Print this page
Thursday, 29 November 2012 10:43

ያንቺ ዓይነት እናት አለችኝ

Written by  ነ.መ
Rate this item
(16 votes)

ፍቅሬ …አገሬ…ፍቅሬ
እንደዛሬ
በግ ሳትሆን በፊት፣ የዱር አውሬ
እወድሽ ነበር አክብሬ፡፡
አሁን ግን…
የቤት እንስሳ፣ ከመግዛት፤
የዱር አውሬ ማደን ቀሎ
ሰው ሁሉ አዳኝ ሆነ አሉኝ፣
መርጦ የጫካውን ውሎ
አንድ ቀን ብበላ ብሎ፡፡

እና ደሞ ጫካው ሁሉ 
ተመንጥሮ አለቀ አሉ፡፡
ደምሞ ንፁሁ አየር ሁሉ
በሌላ ፋብሪካ ትንፋሽ፣
በጭሱ ተቃጠለ አሉ
አዳኝ ምን ይተነፍሳል?
በጓስ ምን ትግጣለች?
ወይስ እንደፈረደባት
ያው እንደዘመኑ ወጣት፣ ካገር ትሰደዳለች?
ብቻ ምንም ይበሉኝ ምንም
ዛሬ አልወድሽም አልልም
ፍቅሬ ሙች! ፍቅሬንአልተውም!
አገረ - ገዢ ሳላይ
አዳኝ ታዳኝ ሳልመኝ
ባለፋብሪካም ባላገኝ
የሁሉም ወኪል የሆነች፣
ያንቺ ዓይነት እናት አለችኝ
ይሄንን ብቻ እወቂልኝ!
ሚያዚያ 2004

Read 7003 times Last modified on Thursday, 29 November 2012 11:13