Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 12:04

ጀስቲን ቢበርና ሴሊና ተለያዩ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

የ18 ዓመቱ ጀስቲን ቢበር እና የ20 ዓመቷ ሴሊና ጎሜዝ ከሳምንት በፊት የፍቅር ግንኙነታቸውን በማቋረጥ መለያየታቸውን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ ባለፈው ሳምንት ሴሊና ጎሜዝ በሁለቱ መካከል የነበረው ግንኙነት እጅግ እየተወሳሰበ መምጣቱንና ጀስቲን ቢበር ለፍቅራቸው እንደማይታመን መጠርጠሯን በመግለፅ ለመለያየት ቀድማ መወሰኗን “ዘ ፒፕል” መጽሔት ዘግቧል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት የሆሊውድን ትኩረት ስቦ የቆየው የሁለቱ ታዳጊዎች የፍቅር ግንኙነት ንፋስ የገባበት በስራቸው ፕሮግራም አለመጣጣም ሳይሆን አይቀርም ብሏል - “ኢኦንላይን” ባሰራጨው መረጃ፡፡

ጀስቲን ቢበር ከቪክቶርያ ሴክሪት ኩባንያ የ19 ዓመት ሞዴል ጋር በድብቅ ግንኙነት መጀመሩን የጠቀሰው “ዩኤስ ኤ ዊክሊ”፤ ካናዳዊው ከዚህች ሞዴል ጋር ሲኒማ እየገባ ሲዝናና መታየቱን ጨምሮ ዘግቧል፡፡ የሴሊና ጎሜዝ ቃል አቀባዮች በበኩላቸው፤ ተዋናይቷ ያፈረሰችውን የፍቅር ግንኙነት በፍፁም እንደማትቀጥል እየተናገሩ ቢሆንም ጀስቲን ቢበር ግን እንደሚፈልጋት አንዳንድ ዘገባዎች ይገልፃሉ፡፡የፖፕ ኮከብ ሙዚቀኛው ቢበር እና የዲዝኒ ምርጥ ታዳጊ ተዋናይት ሴሊና የፍቅር ግንኙነት በድንገት መቋረጡ የሁለቱንም አድናቂዎች ማስደንገጡን የገለፀው “ዩኤስ ዊኪሊ” ጠቡ ጊዜያዊ ሊሆን እንደሚችል አልክቷል፡፡

 

Read 7734 times Last modified on Saturday, 17 November 2012 12:16