Print this page
Saturday, 18 August 2012 13:10

ሽንት የመሽናት ችግር...ከስነ ተዋልዶ ጤና ጋር ይገናኛልን?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(4 votes)

በሽንት መሽናት ችግር ላይ የተወሰኑ መልእክቶችን ተቀብለናል። መልእክቶቹ የደረሱን ትዳር ካልያዙት መካከል እንዲሁም የልጆች እናት ከሆኑትም ጭምር ነው። ለመሆኑ ሴቶች የሚገጥማቸው ሽንትን በትክክል ያለመሽናት ሕመም ከስነተዋልዶ አካል ጤንነት ጋር ይገናኛልን? የሚል ጥያቄ አስነስቶአል። ይህንን ጥያቄ ወደሕክምና ባለሙያ አቅርበ ነዋል። ዶክተር ደረጄ አለማየሁ በጋንዲ የአናቶች ማዋለጃ ሆስፒታል የሜዲከል ዳይሬክተር አንዲሁም የጽንስና የማህጸን ህከምና ሰፔቫሊሰት ናቸው። ሴቶች የሚገጥማቸው የሽንት መሽናት ችግር መንስኤ ምን እንደሆነና ከስነ ተዋልዶ ጤና ጋር የሚኖረውን ግንኙነት አብራርተዋል።

ኢሶግ፡  የሴቶች ሽንት መሽኛ አካል ከስነተዋልዶ አካል ጋር ይገናኛልን?

ዶ/ር፡   የሽንት መፈጠሪያው አካል ኩላሊት ነው። ከዚያ በሁዋላ የሽንት መጠራቀም አለ።ሽንት ወደ ፊኛ ከተላለፈ በሁዋላ ከሰውነት እንዲወገድ ይሆናል። እናም በዚያ አካባቢ ያሉ የስነተዋልዶ አካላትን እና የሽንት መሽኛ  አካላትን አፈጣጠር ስናይ ከመጀመሪያ መነሻቸው ከአንድ አከባቢ ነው። ነገር ግን አፈጣጠራቸው ከአንድ አይነት ስትራክቸር ይሁን እንጂ ተግባራቸውን ስንመለከት ግን ሙሉ በሙሉ የተለያዩ አከላት ናቸው። አንዱ ላንዱ በጣም ተቀራራቢ የሆኑ በመሀከላቸው ምንም ነገር ሳይኖር አንዱ አንዱን አየከለለ የሚገኙ ናቸው። አናቶሚ የሚባለውን የተፈጥሮ አወቃቀር ስናይ... ለምሳሌ በማህጸን ዩትረስ የሚባል አካል አለ። ይሄ ዩትረስ የሚባለው ክፍል ልጅ የሚያድግበት ቦታ ሲሆን የሽንት ፊኛ የሚገኘው ከዚያ ስር ነው። ዩሪተር የሚባለው የቨንት ማስተላለ ፊያ ቱቦም የሚያልፈው አሁንም በማህጸን ስር ነው። ከዚያ በሁዋላ ደግሞ ፊኛ አለ። ፊኛ የሚገኘው ከማህጸን ስርና ከሴት ብልት በላይኛው አካል በኩል ነው። በመሃከላቸው ግን ሁለቱንም የሚለይ ሌላ አካል አለ። ከዚያ በሁዋላ ቨንት ሲሸና ከሰውነት የሚወጣ ውም ከላይ በኩል በሴትየዋ ብልት በውጭኛው ከንፈሮች መካከል ከፍ ብሎ በሚገኘው ትንሽዬ ቀዳዳ አማካኝነት ነው። ስለዚህ የሴቶች የሽንት መሽኛ አካልና የስነተዋልዶ አካል ያላቸው ግንኙነት በወሰን ወይንም በድንበር አማካኝነት እንጂ በቀጥታ በመስመር በመሳሰለው መንገድ አይደለም።

ኢሶግ፡  ከደረሱን ደብዳቤዎች መካከል የአንድዋ ወጣት እንዲህ ይነበባል። ..እኔ ልጅ ነኝ ገና አላገባሁም...አልወለድኩም። ነገር ግን ሽንት የመቆጣጠር ችግር አንዳንድ ጊዜ ይገጥመኛል። አንዳንድ ጊዜ ቀላል እና የተለመዱ የመከላከያ መድ ሀኒቶችን አየወሰድኩኝ እድን ነበር። አሁን አሁን ግን ከበድ ወዳለ ነገር እየመጣ አስቸገረኝ። .. ይላል የደብዳቤው ሀሳብ።

ዶ/ር፡  አንግዲህ ሽንት መሽናት በተለይ ይሄ መጣሁ ይልና ሲፈስ የማስጨነቅ ፣ቶሎ ቶሎ የመምጣት እና የማስቸገር ፣የመዘግየት፣ የማጣደፍ ...እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች የቨንት ፊኛ ኢንፌክቨኖች ናቸው። ይህ በማንኛዋም ...ማለትም... ባገባችም ሆነ ባላገባችም ሴት ላይ ሊከ ሰት ይችላል። በእርግጥ ባገቡት ላይ ወይንም በእርጉዞች ፣ብዙ በወለዱት ላይ የህመም መጠኑ ሊጨምር ይችላል። ከላይ ጥያቄ ያቀረበችውን ልጅ ሁኔታ ስንመለከት ግን ከማህጸን ፣ከመራቢያ አካል ወይንም ከስነ ተዋልዶ አካል ጋር ይገናኛል የምንለው ነገር የለም። ስለዚህ ያንን የሽንት መስመሩን ተከትሎ የተፈጠረ ኢንፌክቨን ወይም ደግሞ ዩትራ የሚባለው የሽንት መውጪያ ቱቦ ኢንፍክቨን ሊሆን ይችላል።የዚህች ልጅ ችግር በቀላሉ ሕክምና በማግኘት መዳን የሚችል ነው። እንደዚህ ያለ የሽንት መሽናት ችግር የሚገጥማቸው ሴቶች የሽንት ከልቸር በማሰራት በቀላሉ ውጤ ቱን ለማወቅ ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ  የታመመችው ልጅ አድሜዋ በጣም ትንቨ ከሆነ ምናልባት አፈጣጠር ላይ ያልተስተካከለ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ይህም ችላ የሚባል ሳይሆን በሐኪም መታትየ ያለበት ነው። የሽንት መፈጠሪያው ፣መከማቻውና ፣ መው ጫው አካል አፈጣጣር በትክክል መሆን ያለመሆኑን  በአልትራ ሳውንድ በመታየት ችግር መኖር ያለመኖሩ ይታወቃል። ሌሎችም የተለያዩ የምርመራ ተክኒኮች ስለአሉ ወላጆች እንደዚህ ያለ ችግር በልጆቻቸው ላይ ሲመለከቱ በፍጥነት ወደሕክምና ተቋም ሊወስዱዋቸው ይገባል።

ኢሶግ፡  ከደረሱን ጥያቄዎች መካከል ተከታዩ እንዲህ ይላል።

.. የሁለት ልጆች አናት ነኝ። የሽንት መሽናት ችግር አንደህመም አየሆነ አየተመላለሰ ያስቸግረኛል። ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ የተነሳሁት ሕመሙ እራሴን አስከምስት ድረስ ...ደም ጭምር አስከምሸና አድርሶኝ ሆስፒታል ካደርኩ በሁዋላ ነው። በእለቱ  ሀኪሞችም ከሽንቱ ጋር በሚፈሰው ደም  ግራ ተጋብተው እንደነበር እና ምናልባትም ደሙ ከማህጸን የሚፈስ ሊሆን ይችላል ብለው ገምተው እንደነበር መግለጽ እፈልጋለሁ። ይህ ሕመም ከማህጸን ጋር የሚገናኝበት መንገድ ይኖር ይሆን ?..

ዶ/ር፡   የዚህችኛዋ ሴት ችግር ሽንትዋ ደም አስከሚመስል ያደረሳት እና ከበድ ያለ ነው።

እንደዚህ ያለ ነገር ሲከሰት ብዙ ነገር ማሰብ ያስፈልጋል። በመጀመሪም ከኩላሊት ወይንም የሽንት ፊኛ እንዲሁም ከሽንት ቡዋንቡዋ ጋር በተያያዘ ሕመሙን መፈተሸ ያስፈልጋል። በተለይም የኩላሊት ጠጠር በግልጽ በማይታይበት ሁኔታ ሊኖርና አንድ ቦታ ተቀርቅሮ ችግር ሊያስከትል የሚችል ሲሆን ሕመሙም እራስን እስከመሳት የሚያደርስ ነው። ጠያቂዋ እንደገለጸችውም ከሽንት ጋር ደም ተቀላቅሎ የመፍሰስ ሁኔታ ሊስተዋል ይችላል።ምናልባትም ሕክምና አድርጌአለሁ የሚል መተማመን ሊኖርና ችላ የሚባል ነገር ካለ ታማሚዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ነገር አንዳንድ ጊዜ ጠጠሩ በአል ትራ ሳውንድም የማይታይበት አጋጣሚ እንደሚኖር ነው። ሌላው አንዳንድ ጊዜ ኢንፌ ክሽንም ከሽንት ጋር ደም አስከ መፍሰስ ሊያደርስ ይችላል። ከዚህ ውጭ ግን ከመው ለድ ጋር የተገናኘ ችግር በሚሆንበት ጊዜ በዚያው በወለደችበት ሳምንት ...ማለትም በአ ንድ ወይንም በሁለት ሶስት ሳምንት ውስጥ ችግሩ ይስተዋላል።

ኢሶግ፡  በሴቶች ላይ የሚከሰተው ሽንትን በትክክል ያለመሽናት ችግር ከእርግዘና ወይንም ከመውለድ ጋር የሚያያዝበት አጋጣሚ አለ?

ዶ/ር፡ ሽንት የመሽናት ችግር ከአርግዝና ወይም ከመውለድ ጋር የሚገናኝበት መንገድ አለ። ልጅ ከማህጸን በሚወጣት ወቅት የልጁ ጭንቅላት የቨንት ፊኛውን እና የቨንት መውጫ ቡዋንብዋውን የመጫን ኃይል አለው።በተለይም ረጅም ምጥ ከሆነ አንዳንድ ሴቶች ላይ ፌስቱላ የሚባል የጤና ችግር ያስከትላል። ሴትየዋ የህክምና እርዳታ ሳታገኝ ለቀናት የምታምጥ ከሆነ  በሴት ብልትና በማህጸን ግድግዳ መካከል ያለው ክፍል ይቀደድና ሽንት በማህጸን በኩል መፍሰስ ይጀምራል። ሌላው ደግሞ ሴትየዋ ሳል በሳለች፣ ባስነ ጠሰች ወይንም በሳቀች ቁጥር ሽንት የሚያመልጣት ከሆነ የዚህ ምክንያቱ ብዙ ከመ ውለድ የተነሳ በማህጸን ፣በሽንት ፊኛና ፣በሽንት ቱቦ መሀከል ያለው የተፈጥሮ አካል የመዛባት ችግር ደርሶበት ሊሆን ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ከፊኛው አንገት ላይ ያለው  ጡንቻ ሽንትን አዚያው አፍኖ የሚያስቀር ሲሆን ሴትየዋ ሽንት መሽናት በፈ ለገች ወቅት ብቻ መሽናት ሲኖርባት ያ አንግል ብዙ በመውለድ ምክንያት ቢበላሽና ቢደክም ሽንትን የመቆጣጠር ችግር ያስከትላል። በእርግዝና ወይንም በመውለድ ምክ ንያት በሴትየዋ ላይ የተከሰተው ሽንትን በትክክለኛው መንገድ መሽናት ያለመቻል ችግር ፌስቱላም ሆነ አልሆነ እውቀቱ ባላቸው የህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት ሊታከም የሚችል ነው።

ኢሶግ፡  ሴቶች ሽንትን የመቆጣጠር ችግር ሲደርስባቸው ወደሕክምናው የመምጣት ልምዳቸው

ምን ይመስላል?

ዶ/ር፡  በጣም የሚገርመው ነገር ብዙዎች ችግሩን በጊዜው ተናግረው መፍትሔ አለማግኘታቸው ነው። በእርግጥ አልፎ አልፎ ለሕክምና የሚመጡ አሉ። ሴቶች አድሜያቸው ከ45 ፣50 እና 60 ዓመት በላይ ሲሆን ሽንት ያለመቆጣጠር ወይንም ሽንት የማምለጥ ሁኔታ በጣም አየጨመረ ሊመጣ የሚችል ነው። ስለዚህ ብዙ እናቶች ህክምና መኖሩንም ስለማያውቁ ይጎዳሉ። ብዙ ዎቹ ሴቶች ሕመሙ ሲያጋጥማቸው የሚወስዱትን ፈሳቨ አየቀነሱ ፣ ሽንት አንዳይ መጣባቸው አየተጠነቀቁ መኖር ይጀምራሉ። ስለዚህ የአብዛኞቹ ሴቶች ሕመም ወደሕክምና ተቋም ሪፖርት አይደረግም ማለት ይቻላል።

ኢሶግ፡  በመውለድ ምክንያት የሽንት መሽናት ችግር የደረሰባቸው ሴቶች ለራሳቸው ሊሰጡ የሚችሉት እርዳታ አለ?

ዶ/ር፡  ሁለት አይነት ነገር አለ። አንደኛው ኤክሰርሳይስ ወይንም እስፖርት መስራት ነው።

በማህጸን ...ወይንም የሽንት ፊኛእንዲሁም በብልት ያሉ አካባቢ ጡንቻዎችን ለማጠንከር በተቀመ ጡበት ወይንም ቆመውም ቢሆን ጭብጥ ኩርምት እያደረጉ ገላን የማጠንከር ስፖርት በመስራት ጡንቻዎች አንዲጠነክሩ ማድረግ ይቻላል። ሌላው ደግሞ ሕመሙ እን ደተሰማት ወደክሕምና ተቋም በመሄድ ችግሩ ሳይሰፋ ሕክምና ማድረግ እራስን ከበሽታ ለመከላከል አንዱና ዋነኛው መንገድ ነው።

 

 

Read 11863 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 13:20