Saturday, 03 November 2012 13:02

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ራሷን ሰቅላ ተገኘች

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(5 votes)

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የማኔጅመንት ተማሪ የነበረችው አቡኔ ጌታሁን አለምነህ ትናንት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ በዶርሟ ውስጥ ራስዋን ሰቅላ እንደተገኘች ፖሊስ ጠቆመ፡፡የሃያ አንድ ዓመቷ ተማሪ አቡኔ፤ ጓደኞችዋ ወደ ክፍል ሲገቡ ‹‹ራሴን አሞኛል›› ብላ ስድስት ሆነው የሚያድሩበት ዶርም ትቀራለች፡፡ በዕለቱ ፈተና ቢኖራቸውም እሷ ወደ ክፍል ለመግባት አልፈለገችም፡፡ ጓደኞቿ ከፈተና በኋላ ወደ ዶርም ሲመለሱ በሩ ተቆልፎ ነበር፡፡ በመስኮት ወደ ክፍላቸው ሲያዩም ተማሪ አቡኔ በገመድ ሰቅላ ተመለከቱ፡፡ ወዲያው ፖሊስ ሲደርስም ህይወቷ አልፎ እንደነበር ታውቋል፡፡ ተማሪ አቡኔ፤ ባለፈው ዓመት ከአዊ ዞን ሽኩዳድ ወረዳ በመምጣት ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የገባች ሲሆን፤ የሞቷ መንስዔ ምን እንደሆነ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡

Read 9205 times