Sunday, 31 July 2011 13:41

የሞባይል ስልኮች በሰዎች ላይ አዲስ አመል እየፈጠሩ ነው

Written by  ዮናስ ብርሐኔ
Rate this item
(0 votes)

በርካታ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የምንችልባቸው የተራቀቁ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ብዛት ያላቸው ሰዎች በኑሯቸው ውስጥ እለት ተእለት ለሚያከናውኗቸው እንቅስቃሴዎች በጣም ወሳኝ እንደሆኑ የሚነገር ሲሆን በሞባይል ስልክ አጠቃቀም ዙሪያ በቅርቡ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች በበኩላቸው ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት መግለጫ እንደ¸ያመለክተው፤ እነዚህ ዘመናዊ ስልኮች የሰዎችን ህይወትና ጊዜም እየተሻሙ ይገኛሉ፡፡ ጥናቱን ያደረጉት የሄልሲንኪ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ተጠቃሚዎች ኢሜላቸውን፣ ዜናዎችን እና ሌሎች መልዕክቶችን በሞባይል ስልኮቻቸው ላይ አዘውትረው ቶሎ ቶሎ ከመመልከት ጋር ተያይዞ አዳዲስ ልማዶች እያዳበሩ ሲሆን ሳይንቲስቶቹ ይህንን ሁኔታ ..ቼኪንግ ሃቢት.. (checking habits) ብለውታል፡፡

ጥናቱን በበላይነት የመሩት ተመራማሪ እንዳሉት፤ ሰዎች እንደልማድ ሆኖባቸው ሞባይሎቻቸውን እያነሱ በተደጋጋሚ መጐርጐራቸው ወደ አመልነት እየተለወጠ የሚሄድበት ሁኔታ ያለ ሲሆን አንድ ነገር ለማየት ስልካችንን በምንከፍትበት ጊዜም ሳናስበው ሌላ ነገር ውስጥ ጠልፈው በመክተት በዚያ ተመስጠን ያሰብነውን ነገር እንዳናደርግ ወይም በዙሪያችን ያለውን ሁኔታ እንዳናስተውል እክል እየሆኑብን ይገኛሉ፡፡ ሰዎች አንድ ነገር ለማየት ስልካቸውን ከከፈቱ በኋላ ሳያስበት በሌላ ነገር ይጠመዱና በዚያው ተመስጠው ይቀራሉ፡፡ የስልክ ቁጥሮችን ለማውጣት ፈልገን የሞባይላችንን ..ኮንታክት.. ስንከፍት ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን ከሚያቀብል አፕሊኬሽን ጋር ተጣምሮ በሚገኝበት ሁኔታ በተደረገው በዚህ ጥናት ላይ በብዛት የተስተዋለውም ሰዎች በዚያው ሌላ ነገር ወደ ማየት እንደሚሸጋገሩ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተመራማሪዎቹ የታዘቡት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ከምናዘወትረው አንድ አፕሊኬሽን ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሌላ ተዛማጅ አመልም እንዳለ ነው፡ ያሉትን ነገሮች ያጤኑት ተመራማሪዎቹ፤ በመጨረሻም ከዘመናዊ ሞባይሎች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ልማዶች የሚያስከትሉት አዎንታዊ እና አሉታዊ ነገሮች እንዳሉ ያስቀመጡ ሲሆን ሰዎችን የሚስቡ ሌሎች አፕሊኬሽኖች በሞባይል ስልኮች ላይ በቀላሉ ተደራሽ እየሆኑ መምጣት ደግሞ የበለጠ ጊዜ የሚሻሙበትን ሁኔታ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡ በጥቅሉ የሞባይል ስልኮች በጣም እየተራቀቁና የሰዎችን ቀልብ የሚስቡ የተለያዩ አጓጊ አፕሊኬሽኖችN እያካተቱ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት የተደረጉ ሌሎች ጥናቶች ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለትራፊክ አደጋዎች መብዛት እንደምክንያት ያስቀመጡ ሲሆን አሁን ግን የሰዎችን ጊዜም እየተሻሙ እንደሆነ አዲሱ ጥናት አመልክቷል፡፡

Read 2105 times