Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:33

ጆኒ ዲፕ በ..ፓይሬትስ.. ፊልሞቹ ገቢው 350 ሚ.ዶላር ደረሰ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጆኒ ዲፕ ..የፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያንን.. 5ኛ ክፍል ለመስራት ስምምነት ማድረጉን ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር አስታወቀ፡፡ የፊልሙ 4ኛ ክፍል ..ፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያን ስትሬንጅ ኦፍ ታይድስ.. በዓለም ዙሪያ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት የዓመቱን ከፍተኛ የገበያ ስኬት አስመዝግቧል፡፡ ጆኒ ዲፕ ከ..ፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያን.. 5ኛ ክፍል ፊልም የሚያገኘው የገቢ ድርሻ 350 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

በዚህ ፊልም ላይ ጆኒ ዲፕ የሚጫወተው ..ካፒቴን ጃክ ስፓሮው.. የተባለ ገፀባህርይ ሲሆን የዚሁ ገፀባህርይ አሻንጉሊቶች ሽያጭ ለተዋናዩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሆነውለታል፡፡ ከ2003-2010 የተሠሩት አራቱ የ..ፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያን.. ፊልሞች በዓለም ዙሪያ ያስገቡት ገቢ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በአሜሪካ የሙዚቃው ገበያ ተሟሙቋል
በአሜሪካ የሙዚቃ ገበያ የተሟሟቀ እንደሆነና በቢልቦርድ ¿N«r? የገቡ የሙዚቃ አልበሞች የሽያጭ ገቢ ከባለፈው ዓመት በ8.5% እድገት ማሳየቱን የኔልሰን ሳውድ ስካን መረጃ አመለከተ፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው የሮክና ራፕ ሙዚቃ ስልቶች ገበያ እየደራ ሲሆን ካንትሪ፣ የጃዝ እና የአርኤንድ ቢ ሙዚቃዎች እየተሳካላቸው አይደለም፡፡ የቢልቦርድ መጽሔት እንዳመለከተው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው በ2011 አጋማሽ ላይ የአልበሞች የነጠላ ዜማዎች የሙዚቃ ቪዲዮዎች ሽያጭ ብዛት 821 ሚሊዮን ሲደርስ ቢያንስ 10 የሙዚቃ ስራዎች ያሉባቸው አልበሞች እስከ 221.5 ሚሊዮን ቅጂ ተቸብችበዋል፡፡ በሙዚቃ አልበም ሽያጭ ዘንድሮ ገበያውን የምትመራው 21 የተባለ አልበሟን ለገበያ ያበቃቸው አዴሌ ናት፡፡ አዴሌ 2.5 ሚሊዮን ቅጂ በመሸጥ ገበያውን ስትመራ፤ ሌዲጋጋ በ1.15 ሚሊዮን ቅጂ ሽያጭ ትከተላለች፡፡

Read 5902 times