Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 12:17

“ከለርስ ኦፍ ዘ ናይል” የፊልም ፌስቲቫል በሽልማት ተጠናቀቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከጥቅምት 28 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው “ከለርስ ኦፍ ዘ ናይል” ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል በአስር ዘርፎች ሽልማት በመስጠት ባለፈው እሁድ ምሽት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ተጠናቀቀ፡፡ ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ ከኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ማህበር ጋር ባዘጋጁት ፌስቲቫል፤ 58 ፊልሞች ተሳትፈው ሽልማቱ ተሰጥቷል፡፡ በተለያዩ ዘጠኝ ዘርፎች ከስድስት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፊልሞች “ምርጥ” በመባል ዋንጫ ሲሸለሙ የፌስቲቫሉን ትልቁን ሽልማት “ዘ ግራንድ ናይል አዋርድ“ የናይጄርያው ፊልም አሸንፏል፡፡

የተቀሩትን “ሎሚ ሽታ” ፊልም ላይ ባሳየችው የትወና ብቃት ኢትዮጵያዊቷ ኤልሳቤጥ መላኩ “ምርጥ ሴት ተዋናይ”፣ የደቡብ አፍሪካው ፊልም በምርጥ ሳውንድ ትራክ፣ የግብፁ ፊልም በምርጥ ድምፅ፣ የአልጄርያው በምርጥ የፊልም ጽሑፍ፣ የፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ የቀድሞ ተማሪ የሰራው የናይጄርያው ፊልም በምርጥ ሲኒማቶግራፊ፣ የቡርኪናፋሶው በምርጥ ዶክመንታሪ ፊልም፣ የኢትዮጵያዊው እዝራ ውቤ ፊልም በምርጥ አጭር ፊልም ተሸልመዋል፡፡ ፌስቲቫሉ በመጪው ዓመትም እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

Read 2743 times