Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:39

|3D´ ሞባይል ስልክ መጣ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ምስሎችን በእውኑ እንደምናያቸው አድርገው የሚያሳዩን 3D´ ቴሌቪዥኖች ተሰርተው ለመጀመሪያ ጊዜ ገበያ ላይ ከወጡ ከአንድ ዓመት በኋላ ..ኤልጂ.. የመጀመሪያውን3D´ ሞባይል ስልክ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ነገሮችን ልክ በውኑ እንደምናያቸው ከሦስት አቅጣጫ መመልከት የምንችልብት 3D´ ቴሌቪዥን ሲነሳ ምስሉን ለመመልከት ማድረግ ያለብን መነጽር እንዳለ ይታወቃል፡፡

ለአዲሱ3D´ ሞባይል ታዲያ ..መነጽር ማድረግ ሊኖርብን ነው?.. የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን አዲሱ የኤልጂ  ..ኦፕቲመስ 3D´ ሞባይል የሚፈለገውን እይታ ለማምጣት መነጽር አይጠይቅም፡፡  
አዲሱ ሞባይል ያለ 3D´ መነጽር ነገሮችን ከሦስቱም አቅጣጫ ማየት የምንችልበትን ሁኔታ የሚፈጥርብን የምናይበትን አንግል አቀነባብሮ በማቅረብ ሲሆን በዚህ ስልክ ላይ በአንድ ጊዜ ምስሎችን በ |3D´ ማየት የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በ3D´ ቪዲዮ ምስሎችን መቅረጽ የምንችልበት ባለ አምስት ሜጋ ፒክስል ካሜራም አለው፡፡ በዚህ መንገድ የቀረጽነውን ቪዲዮ ከ3D´ ቴሌቪዥን ጋር አገናኝተን ማየት የምንችል ሲሆን y|3D´ ፊልሞችንም ቀድተን ልንመለከትበት እንችላለን፡፡ 4.3 ኢንች ስክሪን ስፋት ያለው |3D´ ሞባይል ዋጋው 799 (13,600 ብር ገደማ) ዶላር እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

Read 5331 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:42