Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 November 2012 12:51

አዲሱ የጄምስ ቦንድ ፊልም “ስካይፎል”፣ እየተደነቀ ነው

Written by 
Rate this item
(2 votes)

በአያን ፍሌሚን የስለላ ድርሰቶች ላይ ተመስርተው ከተሰረቱት የጄምስ ቦንድ ፊልሞች ሁሉ የላቀ ነው ተብሎ አድናቆት የተቸረው “ስካይፎል”፤ ፊልም ተመልካቾችን ለማርካት በመቻሉ ገበያ ቀንቶታል። በእንግሊዝ የስለላ ተቋም ውስጥ፣ “007” የሚል የሚስጥር ስም የተሰጠው ጄምስ ቦንድን በመወከል ዳንኤል ክሬግ የተወነበት ይሄው ፊልም፤ በአስር ቀናት ውስጥ 670 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ከሌሎቹ የጄምስ ቦንድ ፊልሞች ብልጫ አስመዝግቧል።

“ዶ/ር ኖ” የተሰኘው የመጀመሪያው የጄምስ ቦንድ ፊልም ሃምሳኛ አመቱ በሚከበርበት እለት የተመረቀውና ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ለእይታ የቀረበው “ስካይፎል”፤ 23ኛው የጄምስ ቦንድ ፊልም ነው።
ከሸን ኮነሪ በተጨማሪ ሮጀር ሙርና ፒርስ ብሮስናን በተለያዩ ጊዜያት የጄምስ ቦንድን ገፀባህርይ የተጫወቱ ሲሆን፤ በቦታቸው የተተካው ዳንኤል ክሬግ የአሁኑን ጨምሮ በሶስት ፊልሞች ሰርቷል። “ካሲኖ ሮያል” እ.ኤ.አ በ2006 ለእይታ ሲበቃ በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት 600 ሚ. ዶላር አስገኝቷል። በ2008 ደግሞ፣ “ኳንተም ኦፍ ሶላስ” በአስር ቀናት 590 ሚ. ዶላር አስገብቷል። ከአነሳሱ የተሻለ አድናቆትና ገቢ ለማትረፍ የቻለው የዘንድሮው “ስካይፎል”፤ ወደ ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የተሰራ ነው።

Read 2622 times