“ይሳቃል” ኢንተርቴይመንት፣ ሰላም ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ “ሰላም ፌስቲቫል” የተሰኘ የሙዚቃ ድግስ ሊያቀርቡ ነው፡፡ ህዳር 28 እና ህዳር 29 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች እና ኢትዮጵያውያንም ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ከትናንት ወዲያ በስዊድን ኤምባሲ ይህንኑ አስመልክቶ በተሰጠ የስዊድን አምባሳደር ጄንስ ኦድላንደር በተገኙበት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ የመናገር መብት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ሙዚቃ ነው ካሉ በኋላ፣ መንግስታቸው በኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ የሙዚቃ ድግስ እገዛው የግሉን ዘርፍ ለማጠንከር ከሚተገብራቸው መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡