Print this page
Saturday, 16 June 2012 12:33

.....አንዲትም እርጉዝ ሴት እንዳታመልጠን.....

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ለዚህ እትም በርእስነት መግቢያ ያደረግነው የዶክተር ዮሐንስ ከተማን ንግግር ነው፡፡ ዶ/ር ዮሐንስ ከተማ በአሁኑ ወቅት በድሬደዋ ከተማ አርት ጄኔራል ሆስፒታል የሚሰሩ ሲሆን በሙያቸውም የጽንስና ማህጸን  ሕክምና እስፔሻሊስት ናቸው፡፡ አርት ጄኔራል ሆስፒታል የግል የህክምና ተቋም ሲሆን ዶ/ር ዮሐንስ በሆስፒታሉ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ክፍል ኃላፊ ናቸ ው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በአገሪቱ በተለያዩ መስተዳድሮች ከሚገኙ የግል የህክምና ተቋማት ጋር በመተባበር ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያግ ዘውን ፕሮጀክት ያከናውናል፡፡ በድሬደዋ የቃኘነው አርት ጄኔራል ሆስፒታል ከኢሶግ ጋር ከሚ ሰሩ የግል የህክምና ተቋማት አንዱ ነው፡፡ ዶ/ር ዮሐንስ በስራ አጋጣሚያቸው የታዘቡትንና ያለውን እውነታ አጋርተውናል፡፡

----------////-----------

ኢሶግ/ በድሬደዋ ለኤችአይቪ ቫይረስ ለመጋለጥ ምክንያት ይሆናሉ የሚባሉ የአኑዋኑዋር

ባህርይዎች ምን ይመስላሉ?

ዶ/ር በመሰረታዊው ነገር ይህ አካባቢ ከሌሎች የሚለይበት ምንም መገለጫ የለውም ፡፡

እንደማንኛውም የአለም ክፍል ኤችአይቪ ይተላለፍባቸዋል ተብሎ በሚታመንበት መን ገድ ቫይረሱ ይሰራጫል፡፡ ነገር ግን ቫይረሱ የሚሰራጭባቸውን መንገዶች በሚያባብስ ሁኔታ ኑሮን የመምራት ዘዴ ከአካባቢ አካባቢ እንደሚለያይ የታመነ ነው፡፡ ስለዚህም በምስራቁ የአገራችን ክፍል ድሬደዋን ጨምሮ ለከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ሴቱም ወን ዱም በስፋት ይንቀሳቀሳል፡፡ ሰዎች ለንግድ  በተንቀሳቀሱ ቁጥር ደግሞ ከቤተሰቡ ተለ ይቶ መዋል ማደር እንዲሁም ከተለያዩ ከማያውቁዋቸው ሰዎችጋር መገናኘት ከዚህም በተጨማሪ የአመጋገብ ፣የማረፊያ ሁኔታዎች የመሳሰሉት ሁሉ ለድንገተኛና ላልታሰበ ሁኔታ ሊያጋልጡ ስለሚችሉ ሰዎች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴያቸውን የባህርይ ለውጥ በማድረግ ካልተቆጣጠሩ ለበቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር እሙን ነው፡፡ ስለዚህ በድሬደዋ የኤችአይቪ ቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ በከፍተኛ ሁኔታ የባህርይ ለውጥን ለማምጣት የሚያስችል ትምህርት ለህብረተሰቡ መሰጠቱ መቀጠል ይኖር በታል፡፡

ኢሶግ/ ወደሆስፒታሉ ለምርመራ ከሚመጡ እርጉዝ ሴቶች መካከል ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩት

ከመቶ ምን ያህል ይሆናሉ ?

ዶ/ር  ለእርግዝና ክትትል ከሚመጡት እናቶች ይህን ያህል የሚሆኑት ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ

ናቸው ለማለት የሚያስችል ጥናት ስለሌለ ይህን መናገር ያስቸግራል፡፡ ነገር ግን ችግሩ መኖሩን በግልጽ የምናየው ነው፡፡ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ በመሆናቸው በቋሚነት የሕክ ምና ክትትል የምናደርግላቸው እናቶችም አሉ፡፡ በስፋት ብለን ባንገልጸውም ብዙ እናቶች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ በየእለቱ ከሚያጋጥሙን ታካሚዎች ሁኔታ መረዳት ይቻ ላል፡፡

ኢሶግ /ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ሆስፒታሉ ከተቋቋመ ጀምሮ ምን በመስራት

ላይ ነው?

ዶ/ር  ሆስፒታሉ በተቋቋመ ጊዜ የተሟሉ የሕክምና አገልግሎት መስጫዎች ስላልነበሩና

በወቅቱ እውቀቱም ቢሆን ውስን የነበረ በመሆኑ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተ ላለፍ ለማድረግ የተለየ ጥረት አልተደረገም፡፡ በአሁን ወቅት ግን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ሲሆን በተለይም የእኛ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ጋር በትብብር መስራት በመጀመሩ ደረጃ በደረጃ እያደገ መጥ ቶአል፡፡ የጀመርነው ከዜሮ ሲሆን አሁን ግን ሳይንሳዊ እድገቱን በመከተል በጣም የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡

ኢሶግ/ ምን ያህል ሕጻናትን ከቫይረሱ ነጻ ሆነው እንዲወለዱ አስችላችሁዋል?

ዶ/ር  ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚረዳው አሰራር ከሁለት አመት

በፊት ያልነበረ ሲሆን ባለሙያዎችም ትኩረት ሰጥተን አልሰራንምለ፡፡ በዚያ ጊዜ የተከሰተው ችግር ብዙ ኪሳራ አድርሶአል ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የህክምና ባለሙያዎቹ የሙያ ስልጠና እየወሰዱ እንዲሁም ለምርመራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ለሆስፒታሉ ምቹ ከመደረጋቸውም በላይ መድሀኒቱ ለሕብረተሰቡ በመስጠት ላይ ስለሆነ ለወደፊቱ ጥሩ ውጤት እንደምናገኝ አንጠራጠርም፡፡ ለጊዜውም ቢሆን ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የሚወለዱ ሕጻናት በተቻለ መጠን ከቫይረሱ ነጻ ሆነው እንዲወለዱ አስፈላጊውን ክትትል እያደረግን ነው፡፡

ኢሶግ/ በቫይረሱ ከተያዙ እናቶች የሚወለዱ ልጆችን ነጻ መሆን አለመሆን ለማረጋገጥ

የሚደረገውን  ክትትል በሚመለከት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ምን ይመስላል?

ዶ/ር  በድሬደዋ እያንዳንዱ ሰው በአቅራቢያው የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት

እንደሚገኙ እርግጥ ቢሆንም ወደሆስፒታል ሄዶ ጤናውን የመከታተል ነገርን በሚመለከት ግን ችግር አለ፡፡ በድሬደዋ ሆስፒታሎች በእያንዳንዱ ሰው ደጃፍ ይገኛሉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ አገልግሎት ቢሰጡም ዛሬም በቤታቸው ልጅ የሚወልዱ እናቶች ብዙ ናቸው፡፡ እናቶች በእርግዝና ጊዜ የሚያደርጉት ክትትልም ምናልባት ጎላ ካለ የጤና ሁኔታ ጋር በተያያዘ አንዴ ወይንም ሁለ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ እናቶች የወለዱዋቸው ልጆች ምን ያህል ከቫይረሱ ነጻ ናቸው የሚለውን ለማወቅ የሚያስችለውን ተከታታይ የህክምና ክትትል የማድረጉን ነገር ብዙዎች አይፈ ጽሙትም ፡፡ የሐኪምን የምክር አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግ ክትትሉን የሚያደርጉ ጥቂቶች ናቸው፡፡

ኢሶግ/ባሎች ሚስቶቻቸው ለምርመራ ወደ ሐኪም ዘንድ ሲቀርቡ አብረው የመቅረብ ሁኔታ

በድሬደዋ ምን ይመስላል?

ዶ/ር ባሎች ብዙ ጊዜ ከሚስቶቻቸው ጋር ወደ ሆስፒታል አይሄዱም፡፡ እንኩዋንስ ለክትትል

በሚመጡበት ጊዜ ለመውለድ እንኩዋን ሲመጡ ታጅበው የሚመጡት በጎረቤት በዘመድ አዝማድ ነው፡፡ ባል በአገር ውስጥ ካለ መገኘት ያለበት በምጥ ቀን ቢሆንም ነገር ግን ሴትየዋ ለመውለድ ተዘጋጅታ... ለኦፕራሲዮን ቀርባ... ባለቀ ሰአት ...ካለበት ተፈልጎ የመምጣት ነገር በተደጋጋሚ ያጋጥማል ፡፡፡ በወሊድ ወቅት በሴትየዋ ሕይወት ላይ ለመወሰን በጎረቤት በዘመድ አዝማድ አስተያየቶች በመጨናነቅ ሐኪም የሚሰጠውን ምክር ላለመቀበል ስለሚታገሉ ችግር ይፈጠራል፡፡ ነገር ግን ባልተቤትየው በትክክለኛው ሰአት ቢገኝ ኖሮ ሁሉም ነገር ቀላል ይሆናል፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎ የሚስቶቻቸውን ሁኔታ ለመከታተል በጊዜው የሚቀርቡ ባሎች መኖራቸውን አንክድም፡፡ በእርግጥ በአ ሁኑ ወቅት ብዙ እየተሻሻሉ የመጡ ነገሮችን በማየት ላይ ነን፡፡ ቀደም ሲል ..እኔ በቫይረሱ ልያዝ አልችልም፡፡ እኔ ከአመጋገቤ ከአኑዋኑዋሬ የተነሳ ቫይረሱ አይደፍረኝም፡፡ ስለዚህ መመርመር አልፈልግም.. የሚለው ስሜት ዛሬ ተለውጦ ..ምን ይታወቃል ?እኔም ከሚስ ጋር አብሬ ልመርመርና ቫይረሱ ከተገኘብን አብረን መፍትሔውን እናበጃለን.. የሚሉ ሰዎች እየታዩ ነው፡፡ ስለዚህ ወደፊት የሚሆነውን ስናስብ የተሻለ ነገር እንጠ ብቃለን፡፡ ነገሮችን ካልነበረ ወደነበረ ማምጣት አስፈላጊ በመሆኑም እኛም በጥንካሬ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

ኢሶግ/ በድሬደዋ የኤችአይቪ ስርጭትን በመግታቱ ረገድ አስቸጋሪ የሚባል ነገር ምንድነው?

ዶ/ር ኤችአይቪን በመግታቱ ረገድ እንደሌሎች የአገራችን ክፍሎች የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም

በድሬደዋ ትልቁ አስቸጋሪ ነገር ልማድ ወይንም የአኑዋኑዋር ባህርይ ነው ማለት እንች ላለን፡፡ ከውጭ ሀገር ወደ ቤተሰቦቻቸው ለጉብኝት የመጡ ሕጻናትን ወንዱንም ሴቱንም ከወላጆቻቸው ፈቃድ ውጭ የሚያስገርዙ ጎረቤቶች... ቤተሰቦች ...ያሉበት ነው ድሬደዋ፡፡ ለምሳሌ... ሰዎች በኦፕራሲዮን ወልደው ከሐኪሙ ተገቢው ምክር ተሰጥቶአቸው ከሄዱ በሁዋላ በጎረቤት እና በአካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ምክር በመቀበል ከጉዳት ላይ ወድቀው እንደገና ለህክምና የሚመለሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በግልጽ በሕክምና ባለሙ ያው የተነገረውን ምክር ሐኪሙ ምንም አያውቅም በሚል ያገባናል ባዮች በሚሰጡት ምክር ከጉዳት የሚወድቁ ታካሚዎችን ማየት ለባለሙያው የሚጸጽት ነው፡፡ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይሰራጭም ሆነ አስፈላጊውን ክትትል ለማድረግ እንዳይቻል ማነቆ የሚሆ ኑት ልምዶች ቀስ በቀስ እየተቀረፉ መሄድ እንዳለባቸው አያጠያይቅም፡፡

ኤችአይቪን በሚመለከት ልክ ምግብን በተለያየ ሰአት ሳናቋርጥ እንደምንመገበው ሁሉ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን መረጃን እያገኘን ነው፡፡ በእርግጥ አሁንም የባህርይ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ መረጃው መቋረጥ እንደሌለበት አምናለሁ፡፡ ከእናት ወደልጅ የሚተላለፈውን የቫይረስ ስር ጭት ለመግታት በምናደርገው ጥረት ቢቻል ኤችአይቪ እናቶቸን እንዳይይዝ ማድረግ ...ያ ሳይ ቻል ሲቀር ደግሞ ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የሚወለዱ ሕጻናትን በቫይረሱ እንዳይያዙ ለማድረግ ለራሳችን ቃል የገባንበትን ...አንዲትም እርጉዝ ሴት እንዳታመልጠን... የሚለውን በተ ግባር በማዋል እናትየውንና ጽንሱን በተገቢው መንገድ በመንከባከብ ቀጣዩን ትውልድ ከቫይ ረሱ ነጻ ሆኖ እንዲወለድ የሚያስችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡

 

 

Read 5238 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 12:37