Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:18

“ይሳቃል”፣ “ሰላም” እና የስዊድን ኤምባሲ የሙዚቃ ድግስ ሊያቀርቡ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ይሳቃል” ኢንተርቴይመንት፣ ሰላም ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ “ሰላም ፌስቲቫል” የተሰኘ የሙዚቃ ድግስ ሊያቀርቡ ነው፡፡ ህዳር 28 እና ህዳር 29 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች እና ኢትዮጵያውያንም ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ከትናንት ወዲያ በስዊድን ኤምባሲ ይህንኑ አስመልክቶ በተሰጠ የስዊድን አምባሳደር ጄንስ ኦድላንደር በተገኙበት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ የመናገር መብት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ሙዚቃ ነው ካሉ በኋላ፣ መንግስታቸው በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ የሙዚቃ ድግስ እገዛው የግሉን ዘርፍ ለማጠንከር ከሚተገብራቸው መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከአስር ስድስቱ እጅ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች በሚያቀርቡበት የሁለት ቀን የሙዚቃ ድግስ ከሚሳተፉት ሙዚቀኞች መካከል እውቁ የኮትዲቯር አንጋፋ ድምፃዊ አልፋ ብሎንዲ፣ ኢትዮጵያዊው አለማየሁ እሸቴ፣ ኢትዮጵያዊው ማህሙድ አህመድ ኢትዮጵያዊቷና ጀርመናዊው ሙኒትና ጆርግ፣ ኬንያዊው ኤሪክ ዋንያና የሚገኙበት ሲሆን ጃኖ ባንድ፣ ሴቶች ብቻ ያሉበት የኢትዮጵያው ጃኒናይት ባንድ፣ ኢትዮ ከለር፣ መሃሪ ብራዘርስ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ፣ ከአማራና ደቡብ ክልሎች የመጡ የሙዚቃ ቡድኖችም ይሳተፋሉ፡፡

Read 3798 times