Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 24 July 2011 07:07

የሳይንስና የእምነት ክርክሩ፤ ከህይወታችን ጋር ይገናኛል?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በኑሮና በመንፈስ ድህነት ውስጥ ተዘፍቆ የስቃይ ህይወትን የሚገፋ መሆኑ
ይዘገንናል፡፡ ነገር ግን፤ የአገሪቱችግር ከዚህም ይከፋል፡፡ በቁጭትተንገብግቦ ህይወትን ለመቀየር
ከመጣጣር ይልቅ፤ የኑሮ ችጋሩንና የመንፈስ ጉስቁልናውን እንደ ..ኖርማል.. ተቀብሎ መደንዘዝ... ከሁሉም የባሰ የጨለማ ህይወት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በየአመቱ 200ሺ ገደማ ህፃናት በምግብ እጥረትና በበሽታ የሚሞቱበት አገርኮ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ያልተያያዘ ትልቅና አሳሳቢ የኑሮ ወይም የመንፈስ ጥያቄ ሊኖረን አይችልም፡፡

ታዲያ፤ ሳይንስን፣ እምነትንና ፍልስፍናን በሚመለከት በአዲስ አድማስ ለተከታታይ ሳምንታት በተካሄዱት የፅሁፍ ክርክሮች ውስጥ፤ ይህ ትልቅ ጉዳይ ጎልቶ አለመነሳቱ አያስገርምም?
እስቲ ነገርዬውን በሁለት ጥያቄዎች እንየው፡፡ ድህነትና ረሃብ፣ ኋላቀርነትና ሚስኪንነት ... የዚያን ያህል ኢትዮጵያ ላይ የተደራርቦ የተቆለለው፤ ከቁጥጥራችንና ከምርጫችን ውጭ የእጣፈንታ ጉዳይ ወይም የአርባ ቀን እድል ስለሆነብን ነው? ወይስ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አንዳንዴ በዘፈቀደ ለመንከላወስ እየወሰነ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተሳሳተ አስተሳሰብ ለመነዳት ፈቅዶ፤ የጥፋት መንገድን ስለመረጠ ይሆን?
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያስብባቸውና መፍትሄ ሊፈልግላቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ታዲያ፤ እያንዳንዳችን በትጋት ማሰብና መፍትሄ ማፈላለግ የሚኖርብን፤ ..ቅድሚያ ለህዝብና ለአገር ማሰብ.. በሚባለው የፋሺስቶች ፈሊጥ አይደለም፡፡ ጥያቄዎቹ እያንዳንዳችንን የሚመለከቱና ከህይወታችን ጋር የተቆራኙ ስለሆኑ፤ ለየራሳችን ስንል ልናስብባቸው ይገባል፡፡ ባናስብባቸውስ?
ጥያቄዎቹን በቸልታ ለማለፍ የምንሞክር ከሆነ፤  የረሃብና የኋላቀርነት ምልክት ሆና በምትታይ አገር ውስጥ የነገሰውን ዘግናኝ ህይወት፤ አሜን ብለን በፀጋ የምንቀበል የድንዛዜ ባሮች ሆነን ለመቀጠል እንፈልጋለን ማለት ነው፡፡ ከዚያም አልፈው፤ ጥያቄዎቹ አስፈላጊ እንዳልሆኑ እንድናምንላቸው እየተጣጣሩ ራሳቸውን የሚያታልሉ ጥቂት አይደሉም፡፡ ይህም አንሶ፣ ..ከኑሮና ከመንፈስ ብልፅግና.. የላቀ ሌላ የህይወት አላማ እንዳለ ለማስመሰል፤ ያረጁ የስብከት ሃሳቦችን ሲተበትቡ፤ ..በእውቀት የተራቀቀ.. የሚመስላቸው አሉ፡፡ ግን ሌላ ትርጉም የለውም - በተራቆተ የወረደ መንፈስ የድንዛዜ ባርነትን የሙጢኝ ይዘው ለመቀጠል ነው የሚለፉት፡፡
በነገራችን ላይ፤ ..የመንፈስ ብልፅግና.. ስል፤ ከህይወት ውጭ የሆነ አንዳች ነገርን ለመግለፅ አይደለም፡፡ ከአእምሮ ተፈጥሮ ጋር በተያያዘ ሰዎች የሚያዳብሩት ወይም የሚያፈርሱት ሰብእና ማለቴ ነው - ለምሳሌ ለእውነታ የመታመን ቅን ሰብእናን መጥቀስ ይቻላል - የመንፈስ ብልፅግናን ለማመልከት፡፡ በተቃራኒው ለጭፍን ስሜት፣ ለይሉኝታና ለግፊት በመሸነፍ እውነታን ለማየትና ለማወቅ አለመፈለግ፤ የመንፈስ መራቆትን ያመለክታል፡፡
ጥያቄዎቹን በድጋሚ እናንሳቸው፡፡ ድህነትና ረሃብ፣ ኋላቀርነትና ሚስኪንነት... በአጠቃላይ የኑሮና የመንፈስ መራቆት ኢትዮጵያ ላይ የተደራረው፤ ከምርጫችን ውጭ በእጣፈንታ ወይም በአርባ ቀን እድል ሳቢያ ነው? ወይስ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በዘፈቀደ ለመደናበር ስለሚፈልግ፤ አልያም በተሳሳተ አቅጣጫ ለመጓዝ ፈቅዶ፤ የጥፋት መንገድን ስለመረጠ ይሆን?     
በሳይንስ፣ በእምነትና በፍልስፍና ዙሪያ የተካሄዱ የፅሁፍ ክርክሮችንና የሃሳብ ልውውጦችን፤ በእነዚህ ጥያቄዎች አማካኝነት በጥቅሉ ከሰው ህይወት ጋር በተለይም kኢትዮጵያውያን ህይወት ጋር አያይዘን ልንመለከታቸው እንችላለን፡፡ ለነገሩማ፤ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ፤ ኑሮንና መንፈስን ለማበልፀግ (ህይወትን ለማለምለም) የማይጠቅም ነገርኮ፤ ከንቱ ልፋት ነው፡፡ ስለዚህ፤ ክርክሮቹንና ሃሳቦቹን፤ ከእውነታ ጋር እያመሳከርን፤ ከህይወታችን ጋር አያይዝን እንመዝናቸው - መጀመሪያ ተጨባጩ እውነታ ላይ በመመስረት፤ ከሚታይ ከሚዳሰስ ተጨባጭ መረጃ ጋር እያገናኘን መመዘን ... ከዚያም፤ መረጃዎችን (እውነታውን) በመልክ በመልክ አቀናብረን ጭብጥ ለመያዝ በሚያስችሉን መሰረታዊ ሃሳቦች አማካኝነት መመዘን፡፡ መጀመሪያ በተግባር፤ ከዚያም በቲዎሪ፡፡

የመኖር ያለመኖር ጥያቄ
መቼም፤ ሰሞኑን ሰምታችኋል፡፡ ኧረ አለም ሁሉ ሰምቶታል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሆቹ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ፤ የረሃብተኞች ቁጥር ጨምሯል - ወደ 11 ሚሊዮን፡፡ ከሞት የሚያድን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሎ ከተነገረላቸው የረሃብ ተጠቂዎች መካከል 4.5 ሚሊዮኖቹ ኢትዮጵያዊÃN ናቸው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሴፍቲ ኔት በሚል ስያሜ በብር እርዳታ የሚያገኙ 8 ሚ. ገበሬዎች አሉ - በየአመቱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ በሚመጣ የእርዳታ ገንዘብ፡፡ ያለ እርዳታ የመኖር አቅም ያልፈጠሩ ከ12 ሚ. በላይ ኢትዮጵያዊÃN ገበሬዎችና አርቢዎች! ... ለዚያውም የከተማው ድሃ ሳይጨመርበትኮ ነው፡፡
በአውሮፓና በአሜሪካ፤ ሚሊዮን ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በረሃብ እየተሰቃዩ የሞት አፋፍ ደርሰዋል ሲባል አንሰማም፡፡ ታዲያ፤ ኢትዮጵያ ከአመት አመት በማያቋርጥ ረሃብ አለምን የምታስለቅሰው ለምንድነው? የእጣፈንታ ጉዳይ ወይም በራሳችን የተሳሳተ አስተሳሰብና ምርጫ?
በእርግጥ አምና የረሃብተኛው ቁጥር ከ3 ሚ. በታች እንደሆነ ተነግሮ ነበር፡፡ ያኔ ዜናው በሚዲያ ተቋማት ሲሰራጭ ምን ተብሎ እንደነበር አታስታውሱ ይሆናል፡፡ የረሃብተኛው ቁጥር ሊቀንስ የቻለው በትክክለኛና በውጤታማ የመንግስት ፖሊሲ ነው ተብሎ ነበር፡፡ እሺ፤ ይሄ እውነት ነው እንበል፡፡ ግን፤ ዘንድሮስ የረሃብተኛው ቁጥር የጨመረው፤ በተሳሳተና በውጤት አልባ የመንግስት ፖሊሲ ነው?
8 ሚ. የሴፍቲ ኔት ተረጂዎችን ወይም 4.5ሚ. የረሃብ ተጠቂዎችን እያነሳን፤ የረሃብተኞቹና የተረጂዎቹ ቁጥር የሚጨምረው በመንግስት ፖሊሲ ሳቢያ ነው ብንል እንኳ፤ ፖሊሲውን ማስተካከልና ከረሃብ መውጣት ሳንችል ለአመታት የምንቀጥለው ለምንድነው የሚል ጥያቄ መምጣቱ አይቀርም - የእጣፈንታና የአርባ ቀን እድል ሆኖብን ነው? ወይስ በዘፈቀደ፣ የተሳሳተ አስተሳሰብና የጥፋት መንገድ ስለመረጥን?
እውነታውን በማስተዋል፤ መረጃዎቹን በመመርመር፤ ስህተቶቹን በማረምና የጥፋት መንገድን በማስወገድ፤ አስተሳሰባችንን ማስተካከል፤ የመፍትሄ ሃሳብ ማበጀት፤ ከዚያም ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን - ይሄው ነው ከትክክለኛ ፍልስፍና የሚመነጭ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ፡፡
ወይም ደግሞ፤ ዶ/ር ፍቃዱ አየለ እንደሚሉት ..እምነትን.. መከተል እንችላለን፡፡ በሳይንስና በፍልስፍና ሊታወቁ የማይችሉ ነገሮች እንዳሉ ለማሳመን ሲያስረዱ፤ ለብዙ አመታት ያለ ምግብና ያለ መጠጥ መኖር፤ እሳት ላይ ያለ ቃጠሎና ያለ ስቃይ መራመድ፤ በፀሎት የተለያዩ ነገሮች እንዲፈፀሙ ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል - ዶ/ር ፍቃዱ፡፡ ይሄ ነገር በሳይንስ ወይም በሰው የአእምሮ አቅም ሊታወቅ የማይችል ከሆነ፤ እሳቸውን አምነን በጭፍን እንቀበላቸው?
ከአገሪቱ ኋላቀርነት ጋር ለብዙ ሺ ዘመናት፤ ህፃንና አዋቂ፣ መሃይምና ፊደል የቆጠረ፣ ገበሬና ጠንቋይ፤ የተለያዩ ምትሃቶችን አምነው ለማሳመን ሲሞክሩ በመኖራቸው፤ የዶ/ር ፈቃዱ አባባል ለአገራችን አዲስ ነገር አይደለም - ..በሳይንስ ወይም በሰው የአእምሮ አቅም አይታወቅም፤ እኔን አምነህ ተቀበል.. እንደማለት፡፡
ሳይንስኮ፤ ሌላ ነገር ሳይሆን፤ የምንናገረውንም ሆነ የምንሰማውን ሃሳብ፤ የምናሰላስለውንም ሆነ የምንመራበትን ሃሳብ፤ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እያመሳከሩ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ..በሳይንስ አይታወቅም፤ እኔን አምነህ ተከተል.. ማለትስ? ..ሃሳቦቼ ከእውነታው ጋር ስለማይገጥሙ፤ ከእውነታው ጋር እያመሳከርኩ የሃሳቦቼን እውነተኛነት ማሳየት አልችልም.. እንደማለት ነው፡፡
..ሃሳቦቼ እውነተኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ አትችልም፣ xÃSfLGHM፡፡ ስለዚህ እኔን ወይም እንትናን አምነህ ተቀበል.. በሚል የዶ/ር ፈቃዱ የእምነት መንገድ ለመጓዝ የሚሞክር ሰው፤... ለእውነታ የሚታመንና ለእውነት ክብር የሚሰጥ የቅንነት ስብእናን (የቅንነት መንፈስን) ማዳበር አይችልም፡፡ ነገር ግን መንፈስን ብቻ ሳይሆን፤ ኑሮንም የሚያራቁት መንገድ ነው፡፡ ለእውነታ የመታመን ቅንነትን ሸርሽረን፤ መንፈሳችንን እያራቆትን፤ ሃሳቦችን ሳንመረምር የዶ/ር ፍቃዱ አይነት ኋላቀር ሃሳቦችን በእምነት ከተቀበልን፤ ኑሯችን ምን ሊሆን እንደሚችል በእውን ተመልከቱ፡፡  

ሳይንስና እምነት (በተግባር)
ያለ ምግብ ለብዙ አመታት መኖር፤ እሳት ላይ ተዝናንቶ መራመድ... ድንቅ አይደል! ለመሆኑ፤ ያ ሁሉ ሚሊዮን ህዝብ፣ ህፃናት ሳይቀሩ በረሃብ የሚሰቃዩት፤ ብዙዎቹም የሚሞቱት፤ የዶ/ር ፍቃዱን ድንቅ ..የእምነት ሃሳብ.. የሚነግራቸው አጥተው ነው? ያለምግብ ለብዙ አመታት ያለሃሳብ መኖር እንደሚችሉ አምነው ረሃባቸውን ማስታገስ እየቻሉ፤ አለምን ሁሉ በልመና በማስቸገር የኢትዮጵያን ስም ያረክሳሉ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ቢያንስ በፀሎት ማንኛውንም ነገር ምግብንም ጭምር ማግኘት እንደሚችሉ የሚነግራቸው ሰው ቢያገኙኮ ግልግል ነበር፡፡ ወይስ ለፀሎትም ሰነፉ?
በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በኑሮ ውድነትና በችጋር እየተማረሩ ወደ ውጭ የሚሰደዱት፤ እዚሁ አገራቸው ውስጥ በቀላሉ ያለምግብ ያለመጠጥ ህይወታቸውን ማሻሻል እንደሚችሉ፤ እሳት ውስጥም ቢሆን ተዝናንቶ መኖር እንደማያቅት የሚሰብካቸው ሰው ስላላገኙ ይሆን? ..ኧረ ይሄ የኑሮ ውድነት መፍትሄ ይበጅለት.. እየተባለ ምሬት፣ አቤቱታና የመፍትሄ ሃሳብ የሚቀርበው፤ ያለ ብዙ ድካም በፀሎት ማስተካከል እየቻልን ድከሙ ሲለን ነው?
እያንዳንዱ የገበሬ ቤተሰብ ሰፊ የእንስሶች በረት የሚኖረው፤ እያንዳንዱ የገበሬ ልጅ የመጀመሪያ ስራው እረኝነት የሚሆን ይመስለናል አይደል? እረኝነት በቀላሉ እንደማይገኝ አለማወቃችን! ዘንድሮ በየካቲት የወጣው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ አዲስ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ 15ሚ ገደማ ከሚሆኑት የገበሬ ቤተሰቦች መካከል፤ 65 በመቶዎቹ ምንም በግ የላቸውም፤ 73 በመቶዎቹ ምንም ፍየል የላቸውም፡፡ 71 በመቶዎቹ አህያ የላቸውም፡፡ ፈረስ ደግሞ ብርቅ ነው፤ 91 በመቶዎቹ፤ ቤተሰባቸው ውስጥ ባለ ፈረስ የለም፡፡ መቼም ፍየልና በግ፤ ፈረስና አህያ ሳይኖር፤ ሰፊ በረት መስራትም ሆነ እረኛ መሆን አይቻልም፡፡
ባለፈው ግንቦት ወር የወጣው የእርሻ ሪፖርትም፤ ተመሳሳይ መረጃ ይዟል - 38 በመቶ ያህል ገበሬዎች በሬ የላቸውም፡፡ መሬት ለማረስ ቢያንስ ሁለት በሬ ያስፈልግ የለ? ግን አብዛኞቹ ገበሬዎች (65 በመቶዎቹ) በቤተሰባቸው ውስጥ ሁለት በሬ ሊኖራቸው አልቻለም፤ አንድ በሬ ብቻ ይኖራቸዋል ወይም ምንም በሬ የላቸውም፡፡
ከሶስት የገበሬ ቤተሰቦች መካከል ሁለቱ፤ በኪራይ ወይም በልመና በሬ ካላገኙ በስተቀር ማረስና እህል ማምረት እንደማይችሉ ይገልፃሉ፡፡ ..ተጨነቁ ሲላቸው እንጂ በሬ ምን ያደርግላቸዋል?.. ብንላቸው፤ ከእነሱ ድህነት በባሰ ሁኔታ ለህይወትና ለኑሮ ክብር የማንሰጥ የመንፈስ ድሆች መሆናችን አይቀርም፡፡ ነገር ግን፤ ማረስና እህል ማምረት ባይችሉ እንኳ፤ ዶ/ር ፈቃዱ እንደሚሉት፤ ሰዎች በህይወት ለመኖር ምግብ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን የሳይንስ እውቀት ወዲያ ብናስቀነጥረውስ? በቃ፤ ገበሬዎቹ ለአመታት ያለ ምግብ መቆየት እንደሚቻል የምናምን ከሆነ፤ ገበሬዎቹ በሬ ምን ያደርግላቸዋል!  
በኤድስና በወባ፣ በኮሌራና በቲቢ ኢትዮጵያውያን የሚሞቱት፤ በሳይንቲስቶች የተፈጠሩ የመድሃኒትና የህክምና ዘዴዎችን ለማግኘት ለሰለጠኑት ሃብታም አገራት የልመና ጥሪ የሚቀርበውስ ለምን ይሆን? ሳይንስ ጎደሎ መሆኑን እየነገረ፤ በጭፍን አምነን እንድንከተለው የሚወተውት ሰባኪ ስላላደለን መሆን አለበት - የዶ/ር ፈቃዱን ሃሳብ ከተከተልን፡፡
በአገራችን የአመቱ 200ሺ ህፃናት በምግብ ጉድለትና በበሽታ የሚሞቱትስ ለምን ይሆን? ከአንድ ሺ ህፃናት መካከል መቶ ያህሉ የሚሞቱት አምስተኛ የልደት በአላቸውን ሳያዩ ነው፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካ ግን፤ አስሩ እንኳ አይሞቱም፡፡ ለምን? አውሮፓና አሜሪካ በፀሎት ብዛት ስለሚበልጡን ይሆን? ፈረንሳይ ውስጥ፤ 25 በመቶ ያህሉ በፈጣሪ ባያምኑም፡፡
ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ የ2009 እትም እንደሚለው ከሆነ፤ አውሮፓ ውስጥ መቶ ሚሊዮን የሚጠጉ ሃይማኖት የሌላቸው ወይም ሃይማኖትን የማይቀበሉ ሰዎች አሉ - ከጠቅላላው ህዝብ 14 በመቶ ገደማ፡፡ በአሜሪካና በካናዳ ደግሞ ደግሞ 42 ሚ ሰዎች ገደማ አሉ - ከህዝቡ 12 በመቶ ያህል፡፡ በአፍሪካ ግን፤ ሃይማኖት የሌላቸው ወይም ሃይማኖትን የማይቀበሉ ሰዎች፤ ከህዝቡ አንድ በመቶ ያህል አይሆኑም - ከ7 ሚ. በታች፡፡ ሳይንስን ሳይሆን እምነትን በመከተል፤ አውሮፓንና አሜሪካን በብዙ እጥፍ XÂSknÄcêlN፡፡ በኑሮና በመንፈስ ብልፅግና ደግሞ በብዙ እጥፍ ያስከነዱናል፡፡
በእርግጥ የአውሮፓ አገራትም፤ ከ500 አመታት በፊት (ያኔ፤ ..እምነት.. ያለ ተቀናቃኝ የነገሰበት በሚባለው የሺ አመታት ዘመን)፤ እንደ ኢትዮጵያና እንደ አፍሪካ፤ በኑሮና በመንፈስ እጅግ የተራቆቱ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በበሽታ የሚሞተው እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ፤ የአውሮፓውያን አማካይ እድሜ ከ30 አመት አይበልጥም ነበር፡፡ ለወራት ገላቸውን የማይታጠቡ፤ በኋላ ቀርነት ከንባብ፣ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ ያልተገናኙ፤ ያለፋታ በሴራ፣ በሽኩቻ፣ በግጭትና በጦርነት የሚታመስ ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቀው የሚሰቃዩና የሚጨፋጨፉ፤ በረሃብ የሚያልቁ ... በአጠቃላይ የዘግናኝ ህይወት መጫወቻ ነበሩ - በገጠር የጎስቋላ ገበሬና በከተማ የሚስኪን ድሆች መነሃሪያ ሆነዋል ለሺ አመታት፡፡
ግን እንዲህ አይነት አስቀያሚ ህይወት የሰው እጣፈንታ አይደለም፡፡ ሳይንሳዊ አስተሳሰብን በመምረጥ፤ ወደ ትክክለኛና ወደ ጠቃሚ ጎዳና የሚገቡ ሰዎች ሲበራከቱ፤ የአብዛኞቹ አውሮፓውያን ህይወት ተቀይሯል - ከ14ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በተከሰተው ሬነሳንስ እንዲሁም፤ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ እያበበ በነበረበት የ18ኛው ክፍለዘመን xþNላይTmNT፡፡ አውሮፓና አሜሪካ በስልጣኔ ጎዳና ብዙ የተራመዱት በእነዚህ ዘመናት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ፤ ሳይንሳዊውን አስተሳሰብ እየሸረሸሩ ሲያመናምኑትና ጭፍን እምነት ሲስፋፋ፤ ምን እንደተከሰተ አስታውሱ - ኮሙኒዝምና ፋሺዝም፣ ሶቭዬትና ናዚ፣ አንደኛውና ሁለተኛው የአለም ጦርነት...፡፡ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ሲስፋፋ፤ የሰው ኑሮና መንፈስ ይበለፅጋል፡፡ በተቃራኒው በተለያዩ ሰበቦች ሳይንስን የሚያጣጥል እምነት ሲንሰራፋ ደግሞ፤ የኑሮና የመንፈስ ጉስቁልና ይነግሳል፡፡

ሳይንስና እምነት (በቲዎሪ)
ሳይንስን የሚያጣጥል እምነት መያዝ ምን ማለት ነው? መቼም ይህን እምነት ለሰዎች ለመግለፅና ለማስረዳት፤ የተለያዩ ሃሳቦችን ሲያቀርብ መስማታችን አይቀርም፡፡ ግን፤ አእምሯችንን ተጠቅመን ገለፃውን ለመገንዘብ፣ ሃሳቦቹን ለመረዳትና እውነተኛ መሆናቸውን ለማረጋጥ የምንችለው እንዴት ነው? በዚህ መንገድ የምንቀጥል ከሆነ፤ የሳይንሳዊ አስተሳሰብ መርሆችን መፈለግ ጀምረናል ማለት ነው - አእምሯችንን ተጠቀመን፣ ሃሳቦችን ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እያመሳከርን መመርመር ይኖርብናል የሚል ሳይንሳዊ ዘዴ ላይ እንደርሳለን፡፡
ዶ/ር ፈቃዱ ግን ይህን አይቀበሉትም - በሰው አእምሮና በሳይንሳዊ ዘዴ ሊታወቁ የማይችሉ ሃሳቦች እንዳሉ በመግለፅ፡፡ ምን ይሻላል? በአእምሮ ካልሆነ ሃሳቦቹን በምን እንመርምራቸው? በጭፍን አምኖ መቀበል ነው ሌላው አማራጭ፡፡ ሃሳቦቹ እውነተኛ መሆናቸውን በሳይንሳዊ መንገድ፤ ማለትም ከእውኑ ተፈጥሮ (ከእውነታው) ጋር እያመሳከርን ማረጋገጥ የማንችል ከሆነ፤ ሃሳቦቹ ከንቱ ይሁኑ ቁምነገር፤ እውነት ይሁኑ ሃሰት እንዴት እንወቅ? በቃ በጭፍን አምኖ መቀበል፡፡
በአጭሩ፤ በአእምሮ አቅምና በሳይንሳዊ ዘዴ ሊታወቁ የማይችሉ ሃሳቦች ይዣለሁ ብሎ መናገር፤ በጭፍን እመኑኝ እንደማለት ነው፡፡ ..ሃሳቦቼ እውነተኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ አትችልም፣ ስለዚህ እኔን ወይም እንትናን አምነህ ተቀበል፡፡ በሰው አእምሮ የሃሳቦችን እውነተኛነት ማረጋገጥ ስለማትችል፤ በአእምሮህ ሳትመረምር ይሄን ወይም ያንን የእምነት መፅሃፍ አምነህ ተከተል.. ... በሚል የዶ/ር ፈቃዱ የእምነት መንገድ ለመጓዝ የሚሞክር ሰው፤ ወዲያውኑ ከአንድ ጥያቄ ጋር ይፋጠጣል፡፡ የየትኛውን ሰው ሃሳብ፣ ወይም የየትኛውን መፅሃፍ ሃሳብ አምኜ ልከተል? አንደኛውን ከሌላኛው ለይቶ ወይም አስበልጦ ለመምረጥ፤ ሁለት ነገሮች መሟላት አለባቸው፡፡ የሃሳቦቹን እውነተኛነትና ዋጋ ለመለካት የምናመሳክርበት መመዘኛ (እውኑ ተፈጥሮ) እንዲሁም ለማመሳከርና ለመመዘን የሚያስችል አቅም (አእምሮ) ያስፈልጋል፡፡
በዚሁ ጋዜጣ የተካሄዱ የሃሳብ ልውውጦችና ክርክሮችን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሃሳብ ልውውጥ ለመማማርና በክርክር ትክክለኛውን ሃሳብ ለማየት የምንጥረው ምን አይነት ማስተማመኛ ይዘን ነው? እውነትና ሃሰትን ለመለየት፣ ትክክልና ስህተትን ለመዳኘት፣ ጥሩና መጥፎን ለመምረጥ የሚያስችል የማመሳከሪያ መመዘኛ መኖሩ አንዱ የማስተማመኛ መሰረት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ማገናዘብና መመዘን የሚችል የማስተዋል አቅም መኖሩ ሁለተኛው የማስተማመኛ መሰረት ነው አለ የሚል ነው ማስተማመኛCN፡፡ ማንኛውም እውቀት በእነዚህ ሁለት መሰረቶችች የቆመ ነው፡፡
አንደኛ፤ ሃሳብ የምንለዋወጥበትና የምንማማርበት አንዳች ነገር መኖር አለበት - ቅጠል፣ ፕላኔት፣ ውሃ፣ ቢራቢሮ፣ ጋላክሲ፣ ዩኒቨርስ ወዘተ፡፡ ምንም ነገር ከሌለ ግን፤ ጨርሶ ማሰብና መማር አይቻልም፡፡ ስለዚህ፣ ማሰብና መማር፣ ሃሳብ መለዋወጥና መማማር እንችላለን የምንል ከሆነ፤ በቅድሚያ አንዳች ነገር መኖሩን አረጋግጠናል ማለት ነው፡፡ ..እውኑ ተፈጥሮ፤ በእውን አለ.. የሚል መነሻ ከሌለ ማሰብና መማማር አይኖርም፡፡ ለዚህም ነው፣ ቀዳሚው መሰረት፤ "existence exists" የሚል መሆን እንዳለበት አየን ራንድ የምትናገረው፡፡
ሁለተኛው መሰረት፤ እውኑን ተፈጥሮ ለማወቅ የሚያስችል የአእምሮ አቅም ይዘናል የሚል ነው፡፡ የማሰብና የመማር አቅም ሳይኖረን፤ ሃሳብ መለዋወጥና መማማር ብሎ ነገር አይኖርም - የሰው አእምሮ የማወቅ ብቃት እንዳለው እርግጠኛ ካልሆንን በቀር፡፡ የሰው የማወቅ ብቃት ደካማ እንደሆነ ወይም እስከነአካቴው ከንቱ እንደሆነ እወቁልኝ እያለ ሊያስረዳንና ሊያስተምረን፣ ሃሳቡን እንድንቀበል ሊያብራራልን የሚሞክር ሰው ቢያጋጥመንስ? የሰው የማወቅ ብቃት ደካማና ከንቱ ከሆነኮ፤ እሱም ሰው ስለሆነ ሃሳቦቹና ማብራሪያዎቹ  ደካማና ከንቱ ናቸው - ሃሳብ ለመለዋወጥና ለመማማር አቅም የለኝም ብሎ እንደመናገር ነው፡፡ ሃሳብ መለዋወጥና መማማር እችላለሁ የሚል ከሆነ ግን፤ የሰው አእምሮ የማወቅ (የማሰብና የመማማር) አቅም አለው የሚል መነሻ መሰረት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
ሊታወቅ የሚችል እውን ተፈጥሮ፤ እንዲሁም ማወቅ የሚችል ህያው አእምሮ፤ የመጀመሪያዎቹ ሁለት መነሻ መሰረቶች ናቸው፡፡ ማወቅ ማለት፤ ስለ እውኑ ተፈጥሮ ማወቅ ማለት ነው - ከዚህ ውጭ ሌላ እውቀት የለም፡፡ እውነት ማለት ደግሞ፤ እውኑን ተፈጥሮ ከማስተዋል የሚመነጭ፣ ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር የተመሳከረ ሃሳብ ማለት ነው፡፡ ግን ሃሳቦቻችንን ለምንድነው ከእውኑ ተፈጥሮ ወይም ከእውነታው ጋር ማመሳከር የሚኖርብን?
ሁሉም ነገር የየራሱ ተፈጥሮአዊ ማንነት ስላለው ነዋ የሚል ምላሽ እናገኛለን፡፡ ትልቁ ዛፍ ድንገት ተነስቶ መራመድና መሮጥ ይጀምራል የሚል ሃሳብ ሊኖረን ይችላል፤ ወይም ድንገት ይሟሟል የሚል ሃሳብ፡፡ ግን፤ ትልቁ ዛፍ ድንገት ይሮጣል ወይም ይሟሟል የሚል ሃሳብ ስለያዝን ብቻ፤ ዛፉ በሃሳባችን የሚታዘዝ አይሆንም፡፡ የራሱ ተፈጥሯዊ ምንነት አለው - በቃ፤ ድንገት አይሮጥም፤ ድንገት አይሟሟም፡፡ ለዚህም ነው ሃሳቦቻችን እውነተኛ እንዲሆኑ ከፈለግን፤ ሃሳቦቻችን እውኑን ተፈጥሮ ከማስተዋል መነሳትና መመሳከር የሚኖርባቸው፡፡ ለዚህም ነው፤ ሃሳቦችን ሳንመረምርና ከእውነታው ጋር ሳናመሳክር በጭፍን አምነን መቀበል የማይኖርብን፡፡
በሌላ አነጋገር፤ የማወቂያ ዘዴያችን፤ ሌላ ሳይሆን፤ እውኑን ተፈጥሮ ማስተዋልና ማገናዘብ ነው፡፡ የማወቂያ መሳሪያችን አእምሮ ነው፡፡ የማረጋገጫ ዘዴያችንም፣ ሌላ ሳይሆን፣ ሃሳቦችን ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር ማመሳከር ነው፡፡ በጥቅሉ፤ ይሄው ነው ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ማለት - observation, hypotesis, experiment (more focused observation) ከሚባሉት የሳይንሳዊ ዘዴ መሰረታዊ ክፍሎች ጋር ልናነፃፅረው እንችላለን፡፡

 

Read 4325 times Last modified on Sunday, 24 July 2011 07:12