Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 July 2011 12:50

..ስልቻ ተበላሸ..

Written by 
Rate this item
(4 votes)

..ምኑጋ..
..ሲነፋ..
..ሲነፋ አይደለም፤ መጀመሪያ ሲገፈፍ ነው!..
አንድ ሰውዬ ሚስቱ የመስማት ችሎታዋ ከቀን ቀን እየደከመ በመምጣቱ በጣም ይጨነቃል፡፡ ስለዚህ ወደሀኪም
ሄዶ ምክር መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ያምንበታል፡፡
አንድ ቀን ወደ ሐኪም ይሄድና እንዲህ ሲል ÃSrÄL-
..ዶክተር፤ አንድ ትልቅ ችግር ገጥሞኝ ነው የመጣሁት..
ዶክተሩም፤
..ምን ችግር ገጠመህ?..
ሰውዬው፤
..ባለቤቴ የመስማት ችግር እንዳለባት አውቅ ነበር..
..እሺ?.. ዶክተሩ በጥሞና ያዳምጣል፡፡

..አሁን ግን ከቀን ወደቀን ችግሯ እየተባባሰ መጣ..
..ለምን?..
..ለምን እንደሆነማ አላውቅም፡፡ ግን ብሶባታል፡፡ ያንን እርግጠኛ ሆኜ ለመናገር እችላለሁ፡፡ በጣም አስጨንቆኛል
ነገሩ፡፡..

ዶክተሩም፤
..ወደሌላ የህክምና ደረጃ ከማለፌ በፊት አንድ የፍተሻ ሙከራ ማድረግ ይኖርብኛል..
ሰውዬው፤
..ምን ዓይነት ፍተሻ ዶክተር?..
ዶክተሩ፤
..ልነግርህ ነው፡፡ አንተ ብቻ እኔ የምነግርህን ነገር ሄደህ እቤትህ ትፈጽማለህ..
..መልካም እንዳሉኝ አደርጋለሁ፡፡ ብቻ ካቅሜ በላይ እንዳይሆን ዶክተር..
..በጭራሽ ካቅምህ በላይ አይሆንም፡፡ ማንም በቀላሉ ሊሠራው የሚችለው ነገር ነው፡፡..
..እሺ ምን ማድረግ አለብኝ?..
..ቤት ትሄድና ከባለቤትህ ጀርባ በተለያየ ርቀት ላይ እየቆምክ፤ ጥያቄ ትጠይቃታለህ..
..ምን ዓይነት ጥያቄ ነው የምጠይቃት?..
..የፈለከውን..
..በጣም ጥሩ፡፡ በምን ያህል ርቀት ላይ ልቁም?..
..በመጀመሪያ በአሥር ሜትር ርቀት ላይ ቆመህ ትጠይቃታለህ..
..በጄ..
..ቀጥለህ በአምስት ሜትር ርቀት ላይ ትቆምና ትጠይቃለህ..
..በጄ..
..በመጨረሻ፤ በጣም ቀርበሃት ከጀርባዋ ትቆምና ትጠይቃታለህ..
..እሺ ዶክተር ያሉኝን አደርጋለሁ፡፡´
ሰውዬው የዶክተሩን ምክር ይዞ ወደቤቱ ይሄዳል፡፡ ባለቤቱ ወደ ምድጃው ፊቷን አድርጋ ምግብ ትሠራለች፡፡
ስለዚህ ከጀርባዋ በግምት አንድ አሥር ሜትር ርቀት ላይ ይቆምና፤
..ውድ ባለቤቴ፤ ዛሬ ለእራት ምን አዘጋጀሽልኝ?.. ሲል ይጠይቃታል፡፡
ምንም መልስ የለም፡፡
ወደ አምስት ሜትር ያህል ይጠጋና ደግሞ ይጠይቃል-
..ውድ ባለቤቴ፤ ዛሬ ለእራት ምን አዘጋጀሽልኝ?..
አሁንም ምንም መልስ የለም፡፡
በመጨረሻ አጠገቧ ደርሶ ከጀርባዋ ይቆምና፤
..ውድ ባለቤቴ፤ ዛሬ ለእራት ምን አዘጋጀሽልኝ?.. ይልና ይጠይቃታል፡፡
ባለቤቱ ወደ እሱ ዘወር B§-
..ለሦስተኛ ጊዜ መናገሬ ነው - ሹሮ እየሠራሁ ነው አልኩህ!..
ለካ መስማት እያቃተው ያለው ራሱ ባልየው ኖሯል!
* * *
አንዳንዴ ስለሌሎች በደንብ እናውቃን ብለን የምንገምተው፤ ስለራሳችን የምናውቀው ነገር ውሱን በመሆኑ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሌሎችን ..እንዲህ ናቸው..፣ ..እንዲህ እየሆኑ ነው..፣ ..የዚህ ዓይነት ስጋት አለን.. እያልን ልንናገር እንችላለን፡፡ አልፈን ተርፈንም ስጋቱን ለማስወገድ እንደዚህ ዓይነት እርምጃ መውሰድ አለብን በማለት እንፈጽማለን፡፡ የዕውቀት ውሱንነት ትልቅ አደጋ ነው፡፡ የምናውቀውን ትንሽ ነገር አጋንነን፡፡ ጋራ አሳክለን ማሰብም የዚያኑ ያህል አደገኛ ነው፡፡ ከመነሻው አጥርተን ያላወቅነው ነገር መድረሻችንንም የተዛባ ያደርገዋል፡፡ እኛ የመስማት ችሎታችን እየቀነሰ ሌሎች አይሰሙም እያልን መኮነን እንዳንደማመጥ የሚያደርግ ችግር ነው፡፡ ባልተደማመጥን ቁጥር የተሳሳተ መፍትሔ ወይም እርምጃ ወደመውሰድ እንሸጋገራለን፡፡ ያ ደግሞ ለሀገር ደግ አይደለም፡፡ በአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ ንግግር ከትዕዛዝ የሚቆጠር ነው፡፡ ሁሌ ንግግር ሁሌ ትዕዛዝ ሲሆን ደግሞ አንድ ቀን አልታዘዝ ባይን ይፈጥራል፡፡ ..ብዙ በተናገርክ ቁጥር ጅላጅል ነገር ልትናገር እንደምትችል እወቅ.. የሚባለው ኋላ ሰሚ እንዳታጣ ተጠንቀቅ የሚል መልዕክትም አለው፡፡
ከሌሎች የበለጠ ብልህ መሆን እንጂ የበለጠ ጉልበተኛ መሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚያዋጣ መንገድ አይደለም፡፡ በአስተሳሰብ በልጦ መገኘትን የመሰለ ነገር የለም፡፡
ዊኒስተን ቸርቺል ለአፄ `/o§s¤- ..መሣሪያዎቹን ስጡንና እኛ ሥራውን እንጨርሰዋለን.. አለ አሉ፡፡ አፄ ኃ/ሥላሴም ለቸርችል (1891-1975) በላኩት t½l¤G‰M- ..እኛ ደሞ ሥራውን ጨርሰናል መሣሪያዎቹን ምን እናድርጋቸው?..፤ ብለው መለሱ አሉ፡፡
በጥንታውያን ሮማውያን እምነት ሜርኩሪ የንግድ አምላክ ነው ይባላል፡፡ የሌቦች፣ የቁማርተኞችና በፍጥነት ለማጭበርበር የሚችሉ ሰዎች ሁሉ አለቃ ነው ይባላል፡፡ ራሱ ሜርኩሪ ሲወለድ፤ ክራር ፈጥሯል ይባላል፡፡ በክራር (ፕሮፓጋንዳ) ያማልላል፡፡ ዓለምን የሚያሸንፈው ማናቸውንም ቅርጽ በመያዝ ነው - በየጊዜው ቅርፁን በመለዋወጥ ይሄ ነው የሚባል ቅር እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡ በሱ ስም የሚጠራው ሜርኩሪ የተባለው ፈሳሽ ብረትም የተቀመጠበትን ዕቃ ቅር ነው የሚይዘው - አይጨበጥም፤ አይያዝም የቅር-የለሽነት ኃይል አለውና - ሜርኩሪ የንግድ ህግ ቢያወጣ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል፡፡ እገሌ በሜርኩሪ ነው የበለገው ሲባልም ከመሠረታዊ እምነታዊ አመጣጡ ጋር ይተሳሰርልናል፡፡ ከዚህ ይሰውረን፡፡
አንዳንድ መሪዎች የሜርኩሪን ባህሪ ይጋራሉ ይባላል - ቅር-አልባnTN (formlessness) እንደ አገዛዝ መርህ ይከተላሉና፡፡ የሚታይ ዕቅድ አይኑርህ ለጥቃት ያጋልጥሃልና፣ ይላሉ፡፡ ምንም ነገር እርግጠኛ እንዳይሆን፣ ማናቸውም ህግ የፀና እንዳይሆን ያደርጋሉ፡፡ እንደ ውሃ ፈሳሽና ቅር-አልባ ናቸው፡፡ ከዚህም ይሰውረን፡፡
ህጎች እንዲዋዥቁ የሚያደርጉትም ለዚህ ነው፡፡ አንድ ወጥ ይመስላሉ እንጂ ከዓመታት በፊት የተናገሯቸውና አሁን የሚናገሯቸው ነገሮች ይጣረሳሉ፡፡ ያውም ከልባቸው ይሁን አይሁን የተናገሯቸው ሳናውቅ ነው፡፡
ማኪያቬሊ እንዳለው እንዳይሆን XN«NqQ-
..ለረዥም ጊዜ የማምንበትን አልተናገርኩም፡፡ የተናገርኩትንም አምኜ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ እውነት ተናግሬ ከሆነ እንኳን በብዙ ውሸቶች መካከል ደብቄው ስለሆነ ለማግኘት አደጋች ነው.. ይለናል፡፡
ለመግዛት የሚያመቸንን ዓይነት ውሸት ስንናገር ነው የምንኖረው ማለቱ ነው፡፡ እነሱንም አንጥሮ ለማውጣት ይቸግራችኋል ውስጣቸው ጥበብ ስላለ ማለቱ ነው፡፡ የማናቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዞ ነገረ-ሥራ ከአናቱ ሳይሆን ከውስጠ-መሠረቱ ለማየት መቻል መታደል ነው፡፡ የፖለቲካ መሪዎችን፣ የአለቆችንና የኃላፊዎችን ንግግሮች የዛሬን ብቻ ሳይሆን የትላንት የትላንት-bStEÃ ፍጥረተ-ነገራቸውን ማየት ተገቢ ነው፡፡ መዋዠቅ ነው ዋና ባህሪያቸው፡፡ መዋዠቅ የገበያ ባህሪ ነው፡፡ የፖለቲካችንም ባህሪ ነው፡፡ ሲሻን የታክቲክና የስትራቴጂ ለውጥ እንለዋለን፡፡ ሲሻን ሥር-ነቀል ለውጥ እንለዋለን፡፡ የሚያወጧቸው ህግጋት ጥንተ-ነገራቸው የት ነው፣ ማንስ ላይ ያነጣጠረ ነው? ብለን እንጠይቅ፡፡ ከሜርኩሪ የንግድ አምላክ የመነጩ እንዳልሆኑ በምን እናውቃለን? በፖለቲካ ነጋዴና በኢኮኖሚ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? አነሳሱስ? ምንጩስ ምንድን ነው? እንበል፡፡
..ስልቻ ተበላሸ.. ቢለው
..ምኑጋ?.. አለና ጠየቀው፡፡

..ሲነፋ አይደለም፤ መጀመሪያ ሲገፈፍ ነው.. የተባለው ለዚህ ነው፡፡ ከገፋፊ ይሰውረን!      

Read 6984 times