Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 27 June 2011 16:14

ማህበረሰብ እና ግለሰብ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

የተከበራችሁ አንባብያንዕ-

ስናስብና ስንናገር እንዲመቸን (በቀላሉ እንዲታሰበን) በጥቅሉ ማህበረሰብ እንላለን እንጂ ይሄ ..ማህበረሰብ.. የምንለው ነገር በተጨባጩ አለም ውስጥ የለም፡፡ እንግዲያው ማን ነው ያለው? ግለሰቦች ናቸው፣ እያንዳንዳቸው መልኩም ባህሪዩም ከማናቸውም የተለየ፣ ራሱን የቻለ Universe.

ለዛሬ የባህል ጉዞ አስጎብኚያችን Dr. Sigmund Freud ይሆናሉ፡፡ ህልም ምንድነው) Sigmund ገና የአስራ አራት አመት ወጣት እያለ የጀመረ፣ ረዥም፣ ታታሪነት የጠየቀና ስኬታማ ህይወቱን ሙሉ ህልምን ሲያጠና ሲመረምር አሳለፈ፡፡ ምእራባዊውን አለም በሙሉ ያስደነቀው ወፍራም መሀፉ (እና ለሀምሳ አመት ያህል እንደ መሀፍ ቅዱስ እያመኑበት የዘለቀ) (The interpretation of Dreams) ይባላል፡፡ በነገራችን ላይ፣ ሰውየው ጀርመን - ይሁዲ ነው፡፡ በሂትለር ዘመነ መንግስት የኖረ፡፡ ከአስራ አራት አመቱ እስከ እርጅናው ድረስ፣ እንቅልፍ ሊወስደው ሲል ..ህልም አያለሁ፣ ህልም አያለሁ.. እያለ እየደጋገመ ይተኛል፡፡ ልክ ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ ወድያው ህልሙን (ህልሞቹን) በደብተር ላይ ያሰፍራል፡፡ ጓደኞቹንና ዘመዶቹን ባገኛቸው ቁጥር ምን ህልም እንዳዩ ይጠይቃቸዋል ..እና ፍቺው ምንድነው)..

ህልምንም ህይወትንም ፍሮይድ መርምሮ ሲፍልን የሰው ልጅ ስነ - ልቦና ውስጥ ሶስት አካላት አሉት (ግለሰባዊ ስላሴ))  Id, Ego እና  Super – Ego ይላቸዋል፡፡

አካል አሀዱ -  Id

ኢድ በእድሜም በስልጣንም መሰረታዊ አካል ነው፡፡ አራስ ልጅ ገና ኢድ ብቻ ነው፡፡ እሱና ጡቱ ሁለቱ አካላት መሆናቸውን እንኳ ገና አያውቅም፡፡ እሱ የሚያውቀው ምቾትና ደስታን ብቻ! እውነታን ከምናብ አይለይም፡፡ እውነትም ውሸትም ለሱ ያው ናቸው፡፡ ልጅ በሶስትና አራት አመቱ ሲዋሽ እውነቷን መደበቁ አይደለም፡፡ እውነቷም ውሸቷም ለሱ ያው ስለሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ወላጅ ..አንተ ውሸታም!.. ብሎ ቢያፋጥጠው፣ ወይም በሀበሻ ደምብ ቢገርፈው፣ ስህተቱ ወይም ጥፋቱ የወላጅ ይሆናል፡፡ አራሱ ልጅ ወራት እየጨመረ ሲሄድ፣ ከእለታት አንድ ቀን እናት እጁን ወደ እሳት ታስጠጋውና ..እፉ!.. ትለዋለች፡፡ እጁን ሲያሸሽ ማደግ ብቅ ትላለች፡፡ ከውጭው አለም ጋር ተዋወቀ፡፡ አሁን  Ego ተፈጠረ፡፡

አካል ክልኤቱ - Ego

ኢጎ ከውጭው አለምና ከሌሎች ሰዎች ጋር የምናካሂደውን ግንኙነት ይቆጣጠራል፡፡ ኢጎ ሲበዛ realist ነው፡፡ (ማለት ተጨባጭዋን አለም በደምብ ያውቃታል፡፡) የክፉውንና የደጉን ልዩነት በሚገባ አሳምሮ ያውቃል፣ የሚያስከትሉትንም ጉዳትና ጥቅም ጭምር፡፡ እንድያም ሆኖ ግን ኢጎ ግብረገብን አያውቅም፡፡ ለምሳሌ ..ሰይጣን አስቶህ.. እህትህን በግብረ ስጋ ትመኛለህ፡፡ ኢጎ እንዴት አድርገህ እሺ ልታሰኛት እንደምትችል፣ የትስ እና እንዴስት ብታደርጉት ከመጋለጥ እንደምታመልጡ፣ ይህን ሁሉ ያስተካክልልሀል፡፡ በኋላም እንደገና ሰይጣን አስቶህ ልትገድላት ብትፈልግ፣ የት እና በምን እና እንዴት እንደምትገላት በዝርዝር ያቅድልሀል፡፡ ሳትጋለጥ የምታመልጥበትን ዘዴም ያሳይሀል፡፡ ጥፋት አለብህ የሚባለው ከተያዝክ ብቻ ነው፡፡ ኢጎ ልክ እንደ ኢድ ስለ ግብረ ገብ ደንታ የለውም፡፡

አካል ሰለስቱ - Super – Ego

የግብረ ገብ ጉዳይ የሱፐር - ኢጎ ሀላፊነት ነው፡፡ እሱ የሚሰለጥንብን ክፉውንና ደጉን ለመለየት እድሜያችን ካስቻለን በኋላ ነው፡፡ ሱፐር - ኢጎ እንደ ነፃ አውጪው ሙሴ አምላክ ቂመኛና በቀለኛ ነው፡፡ የሚቀየመውም የሚበቀለውም ኢድን እና ኢጎን ነው፡፡ (የውስጣችን Civil War# ማለት የእርስ በርስ ውጊያ)

በቀለኛነቱ በግል የሚታየን፣ ኢድ እውነታን ከምናብ የማይለይ፣ ኢጎ ደግሞ ግብረገብ የምንለውን እምነት የማያውቅ መሆናቸውን ስናስታውስ ነው፡፡

. . . የሱፐር ኢጎ በቀል እንዲታየን ያህል ኢድ ይህን የማያውቀውን ሱፐር - ኢጎ  እንዴት እንደሚሸውደው እንመልከት (ያውም ሊሸውደው አቅዶ ሳይሆን፣ በየዋህነቱ እና በተፈጠረለት ስጦታ የራሱን ደስታ እያሳደደ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡) ሰውየው ህልም ያያል፡፡ ነጭ ፈረስ ሲጋልብ፣ ሲጋልብ፣ . . . ሲነቃ ለካ Wet dream ኖሯል - ማለት፣ ከሴት ጋር የተቃቀፈ ይመስል ዘሩን ረጭቷል፡፡

ህልሙ ሲዘረዘር ከነፍቺው በፍሮይድ እይታ እንዲህ ይላል፡፡ ነጭ ፈረስ ማለት ፈረንጆቹ  blonde (ፀጉሯ ከወርቃማ እስከ ..ነጭማ.. የሆነች) ሴት ናት - ባለህልሙ ሲመኛት የቆየ፣ የሰነበተ፣ ወይም የከረመ)

ሱፐር - ኢጎ ጊዜውን ጠብቆ ኢድን በደፈጣ ይበቀለዋል፡፡ ባለህልሙ ተራ ወታደር ወይም ጄኔራል ነው እንበል፡፡ ስለጦር መሳርያ ጠንቅቆ እያወቀም፣ የገዛ ጠበንጃውን ሲወለውል ይሁን ሲመረምር እንጃ፣ ባርቆ ይገድለዋል (ሀዥደደጵነ ሰጭዥቸዥደጵ ስውር ራስን መግደል)

ሌላው ባለህልም Mountain ችለፀመበጵረ ነው እንበልቃቃ ከችሎታው ብዛት የተነ ምን አይነት ገመድና ሎች መሳሪያዎች እንደሚያስፈልገ እግርና እጅ እንዴት እንደሚቀናጁ ሎችን ሰዎች እያስተማረ ይኖራልቃቃ ሰጵፐር ጠ አጯጎ ይህን ባለሙያ ስለተቀየመ በአሳቻ ሰአት ወደነዘጯህ የዶክተር ፍሮይድ ግት ወደሆነጵት ሥየውስጣችን ስላዎች.. ትንሽ ቆይተን በቀጥታም ይሀጵን በዘጵርያ ጥምጥም መመለሳችን አይቀርምቃቃ

ምእራፍ ክልተ

ዶክተር ፍሮይድ የጥንቶቸን ያገራቸውን ልጆች የነሙን የነአጯሳያስን ያህል ነብይነት ፈጥሮባቸ ሳይንሳዊ ዘመናችንን አነጣጥረው ውስጣዊ አይነጵን የከፈተለት ናቸው -እዘጯህ ላይ አስተዋይ አንባበጯ ሥአውቆ የተኛ በጯ..ሩት አይሰማም.. የሚባለውን ለጯያስታውስ ይችላል?

ዶክተራችንን ገና ገና ዝነኛ ሳይሆነጵ ጀምሮ -ማለትም ግቶቻቸውን አነስተኛ ቀጥር ያላቸው ባለሙያዎች  (Specialist) ብቻ በሚያነቡዋቸው አመታት) ጥቂት ደቀመዛሙርት ነበሩዋቸው፡፡

Ferenzi የተባለውን የ  Hungary አገር ተወላጅ ጐልማሳ እንደ ልጃቸው ይወዱት ነበር፡፡ እና ባህሪዩን ስለሚያውቁ፣ ከእለታት አንድ ቀን ራሱን እንዳይገድል ይሰጉለት ነበር፡፡

እሳቸው ዝነኛ በሆኑበት ጊዜ፣ ወንጌላቸውን እንዲያሰራጭ ተጋብዞ አንድ አዳራሽ ውስጥ እየሰበከ እያለ፣ አንዱ አክራሪ የፍሮይድ ቲፎዞ ..እሳቸው በፍፁም ይህን ብለው አያውቁም.. እያለ ሲያፋጥጠው፣ ፈረንዚ በዚች ሀቅ ኰረኰረውዕ-

..የገደል ቅራፊ የሚያህል ግዙፍ ሰው፣ አንዱን ድንክ እንኮኮ ቢሸከም፣ ድንክየው ከግዙፉ የሰፋ አድማስ ይታየዋል..

እና እውነትም፣ አንድ ቀን ፈረንዚ ራሱን ገደለ፡፡ እኛ እስከምናውቅ ድረስ፣ የዶክተር ፍሮይድን ቅስም የሰበረ ትራጀዲ ይሄ ብቻ ነው፡፡

ሌሎቹ ..ምርጥ.. ደቀመዛሙርታቸው  Alfred Adler  እና  Carl Jung  ሲሆኑ፣ ሁለቱም ከመምህራቸው ጐዳና አፈንግጠው፣ የየራሳቸውን ተገንጣይ መንገድ እየተጓዙ፣ የሰውን ልጅ እይታ ያሰፉ ናቸው፡፡ ሁለቱንም ለሚቀጥለው ሁፋችን አቆይተን አሁን ከፍሮይድ ጋር እንቀጥል፡፡

ዶክተር ፍሮይድ በሰማንያ አንድ አመታቸው፣ አንድ ቀን ሲያስተምሩ ውለው ሲመለሱ፤ ሁለት የሂትለር  SS (ኤስ ኤስ) ፖሊሶች ቤታቸውን ሲበረብሩ አገኙዋቸው፡፡ ኤስ ኤስ ቤትህ ገብተው ብታገኝ፣ እንኳን ይሁዲ ቀርቶ፣ ጀርመናዊ ዜጋ ብትሆን ..አለቀልኝ! ብለህ ትሽቆጠቆጣለህ፡፡

ዶክተር ፍሮይድ ግን በቁጣ እያፈጠጡባቸው ..ፕሮፌሰር ነኝንጂ ወንጀለኛ መሰልኳችሁ፣ በሌለሁበት ቤቴ ምትገቡት) ውጡ ከዚህ!.. አሉዋቸው፡፡

በተገላቢጦሽ፣ ሁለቱም እየተሽቆጠቆጡ ..ይቅርታ ፕሮፌሰር፣ ስራችን ስለሆነ ነው.. እያሉ ወጡ . . .

. . . እንኳን የሳቸውን ያህል ዝነኛ ቀርቶ፣ ተራ ይሁዲም ከኤስ ኤስ አይን አያመልጥም፣ ተለቅሞ ወደ መርዝ ጪስ ሞት ይወስዳታል እንጂ፡፡

(The Dirary of Anne Fank – ትርጉም ..የአና ማስታወሻ.. የተባለች መሀፍ ያነበባችሁ፣ ያችን የመሰለች ተወዳጅ ያስራ አራት አመት ልጅ እንዴት ወደዚያ የሀያ ሚልዮን ይሁዲዎች አሰቃቂ ሞት እንደተላከች ታስታውሳላችሁ) ዶክተር ፍሮይድ ግን እድለኛ ሰው ነበሩ፡፡

Benito Mussolini ወደ ጦር አጋሩ ወደ ሂትለር ስልክ ደወለ፡፡ ..ዶክተር ፍሮይድን ለኔ ስትል ማርልኝ፣ ወደ ለንደን ሄደው፣ የቀራቸውን ጥቂት አመት በሰላም እንዲኖሩ..

ሂትለር መልካም ፈቃዱ ሆነ፣ ዶክተር ፍሮይድ በክብር ወደ ለንደን ተወሰዱ . . .

ምርቃት

Sigmund በስድስት አመቱ እናቱን እንዲህ አላቸውዕ- ..እግዚአብሔር አዳምን ጭቃ ጠፍጥፎ ኡፍ! ብሎ ሲተነፍሰበት ሰው ሆነ የሚባለው እውነት ሊሆን አይችልም.. ..እኛ አፈርም ጭቃም አይደለንም እያልክ ነው)..

..እያየሽን አይደለም እንዴ) ምናችን ጭቃ ነው)..

..እንግድያው ተመልከት.. አሉትና፣ መዳፍና መዳፋቸውን አፋተጉ፡፡ እና ጥቃቅን ሞላላ ጭቃዎች አሳዩት፣ አመነ፡፡

ምርቃት

ፍሮይድ የመጀመሪያ ዲግሪውን የተቀበለው በህክምና ነበር፡፡ በዚያን ዘመን eel የሚባለው አሳ የዘር መባዣ መሳሪያው(ዋ) ተፈልጎ ተፈልጎ፣ የሚያገኘው ጠፍቶ፣ ..የኢል ወንዱን የሰው ሆዱን የሚያውቀው የለም.. እንደምንለው አይነት ሆኖ ነበር፡፡ ፍሮይድ አገኘዋ!

ከህክምና አልፎ ወደ ..ሳይኮሎጂ - ፊሎዞፊ.. ገብቶ ፈር ቀዳጅ  Psychiatrist ከሆነ በኋላ ደግሞ፣ የሰው ልጅ መሰረታዊ ባህርዩ እና የሚነዳው (ወይም የሚመራው) ሀይል  Sex        !

 

 

 

 

 

 

Read 9909 times Last modified on Monday, 27 June 2011 16:31