Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 11:57

ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግሥትን ለዜጎች ረሃብ ተጠያቂ አደረጉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ርቅ ምክንያት ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች ከአምናው በእጥፍ መጨመሩ አሳሳቢ እንደሆነ የገለ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት፤ ለረሃብተኞቹ አስቸኳይ እርዳታ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በመጥቀስ ለረሃቡ መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡በአምስት ዓመታት የእርሻ ምርት በ40 በመቶ እንደጨመረ የሚገልው መንግሥት፤ በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ 4.5 ሚ. ሰዎች ከመጠባበቂያ ክምችት እርዳታ እየተከፋፈለ እንደሆነ ገልል፡፡

ድርቅ ተፈጥሯዊ ቢሆንም ረሃብን በዘላቂ መፍትሔ መከላከል እንደሚቻል የገለ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፤ በየዓመቱ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው የዜጎች ረሃብ፤ በመንግሥት የተሳሳተ ፖሊሲ ዘላቂ መፍትሔ የማያስገኝ በመሆኑ ሳቢያ የተፈጠረ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡  
ዘንድሮ የተከሰተው ርሃብ በአጋጣሚና በአንድ ሌሊት የተከሰተ እንዳልሆነና ካለፉት ዓመታት ረሃብ ጋር እንደሚመሳሰል የገለት የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ዘውዴ፤ መንግሥት ሁሉንም በሚያሳትፍ ውይይት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ፖሊስ የመቀየስ ሃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ከምርት መጠን ጋር በላይ የሆነ የገንዘብ ፍሰት የዋጋ ንረትን እንደሚያስከትል አቶ ተመስገን ጠቅሰው፤ መንግሥት ወጪዎቹን በመቀነስ ተጨማሪ የገንዘብ ፍሰትን እንዲገታ በተደጋጋሚ ተናግረናል ብለዋል፡፡ መንግሥት በተጨማሪ የገንዘብ ፍሰት የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰ በመጠቆምም፤ የከተማ ነዋሪዎች በዋጋ ውድነት እንደተጎዱ ተናግረዋል - አቶ ተመስገን፡፡
አሁን የተፈጠረው ችግር የምግብ እጥረት ነው ወይስ ረሃብ በሚል የምንሰማው የፖለቲካና የቃላት ጨዋታ መፍትሔ አያስገኝም የሚሉት የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ፤ መንግሥት ስለድርቁ ሁኔታ አስቀድሞ መረጃ አለመስጠቱ አሳሳቢ ሆኖብናል ብለዋል፡፡
ከረሃቡ በተጨማሪ በተለይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች ህዝቡ እንደ ኑሮ መሠረት የሚያያቸው ከብቶች በብዛት መሞታቸው ችግሩን እንደሚÃwúSbW አቶ ሙሼ ጠቅሰው፤ በረሃቡ ምክንያት የዜጎች ህይወት እንዳይጠፋ አፋጣኝ እርዳታ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልዋል፡፡
ድርቅ ተፈጥሯዊ እንደሆነና በተለያዩ አገራትም እንደሚከሰት ቢታወቅም በብዙ አገራት ርሃብ እንደሚፈጠር የተናገሩት  አቶ ሙሼ፤ በየዓመቱ ለሚከሰተው ረሃብ የመንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስህተቶች መንስኤ ናቸው ብለዋል፡፡ መንግስት በአርሶ አደሩና በአርብቶ አደሩ ዙሪያ እየሰራሁ ነው ቢልም የተጠበቀውን ያህል ለውጥ አልመጣም ያሉት አቶ ሙሼ፤ ከመጠን በላይ በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማራው የአገራችን ገበሬ ወደ ዘመናዊ ብቻ ሳይሆን ቀስ በቀስ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት የኢኮኖሚ ዘርፎች የሥራ ዕድል እንዲያገኝ የሚያስችል ፖሊሲ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ መንግሥት የአገራችን ገበሬ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ ከመሬቱ ጋር ተጣብቆ እንዲኖር ይፈልጋል በማለትም አቶ ሙሼ ተችተዋል፡፡
በኢኮኖሚ ድቀቱ፣ በዋጋ ግሽበቱና በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ እስከዛሬ ባልታየ ደረጃ ለማኝነት፣ ጎዳና ተዳዳሪነት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ የመንገድ ላይ ዘረፋና ውንብድና እየተስፋፋ ነው የሚሉት አቶ ሙሼ፤ መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲውን በመቀየር፤ ዜጎች በሥራ ፈጣሪነትና በንግድ ሥራ የኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ክፍለ ኢኮኖሚን እያስፋፉ የኑሮ ገቢ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ብለዋል፡፡
የመኢአድ ዋና ፀሃፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በበኩላቸው፤ 4.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንደሚÃSfLgW በመንግስት ቢነገርም ቁጥሩ ይህ ብቻ ነው የሚል ዕምነት እንደሌላቸው ሲገልፁ፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በብልሹ አስተዳደርና በሙስና በሃገሪቱ ታሪክ እጀግ የከፋ ድህነት ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡
አገር በልመና አያድግም የሚሉት አቶ ተስፋዬ፤ ትውልድንና አገርን ለማዳን ብሄራዊ ጥሪ ተደርጎ ኢትዮጵያ ከገባችበት ለማውጣት ርብርብ ያስፈልጋል፤ የከተማ ገመና ተሸፍኖ እንጂ በቀን ሁለት ጊዜ አይደለም አንድ ጊዜ ጠግቦ እንኳ የሚያድር የለም ብለዋል፡፡

 

Read 5214 times Last modified on Monday, 18 July 2011 12:51