Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:00

1/2 ሌሊት - 1001 ትዝታ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

..ኧረ መርሳ በለኝ!.. እያለ ትንሹ ትልቁ ደረሳው ወልዩ በፍቅር የሚወዳት የአባትዬዋን መንበር፤ የሸህ ሚዕዋን መንደር-መርሳን ከተማዬ ሃብሩን ወረዳዬ እያልኩ መኖር ከጀመርኩ አምስት ወር እንኳን አልሞላኝም፡፡ እኔ አንዷንም ሳላቃት የእሷ አድርጋኝ ከወዳጆቿ ቀላቅላ በዱአዋ እቅፍ ድግፍ አድርጋ አቀማጥላ የያችኝ ሃብሩ፤ አንዳንዶች እንደተረኩልኝ ስፋቷ የአንድ ጠቅላይ ግዛት ያህል ቢገዝፍብኝም፤ ጓዳ ጐድጓዳዋን አብጠርጥሬ ላውቀው ምኞቴ ነበር፡፡

መርሳን በርቀት አፍነው ከሚያሞቋት ተራሮች ጀርባ የሆነ የተደበቀ ምስጢር ያለ ይመስል ሁሌ ሃሳቤ ዓይኔ የማያየውን የተራራውን ጀርባ፣ ክንፎቹን እያማታ የቅኝቱን ትንቢት እየተነበዬ ላለዬው ዓይኔ እውነት አስመስሎ ይነግረዋል፡፡ ዓይኔም አምኖ ለጭንቅላቴ ይነግረዋል፡፡ ጭንቅላቴ አያምነውም! ለምን ቢሉ የትላንት ትንቢት ሌላ፤ የትላንት ወዲያ ሌላ፤ የትላንት ወዲያ ወዲያ ደግሞ እንደዛው... የሌላውን አላውቅም የእኔ አይነቱ ነቄ ጭንቅላት ይህን አያምንም! ..ይልቅ ተረጋጋ ጠቅላይ ግዛት ያከለችብህን ይችን ወረዳ እንደነገሩህ ልትነግር-ልትመሰክር ታቃታለህ.. እያለ በሩን ይከረችማል፡፡
አሁንም ሃሳቤ ከተራሮቹ ጀርባ መሄዱን ግን አያቆምም፤ ዓይኔም ማመኑን አይተውም፤ ጭንቅላቴም ባለማመኑ ይፀናል-በዓይን ይበግናል-ይንጨረጨራል! ዓይንም ብዕር ከአፎቱ አለያይተው ብሶቱን እንዲተነፍስ እድሉ ቢሰጠው ኑሮ እንዴት በጭንቅላት ችኮነት ነዶ ጨሶ ማረሩን ጭራዎቹን እያወናጨፈ የእምባ ማዕበሉን ከዚያና እዚህ እያማታ፣ ነጭ ደረቱ መሃል ቀይ ባንዲራውን እያውለበለበ በገለፀ ነበር!
ቀልብያዬ ሊያዬው የከጀለውን ከዱዓዬ ባሻገር የእንጀራ ነገር ተጨምሮበት ሃብሩን ማወቅ ጀምሬያለሁ፡፡ የማወቄ አሃዱ ደግሞ የድሬ ሮቃው ጉዞዬ ነበር፡፡ የዛሬን አያድርገውና ያኔ የማስታወቂያ መኪና ..አስናቀች.. ..ነብሮ.. እየተባለች ሜዳ ተራራውን በአዲሱ ሾፌር ዘዋሪነት ትሾረዋለች፡፡ ያኔም ቢሆን ግን እንደዛሬው ጨክና አትቁም እንጂ በየሳምንቱ አንድ አንድ ዕቃ እየሰበረች ክፍሉን እንዳላወቀ ፀበልተኛ ሆድ ዕቃዋን በየጋራጅ ቤቱ እየተንከለከለች ማስቦጥቦጥ ስራዋ ነበር፡፡
*   *   *
ከመርሳ የተነቃነቅነው ወደ አራት ሰዓት ገደማ ነው፡፡ አለቃችን ጋቢና፣ እኔ ጃቬኖ፣ ሀብታይ (ስማቸው የተቀየረ) እና አንድ እንግዳ ሰው የሁለተኛውን ጋቢና ይዘናል፡፡ ወልዲያ አጠር ያለ የምሳ እረፍት ወስደን ወደ መዳረሻችን ጉዞ ቀጥሏል፡፡ የሃሳቤን ትንቢት ዓይኔ ከሚያየው ከተራራው ጀርባ እውነት ጋር እያነፃፀረ ይህ እውነት፣ ያ ደግሞ ውሸት እያለ ተጨማሪ ማብራሪያም ከወንበርና ከስራ ባልደረቦቹ እየተጀባው መንጐድ ይዟል፡፡ እንደ ኩር ኩር ወፍጮ እየተንደቀደቀች የምትከንፈው መኪና ሙቀት፤ ከላይ እሳት የምትተፋ ከምትመስለው ጠራራ ፀሃይ ጋር ተዳምሮ ሌላውን ትተነው አፍንጫችንን ያልበን ጀምሯል፡፡ አገር የማያቅ ሰው ..አሁን ደረስን... ምን ያክል ይቀረናል... ያ ተራራ ማን ይባላል... ያኛውስ?.. እያለ መጠየቁ አይቀርምና እኔም እጠይቃለሁ፡፡ ቢያረካኝም ባያረካኝም መልስ አገኛለሁ፤ መጠየቄንም አላቆምም፡፡
ድረስ ያለው ኢየሩሳሌም በእግሩ ሄዶ ይሳለማልና የናፈቅናት ድሬ ሮቃ መንደር ደረስን፡፡ የመንደሯ ስም ዝም ብሎ አምሮኛል፡፡ ምናልባትም ከዝነኛው ድሬድዋ ጋር ተቀራራቢ ስለሆነ ይሆን? ብቻ ወድጄዋለሁ! መንደሯን ሳያት ግን የስሟን ያህል ፍቅር እንዲኖረኝ አላደረገችኝም፡፡ ወደ ጅቡቲ የሚያስኬደውን መኪና መንገድ ተከትለው ለ500 ሜትር ያክል ርዝመት ያልተስተካከለ ሰልፍ ይዘው ከተሰሩት የቆርቆሮና የሳር ጐጆዎች መሀል የቁጥር 24 ቀበሌ አስተዳደር /ቤት፣ የኮምቦልቲ ጤና ኬላ፣ የድሬሮቃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ቀኝ ፈንጠር ብሎም ትልቅ በኬንዳ የተሸፈነ አዳራሽ ይታያል፡፡ የሚራወጠው ይበዛል፡፡ አንዱ ይሄዳል ሌላው ይመለሳል፡፡ ይሰበሰባል፤ ይበተናል-ብቻ ሰው ይታመሳል፡፡ የመኪናው ገባ ወጣም እንደ ሰው ነው፡፡ የያኔዋ ድሬ ሮቃ ማለት ይህች ነች፡፡ ግን ይህች ብቻ አይደለችም! ድሬ ሮቃ ለብዙ ሰው ብዙ ነበረች!
መራወጡም መሰብሰቡም የአፋርና አማራ ወጣቶች ፌስቲቫልን ለማድመቅ ነው፡፡ ሁሉም የየራሱ ድርሻ አለው፡፡ ትንሹ ድርሻ ለበዓሉ መታደም ሳይሆን አይቀርም፡፡ እኔ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ያመጣኝን የሥራ ድርሻ ለመወጣት ከተራዋጮቹ ወገን የተሰለፍኩት ወዲያው ከመድረሴ ነው፡፡ የኔ ቢጤ ሰውነቱ ከሳ ያለ የጤና ኬላው የህክምና ባለሙያ እንድናርፍበት ካዘጋጀልን ጐጆ አረፈ ብለን የአፋሮቹና የእኛዎቹን (የ..አማሮቹን.. ማለቴ ነው) - አንድነትና የባህል ትስስር የሚያጐሉ ፎቶዎች በፈርጅ በፈርጁ ማዘጋጀት ይዘናል፡፡ አንዱ ይለጥፋል፤ አንዱ ይፋል፤ ሌላው የተሰሩትን በሥርዓቱ ያስቀምጣል፡፡ ይህን ሥራ ብቻ የምሰራው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ሌሎቹ በተደራቢነት ለእርቁ ዱዓ ማድረጊያ ከተገዛው ጫት የመነተፉትን ..ጠቅላላ እውቀት.. በትኩስ ሻይ እያራሱ ይጨፈጭፉታል፡፡ (ከፖሊሶቹ እንደሰማኋት ነገርየዋን ጠቅላላ እውቀት ብለው የሚጠሯት ያችን የቀመስክ ጊዜና ነገሩ ሁሉ ይብራራልሃል፤ ይገለጥልሃል ለማለት ነው - ድንቄም መገለጥ!)
11 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ያዘጋጀነውን ፎቶ በተዘጋጀው አዳራሽ መለጠፍ ጀመርን፡፡ ነፋስ ይገነጥላል፤ እኛ እንለጥፋለን፡፡ ተንሸራቶ ይወድቃል፤ እንደገና እናያይዛለን፡፡ ከስንት ትግል በኋላ የተወሰኑ ፎቶዎች ቦታቸውን ያዙልን፡፡ ያሰብነውን ያህል ባይሆንም ያው ከምንም ይሻላል፡፡ የተዘጋጁ ባነሮችም ተሰቀሉ፤ ለአዳራሹ ብርሃንና ለሙዚቃ መሣሪያ መትከያ የሚሆን መብራት ከጄኔሬተር ተያያዘ፡፡
*   *   *
ከወደ ጭፍራ በጭነት መኪና የሚጐርፉት የአፋር ወጣቶች በባሕላዊ ጭፈራቸው የድሬ ሮቃ መሬትን ወደ ላይ እየሰገሩ ይነትሩታል፡፡ ዘያቸውን እየቀያየሩ ጨዋታውን ያፈኩታል፡፡ ጠይም የአፋር ቆነጃጅቶችም የራሳቸውን ጨዋታ ጐን ለጐን ያደሩታል፡፡ ሁሉም ዘና ብለው ነው የሚጨፍሩት፡፡ ከላይ ከአናታቸው ጀምሮ ወደ ታች ወደ አንገታቸው እየተጠቀለለ የሚወርደው ፀጉራቸው ለጭፈራ ወደ ላይ ሲዘሉ አብሮ እነሱ ጋር እየጓነ አንገታቸው ጋር ሲላተም ለተመልካቹ የሚፈጥረው ስሜት የተለየ ነው፡፡ የጭብጨባው ነገር ደግሞ እፁብ ድንቅ ነው! እጅና እጅ እየተላተመ ያን የመሰለ የሚያምባርቅ ድም መፍጠሩን ማመን ይቸግራል፡፡ አንዴ ዓይኑን ወደዚህ ትእይንት ያሳረፈ፣ አቧራው ሳይበግረው ከነሁለመናው እዚያው ይቀራል፡፡
ጀምበር ማዘቅዘቅ ጀምራለች፡፡ በአዳራሹ የታደመው ታዳሚ በኦርጋን ታጅቦ በሚንቆረቆረው ጣእመ ዜማ እየተወዛወዘ፣ የድሬ ሮቃ መንደር ድምቀቷ ሳይጓደልበት የጨዋታው ግለት ሳይሰክን ቀጥሏል፡፡ ጨለማው እየጠቆረ ጊዜው እየገፋ ነው፡፡ እኒያ ድምፀ መረዋ ዘፋኞች የሰውን ሁሉ ስሜት እያጋሉ፣ እያነቃቁት ከጀኔሬተር ተያይዘው ጭል ጭል የሚሉት የአዳራሽ መብራቶች አቅመ ደካማነታቸውን ሸሽገውላቸዋል፡፡ እንደ እኔ በሁኔታው ተመስጠው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በአግራሞት ከሚከታተሉት ታዳሚዎች ባሻገር ሁሉም ወደ መድረክ ጐራ ብሎ አሊያም ደግሞ ባለበት የማይንቀሳቀስ የለም፡፡
ተመስጦዬን እንክትክት አድርጋ ይህን የደራ ትእይንት ትቼ አይኔንም ቀልቤንም ለሷ ጀብቼ እያባበልኩ እንዳወራት ያደረገችኝ ሃድራ ናት፡፡ ቁንጅናውን ቢሮ ውስጥ ከተሰቀለው ፎቶዋ ላይ አፍጥጬ ለወራት የኮመኮምኩት ሚጢጢ ቆንጆ! የወሎ ወዘናና ደም ግባት አብነት! ዓይኗን ገለጥ ሸፈን ስታደርገው የተቆጠበ ፈገግታዋን ለመግለ እነዚያ ጭምቱን ሁሉ እንደ ሴሰኛ ምራቅ የሚያስውጡ ጥርሶቿን ብልጭ ስታደርጋቸው፣ ከአጓጊ ከናፍሮቿና ከጉንጯ ስርጉድ ጋር ተባብረው የልብ ምትን ቀጥ አድርገው፣ ህዝብ አዳምን እንዲገድሉ ወይ በእግዜር አሊያም በሾይጣን የተኸለቁ ነው የሚመስሉት፡፡ ሳወራት ትመልስልኛለች፤ ስጠይቃት ዓይኖቿን ከዚያና እዚህ እያንከባለለች እያፈረች የሆነ ነገር ትለኛለች፡፡ የፈጣሪ ያለህ ስታፍር እንዴት ታምራለች! ቀጥ አድርጐ ማቆም ነበር፡፡
እንደምንም ጉልበቴን አሰባስቤ ዓይኔን ወደዚህኛው ትእይንት ሳዞር፣ መድረኩ በአፋርኛ ሙዚቃ ጨፋሪዎቹ ተጨናንቋል፡፡ ከለበሰችው ጥቁር አበያ ላይ ነጭ ሂጃብ የጠመጠመችው ወጣት፣ ብዙም እሷን ማጀብ ካልተሳካለት ኦርጋኒስት ጋር ህዝቡን ያነቃንቁታል፤ ውሸት መናገር ከሌለብኝ ይህን ቀውጢ በታዛቢነት ከኔ ውጭ የተከታተለው ሌላ ደነዝ ያለ አይመስለኝም፡፡
የሙዚቃው መጨረሻ ለአፍታም ቢሆን በመቋረጡ ሁሉም ወደ ቦታው ተመልሶ እንዲረጋጋ ያደረገው ይመስላል፡፡ ዓይኖቼም እየዘለለች ያን ሁሉ ታዳሚ ያስጨፈረችውን ኮረዳ ሸኘት አድርጐ ሊመለስ ተከትሏት መዳረሻዋ የሚያውቃቸው የሥራ ባልደረቦቹ ሆነው ሲያገኝ እንዳፈጠጠ ቀረ፡፡ ያወራሉ፡፡ ይሳሳቃሉ፡፡ ይሄ ሳይበቃቸው የሚቀጥለውን ሙዚቃ ተጣምረው እስክስት ወረዱ፡፡ ..አሸነፈችው! አሸነፈችው!.. አልተባለም እንጂ ሁኔታውን ላስተዋለ እንጨት ሲሰብሩ አብረው ያደጉ ሚዜ እንጂ እንዲህ አንድ ምሽት ያገናኛቸው የሩቅ አገር ሰዎች መሆናቸውን መቀበል ይቸግረዋል፡፡
የዘፈኑ መጠናቀቅ የፈጠረውን ክፍተት ተጠቅሜ በጭፈራቸው መደሰቴን ፈገግታዬን በእጅ ምልክት አስከትዬ ገለኩላቸው፡፡ ሞቅ አድርገው ምላሻቸውን ቸሩኝ፡፡ ያች አገር ምድሩን ቀውጢ ያደረገች ወጣት ጋርም የመጀመሪያውን የዓይን ለዓይን ግንኙነት ፈፀምን፡፡ ጥሎብኝ የጠመጠመ እወዳለሁና - ቀርቤ ሳላያት ተመችታኛለች! ያው አፋር ጋር በዚህ አይነት ነገር ቀልድ ስለሌለ ተመችታኝ እንደምትቀር አልተጠራጠርኩም፡፡
*   *   *
ሰዓቱ ከእኩለ ሌሊት አለፍ እንዳለ ነው የዋዜማውን ዝግጅት በበቃኝ ተሰናብተን ጐናችንን የምናሰፍርበት ቦታ ፍለጋ የጀመርነው፡፡ ምስጋና ይግባውና ያ ምስኪን ሃኪም ያዘጋጀልን ቤት እኛኑ እየጠበቀች ነው፡፡ በጉዞ የደከመ ሰውነታችንን ለማሳረፍ እየተጨዋወትን ወደ ክፍላችን የምናደርገውን ጉዞ ገታ ያደረግነው የአንዱ ጓደኛዬ ስም ሲጠራ ነበር፡፡ ድምፁ ወደ መጣበት አቅጣጫ ዞርን - የመድረኩ ፈርጥ ሆና ያመሸችው የአፋር ወጣት ነች፡፡ ሁለት ሴቶችም አብረዋት አሉ፡፡ ማደሪያ እንደሌላቸው ስለገለፁልን እኛ ጋር ሊያድሩ እንደሚችሉ ተነጋግረን ጉዞ ወደ ማደሪያችን ቀጠልን፡፡ ከኔ ውጭ ያሉት ልጆች ጋር አብረው ስለነበሩ እየተጨዋወቱ ወደ ድሬ ሮቃዋ ቤታችን ገባን፡፡ የሚነጣጠፉ ነገሮችን አመቻችተን የተለያዩ ጥግ ይዘን ተቀመጥን፡፡ ከእኛ በተጨማሪ እኛ ጋር አብረው ሲደክሙም ሲጨፍሩም ያመሹት የቤቱ ባለቤትና የመንደሩ ወጣቶች ከኛው ሻሚያ ተሰይመዋል፡፡ እንቅልፍ አናቴ ላይ ወጥቶ በጉልበት ዓይኔን ሊያስገጥም ግብ ግብ ተያይዞኝ ለመተኛት ጓጉቼ የመጣሁት እኔ ብቻ እንደሆንኩ የገባኝ በእግራችን መሰብሰብ ምክንያት ከመሃላችን በቀረው ክፍተት ላይ የእኔ አይነቱ አቅመ ቢስ ብቻውን የማይችለው ዙርባ ጫት ዘፍ አርገው ሲጥሉት ነው፡፡
ከወደ በሩ በኩል አንድ ሁለት ሰው አለፍ እንዳልን በእድሜዋ አራት አስሩን ልትደፍን ትንሽ የቀራት ከወደ ጭፈራ የመጣችው ሴትዮ ተቀምጣለች፡፡ ጃቬኖ ከሷ በመቀጠል ግራና ቀኙን እየቃኘ ጨዋታውን የሚያደራበት ምርቃኑን የሚያዥጐደጉድበት ሃድራውን የሚያፈካበት ቦታ ይዟል፡፡ ዘግየት ብዬም ቢሆን ስሟ አሚናት (ስሟ የተቀየረ) እንደምትባል ያወኳት ያች የአፋር ዳንኪረኛ ሀሁ... እንደ¸ÃSö_‰T መምህር ጃቬኖ ላይ ዓይኗን እንደጣለች፣ ከጐኑ ሆና ወሬዋን ትሰልቃለች፡፡ የሚያስቅ ሲሆን ትስቃለች፤ ቁምነገር ሲሆን ትቆምራለች፡፡ ብቻ ቀልቧን የገዛው የድሬ ሮቃ የኔታዋ የመራትን ታደርጋለች፡፡ ስሟን ያላወኳት ጠይም ደርባባ ወጣት አሚናትን በግራ ትከሻዋ ደገፍ ብላ ጠባቧ ቤታችንን ታድማለች፡፡ ከሷ ቀጥሎ ሀብታይ፣ ከሱ ደግሞ እኔ በፋኖስ ብርሃን ተፋጠን ተቀምጠናል፡፡
*   *   *
የተጋደመው ጫት ውጤቱን እያሳየ ጨዋታው እየደመቀ ሲሄድ የጭፍራዋ ድምፀ መረዋ ከተሸለመችው ብር የጋበዘችንን ለስላሳ እየተጐነጨሁ ሌሊቱ እንዳልጠበኩት እያሳለፍኩት ነው፡፡ እኔ የቂምሃው ተሳታፊ አለመሆኔና የእሷም እንዲሁ መሆን - ሁለታችንም እንቅልፍ መጣሁ መጣሁ እያለ ዓይናችን ላይ መንቀዋለሉ የጋራ ፍላጐታችን ሆነና ከጋባዣችን ጋር እንድንነጋገር እድሉን ሰጠኝ፡፡ ይባስ ብሎ በእኔ በኩል የነበረችውን ትንሽ ክፍተት ተጠቅማ ጋደም ካለችው ጠይም ጓደኛዋ ጐን እንድትተኛ ዘመዷ እንደሆነች ከጠረጠርኳት በሰል ካለችው ሴትዮ የተሰጣትን ምክር ተቀብላ ከጐኔ አረፍ ማለቷ የበለጠ ለመግባባታችን እግዜር ሰጥ ሁኔታ ፈጥሮልናል፡፡የለበስኩትን ስስ ሸሚዝ ከቁብ ሳይቆጥሩ ንዳዳቸውን የሚያጋቡብኝ እግሮቿን በጀርባዬ ዘርግታ፣ ከሹክሹክታ ከፍ በሚል የድም ጩሀት ደስ ያላትን ርእስ እያነሳች ታወራኛለች፡፡ እሷን ተወት አድርጌ ወደ ጀመአው ዓይኔን ብመልስ እንኳ ተረጋግቶ ያልተዘረጋው እግሯን ስታንቀሳቅሰው ወዲያው ዓይኔን ወደ እሷ መልሼ ወሬ እጀምራለሁ፡፡ ስለ ድምጿ ማማር፣ ስለጭፈራዋ ውበት እያንቆለጳጰስኩ አዋራታለሁ፡፡ ከዚህ ውጭ ምን የጋራ ነገር ኖሮን በሌላ ርእስ ላይ ላዋራት እችላለሁ!?
እንቅልፍና ድካሙ ምርቃናው የፈጠረው የዝምታ ድባብ ታክሎበት፣ ጨዋታው ጡዘቱ ላይ ደርሶ ቁልቁል ወደ ዝምታ ጉዞ ጀምሯል፡፡ አሚናትም ከሚታይባት ድካም በተጨማሪ ህመም ቢጤ ሳይሰማት አልቀረም መሰል ትኩሳቷ ጨምመሯል፤ ቀይ ዳማው ፊቷም ፈገግታውን ተቀምቶ ደብዝዟል፤ አልፎ አልፎ ማቃሰቷም ህመሟን የሚገል ሌላ ምልክት ነበር፡፡ ስሜቷን ለመጠየቅና ምላሽ ለመስጠትም ከቤቱ ውስጥ ለእሷ ከእኔ የቀረበ የለምና - ስታመም እናቴ ለኔ እንደምታደርግልኝ ግለቷን ለመለካት እጆቼን አንገቷ ስር እያስጠጋሁ ጤንነቷን እጠይቃታለሁ፤ እጆቿን እንደ ህፃን ልጅ እያሻሸሁ እንቅልፍ እንዲያሸልባት xÆብላ¬lhù”” ድንገት እጆቿን ማሻሻቴን ካቆምኩ ሥራዬን እንድቀጥል ምልክት ትሰጠኛለች፤ እኔም እቀጥላለሁ፡፡

Read 6574 times