Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 13:48

የቁርስ እወጃ በአሜሪካን ኤምባሲ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አንድ የሕዝብ አስተያየት አሰባሳቢ ባለሙያ እንደተናገረው “የሕዝብ አስተያየቶች ዕጩዎች የሚያዩትንና ሕዝቡ የሚሰማውን ስሜት ማለትም እርካታን፣ ጥላቻን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ መተማመንን በሳይሳዊ ዘዴ ያሳያሉ፡፡” ብሏል፡፡  ***እያንዳንዱ የምክር ቤት መቀመጫ የራሱ የሆነ ጂኦግራፊያዊ አካባቢን የሚወክል ሲሆን እያንዳንዱ አባልም ብቸኛው የአካባቢው ተወካይ ሆኖ በብዙ (Plural) ድምጽ የሚመረጥ ነው፡፡ 50ዎቹ ግዛቶች እያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ የምክር ቤት ወንበር ይኖራቸዋል፤ ቀሪው ወንበር በሕዝብ ብዛት መጠን ለየግዛቱ ይመደባል፡፡ለምሳሌ በአላስካ ግዛት የሕዝቡ ብዛት አነስተኛ በመሆኑ በምክር ቤቱ ያለው ተወካይ አንድ ብቻ ነው፡፡ በአንጻሩ የካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ይለው በመሆኑ በምክር ቤት 53 መቀመጫዎች አሉት፡፡ በየአስር ዓመቱ የሚካሄደውን የሕዝብ ቆጠራ ተከትሎ በሚኖረው የሕዝብ ብዛት ለውጥ መነሻነት ለየግዛቱ የተመደበው የምክር ቤት ወንበር በድጋሚ ይሰላል፡፡

***አንድ መራጭ ለፕሬዚዳንትነት የራሱን ፓርቲ ዕጩ፤ ለኮንግረስ አባልነት ደግሞ  የሌላኛውን ፓርቲ ዕጩ ሊመርጥ ይችላል፡፡ ***የሕዝብ አስተያየቶች ሁልጊዜም የሚያሳዩት አብዛኛው ሕዝብ ፓርቲዎች አንዳንዴ ጉዳዮችን ከማብራራት ይበልጥ ሕዝብን በማደናገር ላይ ያተኩራሉ የሚል እምነት አለው፡፡ በመሆኑም በዕጩዎች ዝርዝር ላይ የፓርቲ ምልክት ባይኖር ይሻላል ይላሉ፡፡ ዘመናዊ አሜሪካውያን የፓርቲ መሳሪያዎቻቸውን ያልተገደበ የመንግስት ስልጣን የሚመለከቱት በጥርጣሬ ነው፡፡ የኮንግረስና የግዛት ዕጩዎችን በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ስርዓት መሰየም መጀመሩና ዕድገቱም በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ጸረ ፓርቲ ስሜት ያመለክታል፡፡ በአሜሪካ ፖለቲካ የቆየና የተደራጀ የፓርቲ ወገንተኝነት ታሪክ ቢኖርም እየጨመሪ የመጣው የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያለማመን ዝንባሌ የአሜሪካ ሲቪክ ባህል ዋነኛ አካል ነው፡፡ ***በርዕዮተ ዓለም ረገድ ተለማጭ ከመሆን በተጨማሪ ሁለቱ ዓበይት የአሜሪካ ፓርቲዎች ባልተማከለ መዋቅራቸውም ይታወቃሉ፡፡ … ከፕሬዚዳንቱ ጋር ተመሳሳይ ፓርቲ ቢሆኑም እንኳ ከፕሬዚዳንቱ ተቃራኒ የሆነ የፖሊሲ አቅጣጫ ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ ***ትነት መብቶችና ግለሰባዊ ሃብት ማካበት ትልቅ ትኩር ስለሚሰጡ እንደ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ይታያሉ፡፡ ዴሞክራቶቹ ደግም ግራ ዘመም በመሆን ሊበራል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን ይደግፋሉ፡፡ ስልጣን ሲይዙ ግን ሁለቱም ፓርቲዎች በተግባር ላይ የተመሰረተ (ፕራግማቲክ) ፖሊሲን ይከተላሉ፡፡ ***በዩናይትድ ስቴስት የሪፐብሊካኑና የዴሞክራቱ ፓርቲ ዕጩ ማን መሆን እንዳለበት የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጡት መራጮች ናቸው፡፡ ***በዓለም ካሉ የዲሞክራሲ ስርዓቶች ሁሉ የአሜሪካው የሚለየው ለፕሬዚዳንትነት፣  ለኮንግረስ አባልነትና ለግዛት ስልጣኖች የሚወዳደሩ የፓርቲ ዕጩዎች የሚወከሉት በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች በኩል መሆኑ ነው፡፡ ***ታዲያ ከሁለት ይልቅ ለምን ሶስት በቂ የፋናይንስ አቅም ያላቸው ብሔራዊ ፓርቲዎች እንዲኖሩ አልተደረገም? ለዚህ ምክንያቱ በከፊል ሁለት ፓርቲዎች ለመራጮች በቂ አማራጭ ይሰጣሉ ተብሎ ስለሚታመን፤ በከፊል አሜሪካውያን በታሪካቸው ፖለቲካዊ ጽንፈኝነትን የማይቀበሉ መሆናቸውና በከፊል ደግሞ ሁለቱም ፓርቲዎች አዳዲስ ሃሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ነው፡፡ ***ለአነስተኛ ከተሞች ስልጣን የሚወዳደሩ ዕጩዎች የትኛውንም ፓርቲ ሳይወክሉ የአካባቢ ልማትን ወይም የትምህርት ቤት ግንባታን የመሳሰሉ ጉዳዮችን አንግበው ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ ***ፓርቲዎች በአሜሪካ የዴሞክራሲ ግንባታ አካል እየሆኑ መጥተው ከ1830ዎቹ ጀምሮ ደግሞ ጠንካራ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሆኑ፡፡ ***የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ገደብ እንዲቀመጥ ቢወተውቱም የአሜሪካ ሕገመንግስት ለኮንግረስና ሴኔት አባላት ምንም ዓይነት የጊዜ ገደብ አያስቀምጥም፡፡ የግዛቶችና አካባቢያዊ ባለስልጣናት የስልጣን ዘመን በክልል ሕገመንግስታትና በአካባቢያዊ መተዳደሪያዎች መሰረት ይወሰናል፡፡ ***ድምጽ የሚሰጡ መራጮች ቁጥር ከምርጫ ምርጫ የሚለያይ ቢሆንም በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንኳን ድምጽ የሚሰጡ መራጮች ቁጥር ከብዙ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶች ያነሰ ነው፡፡ ***ጉባኤያቱ በቴሌቭዥን የሚተላለፉ ሁነቶችና የጠቅላላ ምርጫ ዘመቻው መጀመሪያ እንደመሆናቸው የፓርቲ ዕጩዎችን ለማስተዋወቅና ከተቃዋሚው ፓርቲ ጋር ያሉ ልዩነቶችን ለማሳየት መልካም አጋጣሚ ይፈጥራሉ፡፡ ***በየሙሉ ዓመቱ ከሚደረጉ የፌዴራል፣ የግዛትና አካባቢያዊ ምርጫዎች በተጨማሪ አንዳንድ ግዛቶች የአካባቢ መስተዳድሮች ምርጫዎቻቸውን በየጎዶሎ ቁጥር ዓመታት ያደርጋሉ፡፡ አብዛኞቹ ግዛቶች ባልተጠበቀ ምክንያት የተጓደሉ የስልጣን ቦታዎችን ለመሙላት በማንኛውም ጊዜ ምርጫ ሊያካሂዱ የሚችሉበት አሰራር አላቸው፡፡ ***በአንዳንድ ግዛቶች ፖሊሲን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ከእጩዎች ዝርዝር ጋር ተያይዘው መራጮች እንዲወስኑባቸው ይደረጋል፡፡ በአሜሪካ ምርጫ ሰዎችን ለመንግስት ስልጣን ከመምረጥ ያለፈ ተግባርም አለው፡፡ ***አሜሪካ ውስብስብ የሆነ ፌዴራላዊ ሥርዓተ መንግስት የምትከተል ሲሆን በዚህ ስርዓት ማዕከላዊው መንግስት ከፍተኛ ሥልጣን ቢኖረውም ግዛቶችና አካባቢያዊ መስተዳድሮች የፌዴራል መንግስቱ የማያዝበት የራሳቸው ስልጣን አላቸው፡፡ ግዛቶችና አካባቢያዊ መንግስታት በክልላቸው ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል የተለያየ የራስ ገዝ ስልጣን ደረጃ ቢኖራቸውም ወሳኝና በአግባቡ የሚፈጸሙ ምርጫዎችን በየጊዜው ያደርጋሉ፡፡ በየሁለት ዓመቱ አሜሪካውያን ሁሉንም 435 የተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከ100 የሴኔት አባላት አንድ ሶስተኛ ያህሉን ይመርጣሉ፡፡ የሴናተሮች የስልጣን ዘመን ስድስት ዓመት ነው፡፡ በየአራት ዓመቱ ደግሞ አሜሪካውያን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ፡፡ አንዳንድ ግዛቶችና አካባቢዎች ደግሞ ምርጫን በየጎዶሎ ቁጥር ዓመት ያካሄዳሉ፡፡በአሜሪካ ጥቂት የፌዴራልና የአብዛኞቹ ግዛቶች ምርጫ በየሙሉ ቁጥር አመት ይካሄዳሉ፡፡ ምርጫ በአሜሪካ***የምርጫ ባህል በቅኝ አገዛዙ ዘመን ከእንግሊዝ ታሪክ ጋር ተያይዞ የተጀመረ ቢሆንም አሜሪካ ሕገመንግስቷ ከታወጀበት ከ1787 ጀምሮ የውክልና ዴሞክራሲ ተከታይ ነች፡፡  ይህ መጽሐፍ ዘመናዊው የአሜሪካ የምርጫ ሂደት በፌዴራል፤ በክልልና በአካባቢ ደረጃ ምን መልክ እንዳለው ያትታል፡፡ ውስብስብና አንዳንዴም ግራ አጋቢ የሆነው የምርጫ ሂደት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸውን ወንድና ሴት አሜሪካውያንን በዕኩልነት ለማሳተፍ ረጅም ሂደት አልፏል፡፡ መራጮች እንደራሴዎቻቸውን ሲመርጡ የሕብረተሰባቸውን መጻኢ ዕድል የሚወስኑ መሪዎችን ይመርጣሉ፡፡ ስለዚህም ምርጫ ተራ ዜጎች የመንግስታቸውን ፖሊሲና የራሳቸውን መጻኢ ዕድል እንዲወስኑ ስልጣን ይሰጣል፡፡ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ የየትኛውም ዲሞክራሲ ቁልፍ መገለጫ ነው፡፡ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ (የትኞቹ በተግባር ውለዋል ወይም  ይውላሉ እግዜር ይወቅ) ለመረጃ እናንኩራቸው፡- “ፕሬዚዳንት ኦባማ የእሳቸውንም ደጋፊዎች፣ የሩምኒንም ደጋፊዎች ያላንዳች አድልዎ፣ የሁለቱም ፕሬዚዳንት ሆነው ይመራሉ፡፡” ሶስቱም ነጥቦች አስቀኝተውኛል፡፡ መች ይሆን እኛ አገር ይሄ ዕድል የሚገኘው? አልኩ በሆዴ፡፡ በተረፈ “ምርጫ በአሜሪካ” አጭር መግለጫ የሚለው እንጎቻ መጽሀፍ ላይ የቀረቡት ማራኪ ነጥቦች እነሆ፡-“ተሸናፊው ሩምኒ የኦባማን ድል በፀጋ ተቀብለው፣ በሰላም የመሰናበቻቸውን ንግግር ያደርጋሉ፡፡ ያንን አዳምጡ!” “አሜሪካ ከሁለት ሰዎች (ኦባማና ሩምኒ) ፍልሚያ በኋላ አሜሪካ መሆኗ ይቀጥላል” የመጨረሻው ንግግር የፖለቲካ ተወካይዋ ነበር፡፡ እሳቸው ካቀረቧቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የመሰጡኝ ሀሳቦች፡- “ምርጫው ተካሂዶ ውጤቱ የተሰማበትን የኛን ዲሞክራሲያዊ አካሄድ “ዲሞክራቲክ (Democratic Exercise) አጠናቀን እነሆ ዛሬ ማን እንዳሸነፈ ያወቅንበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን” በሚል ጀምረው የተካሄደውን ምርጫ ሂደት ገልጸው፣ የፖለቲካ ዲፓርትመንቱ ሦስተኛ ሰው የሆኑትን አዲስ የመጡ ባለሥልጣን ሚስስ ዌንዲ ሼር ማን የፖለለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ ሴት ሊያስተዋውቁን መሆኑን እና የኦባማና የሩምኒ ከፍተኛ ተምሳሌት በመሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ እነሱን መስለው፣ እነሱን አክለው፣ የክርክር ፉክክር በማድረግ ባካሄዱት የምርጫ ናሙና ስነስርዓት፤ ውጤት ያመጡትን ተወዳዳሪዎች የሰርተፊኬት  ስነ ስርዓት የሚካሄድበት ፕሮግራም መኖሩን አሳወቁ፡፡ እውነትም ከጥቂት ጊዜ በኋላ “Your attention Please” የሚለው የጥሪ ድምጽ አስተጋባ፡፡ “አንድ ጊዜ ወደዚህ አዳምጡ” እንደማለት ነው፡፡ “ዛሬ ከመጣሁ አራት ወሬ ነው” አሉኝ፡፡ ከአፍታ በኋላ፤ አንድ ወዳጄ፤ “አሁን አምባሳደሩ አንደር ሴክሬተሪዋን ይዘው ከፎቅ ይወርዳሉ” አለኝ ቀና ብዬ ወደ ፎቁ ተመለከትኩ፡፡ “ኢትዮጵያ ከመጡ ስንት ጊዜዎ ነው?”  “የሚኪሊላንድ አውሮፕላን አደጋ ጊዜ 4 የኤምባሲው ባልደረቦቼ ተቃጥለዋል፡፡” አሉ፡፡  ሰው ቀስ እያለ መሙላት ያዘ፡፡ በመካከል የፒስ ኮር ዲፓርትመንት ኃላፊ ነኝ ከሚሉ ሰው ተገናኘሁ፡፡ “በ1989 ዓ.ም እዚሁ ነበርኩ” አሉኝ፡፡“አዎ፤ ከዚያ የቡና ቁርስ ብለን ቤት ያፈራውን እናቀርባለን!” አልኩት፡፡ እንግዲህ የየባህላችን ልዩነት ነገር ይሆናል፤ አልኩኝ፡፡ቀልዱ ገብቶኝ፤ “እኛምኮ ኑ ቡና ጠጡ ብለን እናውቃለን በየቤታችን ጎረቤታችንን!” አለ እየሳቀ፡፡ከዚያ የቁርሱ ገበታ አለ፡፡ ካገኘሁዋቸው ሰዎች መካከል አንዱ የኃ/ሥላሴ ጊዜ ባለ ሥልጣን፤ ቁርሱ ገርሞታል፡፡ ምክንያቱም ቁርሱ የምር መስሎት ነበርና አሁን ሲያየው ሻይ በቡና እና የኬክ መሣይ ዳቦ ቁራጮች ስለነበሩ ነው፡፡ ሥነ ስርዓቱ ሲጀመር ወደ መሰብሰቢያው ቦታ ሲገባ ተቀባዮች አሉ፡፡ የኦባማን አርማ (ፒን) እና የሩምኒ አርማ (ፒን) ይሰጣሉ፡፡ የምርመርጠውን ደረትህ ላይ ትሰካለህ፡፡ የተዘጋጀውን ማህደር ይሰጣሉ፡፡ ውስጡ የመርጠከው ፕሬዚዳንት ስቲከር አለ፡፡ በአጠቃላይ የመምረጥህ ምልክት “እኔ መርጫለሁ” የሚልም ተለጣፊ ምልክት ይሰጣል፡፡ ሌላው በማህደሩ ውስጥ ያለው ነገር የሁለቱ ተፎካካሪዎች የህይወት ታሪክና “ምርጫ በአሜሪካ” ‘አጭር መግለጫ’ የሚል እንጎቻ መፅሀፍ ነው፡፡  ውስጡ የአሜሪካ ምርጫ ታሪክ ከጅምሩ እስከዛሬ አለበት፡፡ አሜሪካን ኤምባሲ የአሜሪካንን ምርጫ ውጤት እወጃ አስመልክቶ ከየተቋሙ ወኪል የሚላቸውን (በእኔ ግምት) ጠርቶ ነበር፡፡ ጠዋት በ2 ሰዓት ነው ጥሪው! የዛሬ አራት ዓመት እንዲሁ ነበር፡፡ በኤምባሲው ቅፅር ግቢ ባይሆንም፡፡

 

Read 3373 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 13:51