና በተለይም እርጉዝ የሆኑ ሴቶች እስከሚወልዱ ድረስ የሚያርፉበት መሆኑን በሚመለከት ሁኔታውን ለመታዘብ ነበር ከዚያ የተገኘነው፡፡ ከወልቂጤ ከተማ 17/ ኪሎሜትር ይህል ወደገጠር የሚገባው አጣጥ ሆስፒታል በምግብ እጥረት ለተጎዱ በአካባቢው ለሚገኙ ሕጻናትም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በሆስፒታሉ የህጻናት ማቆያ ክፍል ያገኘናቸው ባለሙያ ሁኔታውን አስረድተውናልና እናካፍላችሁ፡፡

.. ስሜ እሮዛ ይባላል፡፡ መጀመሪያ በመዋእለ ሕጻናት እሰራ ነበር፡፡ አሁን ግን ጤና ረዳት ሆኛለሁ፡፡ ይህ ክፍል ቃበቈሽሽቄቃ ቈስሻሮሯሽቁሽሮሽቄቃ በቃሽ ይባላል፡፡ ይህም ማለት ሕጻናት ከተወለዱ ጀምሮ የሚከሰትባቸውን የምግብ እጥረት በማስወገድ ህጻናቱ መልሶ ማገገም እንዲችሉ የሚያአስችል ነው፡፡ እናቶች ልጆቻቸውን በመታመማቸው ወይንም ከሚገባው በላይ በመክሳታቸው ምክንያት ሲያመጡ አቸው ክብደታቸው ከእድሜና ከቁመታቸው ጋር ሲነጻጸር ከ60 በታች ከሆነ እነዚህ ልጆች በተቻለ መጠን በሆስፒታሉ እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ እናቶችን በማግባባት ወይንም ካልተቻለ ከቤተሰብ ጋር በመሆን ልጁን ይዘው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ በቆይታቸው ወቅት ለልጁ በቀን በቀን ክትትል በማድረግ ተገቢው አመጋገብና ሕክምና ይሰጣል፡፡ እንዲሁም እናቶች ወደቤታቸወ ከሄዱ በሁዋላ ልጆቻቸውን በደንብ እንዲይዙ ለማስቻል ስለልጅ አያያዝ ትምህርት ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም የልጆቹ ጤና ከታየ በሁዋላ ክብደታቸው መጨመሩ ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡ እናቶች ወደቤታቸው ከሄዱ በሁዋላ በተወሰነ ጊዜ ወደሆስፒታሉ እየመጡ የልጃቸውን የጤንነት ሁኔታ እንዲከታተሉ ምክር ይሰጣል፡፡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአስር እስከአስራ አምስት ልጆችን በዚህ ሁኔታ በመቀበል እናስተናግዳለን፡፡ይህ አገልግሎት ቢስፋፋ ህጻናቱን ከመጎዳት እንደሚያድናቸው እሙን ነው፡፡ ..

በሆስፒታሉ ሕጻናትን ለማስታመም የሚቆዩበትን ክፍል በተመለከትንበት ወቅት ሌሎችንም እናቶች አነጋግረናል፡፡

.. ስሜ በህርያ አህመድ እባላለሁ፡፡ አካባቢዬ ኤዣ ነው፡፡ በትራንስፖርት ካልሆነ በእግር መምጣት አይቻልም፡፡ በቤ የአቅም ችግር ነበረብኝ፡፡ ወተት የመሳሰሉ ትን ነገሮች በቀላሉ ማግኘት አልችልም... በቤም የለም፡፡ ልጄ መጠኑዋ እየቀነሰ ሲመጣ ግን ወደ አጣጥ ሆስፒታል ውሰጃት በማለት ሰዎች ስለነገሩኝ ይዤአት መጣሁ፡፡ ልጅሽ እንድትድን ከፈለግሽ ቁጭ ብለሽ አስታምሚ በተባልኩት መሰረት ሁሉን ነገር ትቼ ቁጭ ካልኩ ይኼው አንድ ወር አለፈኝ፡፡ የቀሩትን ልጆቼን አባታቸው ከቤቱ ይዞ ቁጭ ብሎአል፡፡ እኔ ለልጅቷ የሚሰጠኝን እርዳታ እየተቀበልኩ እየመገብኩ ሕክምናዋንም እየተከታተልኩ አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ድናልኛለች፡፡ ..

ወደሌላው አልጋ ስናማትር በጣም የታመመች ሐጻን ተመለከትን፡፡ በጣም ከሲታ ናት፡፡ የህጻንዋን እናት መልካምነሽን ልጅሽ ምን ሆና ነው ስንል ጠየቅናት፡፡

.. አሁንማ ድና አግኝታችሁዋት ነው... በጣም ነበር የታመመችው፡፡ ትንፋሽም አልነበራትም፡፡ ይኼው ምግብና መድሀኒት ሲሰጣት ሁለት ወር ሆናት... አሁን እግዚአብሔር ይመስገን አገግማለች፡፡ ልጄን ለበሽታ ያጋለጣት ምንም አይደለም ...የእውቀት ማነስ ነው፡፡ ልጄ የታመመችው ቀላሉን በተፈጥሮ የሚገኘውን የጸሐይ ብርሀን አጥታ ነው አሉን ፡፡ ሐኪሙዋም በጣም ነው ያዘነችው፡፡ ምክንያቱም የእውቀት ችግር በመሆኑ ነው፡፡ ..

በሆስፒታሉ ለአስራ አምስት አመት ያገለገሉት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር  ዶ/ር ሪታ ሽፋ እንደሚሉት...

.. በማዋለጃ ክፍላችን እና እናቶች ለሕክምና ...ለእርግዝና ክትትል መጥተው የሚያደ ርጉትን ውይይት እና የሚሰጠውን ሕክምና በሚመለከት ያላቸው ስሜት ሁልጊዜ ይደንቀኛል፡፡ አንዳንዶቹ ከእራሳቸው ልምድ በመነሳት.....እኔ ከአሁን ቀደም የወለድኩት ልጅ ባላወቅሁት ሕመም የተነሳ ሞቶብኛል፡፡ ከዚያ በሁዋላ ግን በዚህ በአጣጥ ሆስፒታል እንዳሳክም ስለተነገረኝ ሁለተኛውን ልጄን አድኛለሁ፡፡ አሁን ደግሞ እኔም እራሴ እስከም ወልድ ድረስ በሆስፒታሉ የእናቶች ማቆያ ቆይታ ለማድረግ መጥቻለሁ፡፡ ስለዚህ ለመው ለድ ስትቃረቡ ወደሆስፒታሉ ኑ..... በማለት እናቶች እርስ በእርሳቸው ይመካከራሉ፡፡ ይህም በስራችን አንድንበረታ ያደርገናል፡፡

የአጣጥ ሆስፒታል አላማ የእናቶችንና የጨቅላ ሕጻናትን ጤና መንከባከብ ነው፡፡ በውጤቱም ጤናማ ህብረተሰብን እናገኛለን፡፡በአገራችን በአሁኑ ወቅት የህጻናቱን ሞት መቀነስ መቻሉ በየአቅጣጫው እንደዚህ ያለ አገልግሎት በመሰጠቱ መሆኑ አያጠራ ጥርም፡፡

ወደእናቶች ማቆያው ስንመለስ ...አብስለው ከሚበሉበት ማብሰያ ክፍል ነበር የሄድነው፡፡ ድስት በአንድ ምድጃ ላይ...የቡና ጀበና በሌላው ምድጃ ተጥዶአል፡፡ እርጉዝ ሴቶች በቀስታ እንቅስቃሴ እያደረጉ የተለያየ ነገር ይሰራሉ፡፡ ስናነጋግራቸውም ...አሁን ከሚያገኙት አገልግሎት ባሻገር ህብረተሰቡን ማስተማር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

.. እኔ ስሜ ጊዜወርቅ ኪርጋ ይባላል፡፡ ወደ አጣጥ ሆስፒታል የመጣሁት ከቸሀ ወረዳ ነው፡፡ ከአሁን ቀደም ሁለት ልጆች አሉኝ፡፡ ከዚያም መከላከያ እየወሰድኩ ለአስር አመት ያህል ቆይቻለሁ፡፡ አሁን ግን ሳረግዝ ...እድሜዬ ገፍቶ ነው መሰል...አደከመኝ፡፡ ገና ከአምስተኛ ወሬ ጀምሮ ደም መፍሰስ የመሳሰለው ሲታይ ክትትል ጀመርኩ፡፡ እናም ለህክምና ወደዚህ ሆስፒታል ስመጣ የመውለጃ ጊዜሽን እዚሁ ሆነሽ ጠብቂ ተባልኩ፡፡ ስገባ የሰባት ወር እርጉዝ ነበርኩ፡፡ አሁን ግን መውለጃዬ ደርሶአል፡፡ ዛሬም ነገም ምን እሆናለሁ በሚል ጭንቀት ውስጥ ከምገባ በሚል እዚህ መጥቼ ቁጭ ብዬአለሁ፡፡ በሰበ ቡም እረፍት አድርጌአለሁ፡፡ በሆስፒታሉ የሚሰጠው አገልግሎት ...በተለይም እናቶችን በሆስፒታሉ ወር ሁለት ወር ቁጭ ብለው የመውለጃ ጊዜያቸውን እንዲጠብቁ መደረጉ... በጣም ትልቅ አገልግሎት ነው፡፡ እናቶች በየቤታቸው ምጥ ይዞአቸው...ደም እየፈሰሳ ቸው...የሽንት ውሀ በየመንገዱ እየፈሰሳቸውና ልጅ እየሞተባቸው...አንዳንዶች እናቶች እራሳቸውም እየሞቱ...አረ ስንት ጉዳት አየን...በየገጠሩ የሚጎዱ እናቶች ቤት ይቁጠ ራቸው፡፡ እኔ በበኩሌ ከዚህ በሁዋላ ልጄን ወልጄ ወደአገሬ ስመለስ ወጥቼ ህዝቡን አስተምራ ለሁ፡፡..

በስተመጨረሻ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርና የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሪታ ሽፋ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ምን ያህል አስተዋጽኦ አድርጋችሁዋል ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን መልስ ሰጥተዋል፡፡

.. ...የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ዋናው መስፈርት ቅድመ እርግዝናና ቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል ማድረግ ነው፡፡ እናቶች ለማርገዝ ሲያስቡና ማርገዛቸውን ሲያውቁ ወደሐኪም ዘንድ ቢቀርቡ እና ክትትል ቢያደርጉ እነሱም ጤናኛ ሆነው ጤነኛ ልጅም መውለድ ይችላሉ፡፡ እኛ ባለንበት አካባቢ ሁኔታ ደግሞ ሊሰጥ የሚገባው አገልግሎት ከዚህም በላይ መሆን አለበት ብለን ስለምናምን ነወ የእናቶችን ማቆያ ከ30/አመት ጀምሮ በመተግበር ላ ያለነው፡፡ ምክንያቱም እናቶች የሚገኙት በሆስፒታሉ ዙሪያ በሚገኙ ወረዳ ዎች ከ25/ እስከ 70/እና 80/ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚኖሩ እር ጉዞች በምጥ ወቅት ወደሆስፒታሉ ለመምጣት ይቸገራሉ፡፡ የመጉዋጉዋዣና የገንዘብ ችግር ስለሚገጥማቸው በቤታቸው በተራዘመ ምጥ ይሰቃያሉ፡፡ ውጤቱም ምናልባት አስከፊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም ነው ከርቀት የሚመጡት እናቶች በጤና ምክንያትም ይሁን በተለያየ ምክንያት ከዚህ ከማቆያው አረፍ ብለው የምጥ ጊዜአቸውን እንዲጠባበቁ የምናደርገው፡፡ በዚህ አገልግሎት የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ የበኩላችንን አስተዋ ጽኦ ማድረጋችንን አንጠራጠርም፡፡ ..

 

 

Read 2587 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:19