Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 10:23

ኢትዮጵያ የዓለም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኮንፍረንስ ታዘጋጃለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በጋና አክራ በተካሄደው 18ኛው የዓለም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጉባኤ የ“ወርልድ ውሜን ትሬድ ፌር አፍሪካ” ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ መኩሪያ የክብር ሽልማት የተሸለሙ ሲሆን ኢትዮጵያ 20ኛውን የዓለም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጉባኤ በ2014 ዓ.ም እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡ በጋናው ጉባኤ የመቀሌ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ሦስት ተወካዮችና የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ተሳትፈዋል፡፡ የአባይ ባንክ ፕሬዚዳንት በጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ኢትዮጵያ በጥቃቅንና አነስተኛ የት ደርሳለች? ምን ልምድስ አላት?” በሚልና “ባንክና ሴቶች” በተሰኘ ርዕሰ ጉዳይ የአባይ ባንክ ከሴቶች ጋር ያለውን ግንኙነትና የአሰራር ልምድ ለታዳሚዎች አጋርተዋል፡፡ 

19ኛው የዓለምን ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኮንፍረንስ በ2013 ዓ.ም የምታዘጋጀው ደቡብ አፍሪካ እንደሆነች ታውቋል፡፡የ “ወርልድ ውሜን ትሬድ ፌር አፍሪካ” ዳይሬክተር ወይዘሮ መቅደስ መኩርያ በጋናው ኮንፍረንስ ላይ ልዩ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን “አንድ ቀን በአገሬ እንደምሸለም አልጠራጠርም” ብለዋል፡፡ በጋናው ኮንፍረንስ የኢትዮጵያ ልዑካን በድል መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው የገለፁት ዳይሬክተሯ፤ “ውሜን አት 50’s (Women at 50’s) የተሰኘው የሃምሳዎቹ ዕድሜ ሴቶች ክብር የሆነው ፕሮግራም በኮንፍረንሱ ላይ በኢትዮጵያ ስም በይፋ መመረቁ አንዱ ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል፡፡ 
በመጪው መጋቢት ወር ላይ የመጀመሪያው “ውሜን አት 50’s” መድረክ በኢትዮጵያ እንደሚዘጋጅ የተናገሩት ወይዘሮ መቅደስ፤ አሸናፊው አገር ሁለተኛውን “ውሜን አት 50’s” ያዘጋጃል፤ ከዚያም በየዓመቱ ፕሮግራሙ በዓለም ይዞራል ብለዋል፡፡

Read 3183 times