በአኮርድዮን ዘፈኖቹ የሚታወቀው የእውቁ ድምፃዊ ፍሬው ኃይሉ ልጅ ዳዊት ፍሬው “ጥላ ከለላዬ” በሚል ርእስ ያሳተመውን አልበም የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11 ሰአት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት እንደሚያስመርቅ ገለጠ፡፡ በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀናበሩት ዜማዎች የጥላሁን ገሠሠን፣ የፍሬው ኃይሉን፣ የማህሙድ አህመድን፣ የምኒሊክ ወስናቸውን ዘፈኖች የያዘው አልበም፤ ለዳዊት ሁለተኛ አልበሙ ነው፡፡ “ጥላ ከለላዬ” ከማክሰኞው ምርቃት በኋላ ለሕዝብ መቅረብ እንደሚጀምር ሙዚቀኛው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡