Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 10:23

ሕብረት ባንክ 300 ሚ. ብር አተረፈ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሕብረት ባንክ ካለፈው ዓመት በ200 ሚ.ጂ የሚበልጥ ገቢ በማሰባሰብ፤ 300 ሚ.ብር ብር አተረፈ፡፡
በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ችግሮች ቢኖሩም የደንበኞችን ፍላጐት በመጠበቅ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቃቸውን የጠቀሱት የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር፤ አምና የነበረውን 6.1 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ሂሳብ በማሳደግ፣ 6.8 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡ በብድር ዘርፍም ከአምናው 3.3 ቢሊዮን ብር በ25 በመቶ የበለጠ 4.1 ቢሊዮን ብር ማበደራቸውን ተናግረዋል፡፡ የምንዛሬ አቅርቦትን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት የተገኘው 520ሚ. ብር ከአምናው በ80 ሚ. ብር እንደሚበልጥ ጠቅሰው፤ ከባንኩ አጠቃላይ ገቢ 47 በመቶ በመሸፈን ዋነኛ የባንኩ የገቢ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማጠናከር ከ147 የውጭ ባንኮች ጋር ግንኙነት መስርቶ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ሊቀመንበሩ፤ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ እውቅና ካላቸው ሰባት ባንኮች ጋር የሂሳብ ግንኙነት በመፍጠር በአራት የተለያዩ አገራት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 
ባንኩ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ ምቾት ያለው ፈጣን የኤቲ ኤም፣ የፖይንት ኤፍ ሴል፣ የሞባይል ባንኪንግና ኢ-ኮሜርስ የክፍያ አገልግሎቶች ለመስጠት መሠረት መጣሉን ጠቁመው፤ ከአዋሽና ከንብ ኢንተርናሽናል ባንኮች ጋር ያቋቋሙት ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽን የተባለው ኩባንያ በዚህ ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
በዓመት ውስጥ 15 ቅርንጫፎች በመክፈት የቅርንጫፎቹን ብዛት 63 ያደረሰ ሲሆን፣ የሰው ኃይሉም 1,975 መሆኑ ታውቋል፡፡

Read 3126 times