Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:36

ገመድ አልባ ስፒከር ለገበያ ቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሶኖስ.. የተራቀቀ እና በአይነቱ የተለየ አዲስ ገመድ አልባ ስፒከር ሰርቶ ለገበያ ማቅረቡ ተገለ፡፡ በአዲሱ የሶኖስ |Pl¤Y: 3.. (Play: 3) ገመድ አልባ ስፒከሮች አንድ ዘፈን በሁሉም የመኖሪያ ቤት ክፍሎቻችን ውስጥ ማጫወት የምንችል ሲሆን በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የተለያዩ ሙዚቃዎችን መክፈትም እንችላለን፡፡

የሶኖስ ሙዚቃ ማጫወቻዎች ያለ ገመድ በርቀት የሚገናኙበት ..ኔትዎርክ.. ያላቸው በመሆኑ ማንኛውም ቦታ ሰክተን ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሲዲ ሆነ አይፖድ ከማናቸውንም አይነት የሙዚቃ ማጫወቻዎች ጋር አገናኝተን መጠቀም የምንችል ሲሆን ሁሉንም ሲስተም ከርቀት ሆነን በገመድ አልባው መቆጣጠሪያ አማካኝነት ማዘዝ እንችላለን፡፡
በኢንተርኔት ከሚሰራጩ የሬድዮ ፕሮግራሞች ጋር አገናኝተንም ሙዚቃ ልንሰማበትና የራሳችንን የዘፈን ማጠራቀሚያ ላይብረሪም መፍጠር የምንችል ሲሆን ዋጋው 999 ዶላር (17,000 ብር ገደማ) እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 2501 times