በ2003 ዓ.ም ጥበብ በደንብ አድጓል፡፡ በሞያው ስላደረኩት አስተዋጽኦ ከእኔ ይልቅ ሰው ቢናገረው ይሻላል፡፡ በአጠቃላይ በርካታ ሥራዎች በመሠራታቸው ግን ማደጉን እያየን ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ስኬታማ የሆንበትን ጥሩ የቴሌቪዥን ድራማ ሠርተናል፡፡ እየሠራንም ነው፡፡በዓመቱ አስቸጋሪ የምለው የኑሮ ውድነቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በ2004 ዓ.ም ሠላም የሠፈነባት፤ ኑሮ ተስተካክሎ ከሠላም ጋር የምናያት ኢትዮጵያ እንድትሆን እመኛለሁ፡፡
ሙሉአለም ታደሰ
የማስታወቂያ ባለሙያ እና ተዋናይ
Published in
የሰሞኑ አጀንዳ